ይድረስ ለሰርፀ ደስታና መሃመድ አሊ (ከአባዊርቱ)

ሰርፀ ደስታ የዛሬው ሃተታህ ብዙ ቁምነገሮችን የተማርኩበት ሲሆን ዋናውን ችግርህን በደንብ ተረድቻለሁ፤፤ ፅሁፎችህን በደንብ ተከታትያለሁና፤፤ሳስበው አቢይ ላይ ከባድ ቁርሾ አሳድረሃል፤፤ እንዴት በለኝ፤፤
1) ባለፈው ስለጤፍ ፓተንትነት ጉዳይ ብዙ የምረዳው እያለ እርዳታዬን የፈለገው ወይም ቁብ የሰጠኝ የለም ስለማለትህ
2) የሸገርን መናፈሻ አስመልክቶ ፅንሰሃሳቡ ካንተ እንድድፈለቀና አቢይ የራሱ አስመስሎ ስለማቅረቡ
ዛሬም እዚሁ ክስህ ላይ ብዙ የምንረዳው ነገር እያለ ማንስ ይሰማናል አይነት ፤ አልፎም የአቢይን ጉዞ ሁሉ አስመልክተህ ፕሮቶኮል እንደጎደለው፤፤ ጭራሽ ሰው መለስን ሁሉ እስከመናፈቅ እንደደረሰ፤ ( ይህ ደሞ ጭራሽ ማንነትህን ፍንትው አርጎታል)
ወንድሜ ሆይ፤ ከባድ በኦሮሞ ህብረተሰብ ላይ ቂም አቂመሃል፤፤ ኦነግንና ኦሮሞን ልክ እንደ ስልቻና ቀልቀሎ እኮ ነው ንፅፅርህ፤፤ አደገኛ አካሄድ ነው ያለህበቱ ጉዞ፤፤ ከዚህ ቀደም ሸዋ የራሱ ክልል ያቁዋቅም እንዳላልክ ዛሬ ደሞ የሸዋውን ኦሮሞ  በሌላው እንዴት እንደተበደለ ልትነግረን ይዳዳሃል፤፤ ባለፈው እኔም እንደሌሎች ላንዲት አፍታ ግልብ ሆኜ በትንሽ ብልቃጥ ትልቁ  የመርዝ ሳፋ ላይ የጠብታ ያህል  የተከለሰችን ጣፋጭ ማር ይዤ ብዙ ብዬ ነበር፤፤ሳተናዎችን ነገርዬው ከንክኖኝ አታውጡልኝም ብዬ ነበር ዘገየሁ እንጂ፤፤ መቼስ ምን ማር ቢበዛው የመርዝ ነገር ያስታውቃልንስ፤፤ ፈረሱና ፈረሰኛው አማለውኝ ነው ለነገሩ፡፤ አሃ ለካ የዛ ፀሃፊው እንኩዋ ግርማ ዳዲ ገቢሳ የሚባል የሸዋ ኦሮሞ ነበር፤፤ ይህ አሳሳች እኔንም አሳስቶኝ ነበር፤፤ ልክን እሱኑ መሰልከኝ ነው የምልህ፤፤ ተመልሼ እመጣለሁ ብሎ በዛው ጠፋብን፤፤ የሸዋ ኦሮሞ እንኩዋ ለቃሉ ይሞታል፤፤ ድንገት ካወከው ብዬ ነው፤፤ቅቅ
ወደፍሬ ጉዳይህ ስገባ፤ ሁለት ቦታ ሚስኮት አርገኅኛልና መልስ ይሻዋል፤
1) አባዊርቱ የዘር ፖለቲካው ትክክል ነው አላልኩም፤፤ 27 አመት አንድ ትውልድ የፈጠርንበት በዘር ፖለቲካ ሃቅ ነው፤፤ ምን ይገርምሃል እንጂ፤፤ ምንስ ጉድ ያስብላል እንጂ
2) አቢይ አህመድ የንግድ ባንኩን ገዢ አልቀጠረም ይሆናል  በየነ ገ/ መስቀል እንጂ፤ ነው ያልኩህ፤፤ አንተ ደሞ አቢይ  ጉዳዩን ያውቃልን ነው፤፤ አቢይ አይምሮ ውስጥ የዘለቀ ይመስላል ያንተውስ ምሁርነት፤፤
ዋናው  ማጠንጠኛህ አገሪቱ በኦሮሞ ልጆች ተወራለች፤፤ ያውም በወለጎችና አርሲዎች፤ ያውም በመስሊሞቹ፤ ሸዋ ጉድህ ፈላ፤ አማራውም ሞተሃል አንተ አያለህ? ምድር ቀውጢ ልትሆን ነው፤፤ እኔ ብዙ የማውቀው ጉዳይ አለ፤ ማን አማከረኝ እንጂ፤፤ ማንስ አዳመጠኝ እንጂ፤፤ እነዚህ ኦሮሞዎች እንኩዋንስ «የማይወዱትን» አገር የገዛ ልጆቻቸውንም ፤ ቤተሰባቸውንም እንጃልኝ፤፤ እስቲ ምን የሚሉት ነው አቢይ አውሮፕላኑን እያነሳ በየቦታው አለ ፕላን የሚበረው? ደሞ ፊልም አክተር ይመስል ወይ ድራማ ይሰራል፤ አንጋቾቹም ይደብራሉ፤ ይህን ሁሉ እያልከን ነው፤፤ እነመለስን ሰው እየናፈቀ ነው ድረስ፤፤  ምን ታረግ? 400 በላይ ሼር አርገንሃል፤፤ ያው እንደምትገምተው ግልቦች አይደለን?  ምን እንደደመደምኩ ታውቃለህ?
1) በአገር ፍቅር የነደደ ኢትዮጵያዊ መስለህኝ ወርቃማ ጊዜዬን ሰውቼ ያነበብኩህን ቀናት በፀፀት እራሴን መገምገሜን
2) ከባድ አቴንሺን ፈላጊ« ምሁር »  መሆንክን
በየማሳረጊያው የምትጠራው ልኡል እግዚአብሄር ወደ ህሊናህ ይመልስህ፤፤ አሜን፤፤
ግልባጭ፤ ለ ዶር አቢይ፤፤ እባክዎ ይህን በጎ አሳቢ ወገን በሆነ አዘእርት ሪሰርች ክፍል ቀላቅሉልንና ጊዜውን ለመልካም ነገር ያውልልና እኛም አንወናበድ፤፤
መልስ ለመሃድ አሊ፤፤ ያንተውንስ ይህን እየመለስኩ በቁም ነው ያየሁት፤፤ እንደው ይህም የሰርፀ አይነት ይመስላልና አንድ ላይ ልመልስልላችሁ ከሚል ነው፤፤ 
 
 
እንተም መክረህ ሞተሀል::
ሀ) ከ 1 – 3  ለተዘረዘረው መልሱ መስቲካ እያኘኩ መሮጥ ይቻላል:: 100 ሚሊዮን ህዝብ ያለበት ሀገር ብዙ ጉዳዮችን ጎን ለጎን ማራመድ ይቻላል multitasking ይሉታል ፈረንጆቹ፤፤ አቢይ አህመድ ደሞ ለየት ያለብህ ስለሆነ  ነው አግራሞት የጫረብህ፤፤
ለ) 4-5 ፕሮጄክቶቹን ለመፈፀም ታሳቢ የተደረገው ሰራተኛ ከአሜሪካ  ለማምጣት እይደለም:: ለኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ ስራ ይፈጥራልን ታስቦ እንጂ፤፤
የዱባይ ኢንቨስትመንት በተጨማሪ ሀገሪትዋን ቀውስ ውስጥ ያስገባትን የውጪ ምንዛሬ ይሸፍናል:: ህውሀት የዘረፈው ሀብት ሀገሪትዋን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ከቷልና:: እርዳታ የሚሆነው ትችት እየተቹም እኔ ብሆን ኖሮ እንዲህ አደርግን ቢታከልበት ነበር፤፤ አለበለዚያ እንደው ልፋትዎ ልፋት ሆኖ እንዳይቀር ከሚል ነው፤፤
ይድረስ ለተቺዎች በሙሉ፤፤
ስትተቹ  እኔ ብሆን እንዲህ እንዲህ አደርግ ነበር እያላችሁ ዋቢ ነገሮችን እያጣቀሳችሁ ብትፅፉ ከባድ እርዳታ ነው፤፤ አገር ይህን ትፈልጋለች፤፤ እነ የህውሃት ተውዘግዛጊ ድሮንን አያካትትም ይህ ጥሪዬ፤፤ እናንተማ በምን ትተዳደሩ? እውቀቱ ስለሌለ መብያችሁ ነውና፤፤

6 COMMENTS

 1. ይሄ ሠው ሰርፀ ደስታ እያለ የሚፅፈው ሠው ኦሮሞን ለመከፋፈል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም፡፡ ፅሑፎቹ በሙሉ በኦሮሞ ጉዳዮች የሚያጠነጥኑ ና የውሸት ታሪኮች በመተረክ የኦሮሞን ህዝብ ለመከፋፈል በእጅጉ የሚጥር ሰው ነው፡፡ ይሄን ያክል ጭፍን ጥላቻ ና የህዝብ ጠላትነት ግን የሚገርምና የሚያሳዝን ነው፡፡

  ያልገባው ነገር የኦሮሞ ህዝብ የደረሰበት የንቃተ ሂሊና እና አንድነት ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ሐይል ወደ ኋላ ሊመልሰው የማይችል መሆኑን ነው፡፡

  “የጠላህ ይጠላ “

 2. ስድብ ጥላቻና ትችት የተለያዩ ናቸው ፡ አባ ውሪቱ ከንቱዎችን አስተምርልኝ ፡ ፡አቦ ኑርልኝ…..ይመችህ

 3. አባዊርቱ የምትባለው ሰውዬ ለመሆኑ አንተን የአብይ ቃል አቀባይ ያደረገህ ማነው? አብይ ሰው አንጂ ኣምላክ መሰለህ አንዴ? ሰው ስለሆነ ሊሳሳት ይችላል። ስለዚህም ደግሞ አንዲታረም ከሰዎች ሂስን መቀበል ያስፈልገዋል።አንተ ግን ልክ አይምሮውን የሚያነብ ሰው ይመስል አንዲህ ስለሆነ አንዲያ ስለሆነ ነው ትለናለህ። ሹመት ፈልገህ ከሆነ ደግሞ ኣካባቢህ ካለው የጎሳ ፓርቲ ኣባል ሁን። ከወደዱህ ሹመት ይሰጡሃል። ለገሰ ዜናዊ በአንድ ወቅት አንዳለው ማንም ሰው የርሱን አፍራሽ አላማ የሚከተል ከሆነ አንደሚሾም ተናግሮ ነበር። አኛም ምስክር ነን። ስሙን በቅጥ የማይጽፍ ሁሉ ጄነራል ሲባል ፤ፓርላማ ገብቶ አጅ ሲያወጡ የሚያወጣ ሲያወርዱ የሚያወርድ የሰው ሮቦት ለማየት በቅተናል። አንተም ግባና ሞክረው። ኢትዮጵያ አንደሆን የማንም መጫወቻ ሆናለች።

 4. ይሄ ሠው ሰርፀ ደስታ እያለ የሚፅፈው ሠው ኦሮሞን ለመከፋፈል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም፡፡ ፅሑፎቹ በሙሉ በኦሮሞ ጉዳዮች የሚያጠነጥኑ ና የውሸት ታሪኮች በመተረክ የኦሮሞን ህዝብ ለመከፋፈል በእጅጉ የሚጥር ሰው ነው፡፡ ይሄን ያክል ጭፍን ጥላቻ ና የህዝብ ጠላትነት ግን የሚገርምና የሚያሳዝን ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ እንኳን አንድ ሰረፀ ሚሊዮኖች ቢቀባጥሩ የኦሮሞ ህዝብ ለነዚህ ወሬች ጆሮ የለውም፡፡ ልፋ ያለው… …ነው ነገሩ

  ያልገባው ነገር የኦሮሞ ህዝብ የደረሰበት የንቃተ ሂሊና እና አንድነት ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ሐይል ወደ ኋላ ሊመልሰው የማይችል መሆኑን ነው፡፡

  የፀረ ጥላቻ ህግ ፀድቆ ሲወጣ ይህን ሠው የኦሮሞ ህዝብ ሊፋረደው ይገባል፡፡

  ” የጠላህ ይጠላ “

 5. Comment:
  ጠ/ሚ የብሔራዊ ባንክ ሰብሳቢ ነው። የንግድ ባንክ ሰብሳቢ ማን እንደሆነ አገር ምድሩ ያውቃል። ስለ እሱ ምንም ሲባል አልሰማም። የንግድ ባንክ ውስጥ የብሔር ገመድ የመዘርጋት ስራ ካለ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለመጀመሪያ ጌዜ ሆን ተብሎ አገርን የማጥፋት ስራ እየተራ እንደሆነ ነው የምረዳው። ለምሳሌ አዋሽ ባንክ ባለፈት 25 አመታት ውስጥ ያከናወነው የባንኪንግ ኦፕሬሽን ለማንም ባንክ አርአያ የሚሆን መሆኑን ስለማውቅ ከዚያ ባንክ ፕሬዝዳንት ማምጣቱ አልጠላም። ሆኖም እንደ አንድ ተራ የባንክ ባለሞያ ፕሬዝደንቱ ለክልሎች ያከፋፈለውን 100 ሚሊዮን ብር አስመልክቶ ለጋዜጠኞች የሰጡት መግለጫ ብቻውን ኃላፊነት ቢኖረኝ በማግስቱ ከስራ አባራቸው ነበር። እንደ ሙያ እንጂ እንደ ፓለቲካ አይደለም የማወራው። ቃለ ምልልሳቸው በበጀት የሚተዳደሩት ጀነራል ወይም ኮነሌል እገሌን ይመስል ፍጹም አንባገነንነት የሚታይበት ነበር። ይህን ባንክ ኦፕሬሽን የህዝብ አመኔታ የሚሻ ንግድ በመሆኑ ትህትና እንጂ እንደ ጀነራል ምን ታመጣላችሁ የሚል ትእቢተኛን አይሻም። የባንክ ስራ በተቻለ መጠን አንድም ደንበኛ እንዳይቀየምህ ጥንቃቄ የምታደርግበት ሆኖ እያለ የአንድ ክልል ያውም የአጉሪቱ 30% ህዝብን የሚወክል ቅሬታን የፌስ ቡክ ጫጫታ ሰምተን አይደለም ብለህ የምትታበይበት አይደለም። ህዝብን ማቀልገል እሴቴ ነው ብሎ የቅሬጣ ሳጥን በየቅርንጫፉ አስቀምጦ የሚሰራ ባንክ አዎ ቅሬታችሀን ሰምቼ ነው ምላሽ የሰጠሁት ማለት ነው? ወይስ ከእናንተ ይበልጥ እኔ ቀድሞም አስቤያለሁ ማለት አገልጋይነቱን ይበልጥ የሚገልፅለት። ከሰርፀ ጋር ስለምትመላለሱት ሙሉ ክርክር አላውቅም። የንግድ ባንክ ሹመቶችን በተመለከተ ግን ጠቅላይ ሳይሆን ማንን እንደሚመለከት በደንብ ስለሚታወቅ እንዲህ አይነት የራሱን ወገን የማግለል ስራ ሲሰራ ዝም ይላል ብዬ አልገምትም። ሆኖም ግን ከባንክ የንግድ ባህሪ አንፃር እጅግ እጅግ የሚያሳፍር ፕሬዝደንት እንደ መረጡ ተረድቻለሁ። በርግጥ የሙያ ሰው እንደ መሆኑ ከእርሱ ይልቅ የህዝብ ግንኙነት ባለሜያን መጠቀም ሲችል እሱ ቀርቦ ያሳየው ባህሪ ግን በግሌ አስደንግጦኛል። ከአገሪቱ 37-40% ከሆነ ህዝብ የባንክ መሪ ለምን አየሁ የምል ግብዝ አይደለሁም። የምፈልገው የባንክ ስነልቦና የተላበሰ እንጂ እንዲህ ይቅርታ እንኳን ሊቀርፈው የማይችል ወታደራዊ አዛዥ የአገሪቱን ትልቅ ባንክ እንዲመራ አይደለም።

 6. ሰላም ለሁላችን ይሁን
  ለትውልድ ሃገራችን ዛሬ የሚያስፈልገን በቅንነት በመከባበር በመግባባት መወያየት ሲሆን ከዚህውጭ የተለየ ሃሳብ ያለውን በቡድን መኮነን ድሮ ሰሜን አሪሜካና አውሮፓ ላይ ሲተጉ ወደግራ ዘመም ፖለቲካ ሲያቀኑ የታላቆችን ምክር ባለምስማት ይህ ሁሉ የመስመር ልዩነት በሚል ትውልድ የተፈጀበትን ከዚያ የተረፍን ከአንድ ማህጸን ከወጣ ወንድም ጋር በተለያየ ጎራ የነበርን ምስክሮች ስላለን ክፉ ነውና ባንደግመው ይመረጣል::
  እዚህ በተነሳው ጉዳይም ሆነ በዶ/ር አብይ በጽንፈኛ ኦነጎች ጫና ሊታገዱና ለፍርድ መቅረብ የሚገባቸውን ባለሜንጫዎች ማቀፉ የከተማችን የራስ መብት ይከበር ባዮችን በብእር ብቻ የሚታገሉትን በረሃ ወስዶ ማሰር ማገድ የሁላችንም ጥያቄ ለመሆኑ ለዶ/ር አብይ ማሳሰቢያ የጻፉት ታላቆች ስጋታችንን ያንጸባርቀዋልና በጋራ ሆነን የተጀምረው ለውጥ በተሰጠው ተስፋ ይሄድ ዘንድ ትግላችንን በህሉም መንገድ መቀጥል ይኖርብናል:: ከዚህ በተረፈ አባዊርቱ ብዙ ልምድ ያለው የሃገራችን የቀድሞ ሰራዊት አባል ላላፉት ኣስራሁለት ኣመታት በሳይበር ሳውቀው የህዝባችንን ማደግ በጎነት የሚመገኝ መሆኑን መሰክራለሁ:: ሆኖም ግን የቀድሞው የወያኔ ተቺ ምሁራን ፕሮፌሰር አላማየሁን የመሰሉ ባጎበደዱበት መልክ ባይሆንም የዶር አብይን መንግስት ከመሰመር መውጣት ለማውገዝ ያለመቸኮሉን መብት ብንጠብቀለት በሃገራዊ ጉዳዮች ግን ሃሳቡን በሃሳብ እንድንሞግት ለማሰሳብ እወዳለሁ::
  ዲጎኔ ሞረቴው ከድብልቅ ኢትዮጲያዊያን ብዙሃኑ የህዝብ ማህበር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.