የአገር መከላከያ ሃይል ኢትዮጲያን ለማዳን ያለበት ቤሔራዊ  ሃላፊነት ና ግዴታ! (ከሙሉቀን ገበየሁ) 

ከሙሉቀን ገበየሁ  14 04 2019

የኢትዮጲያ ህዝብ በህወሃት(ወያኔ)  መራሹ  አስከፊ 27  አመታት አገዛዝ  ላይ ያደርገው መራራ ሰላምዊ ትግል ጫፍ ደርሶ ፍሬውን ለማየት ጭላንጭል  ተስፋ ማየት ጀምሮ ነበር። ባለፉት 3 አመታት ይህን የህዝብ ብሶትና ትግል መዳራሻውን ያዩ በገዥው ኢሕአዴግ ውስጥ በመካከልኛ የስልጣን ረክብ ያሉ በተለይም የ  OPDO  ና ANDM  “የለውጥ ፈላጊዎች”  ያደረጉት ስትራቴጂክ መተጋገዝና ውስጥ ለውስጥ የስልጣን ሽኩቻን ባሸናፊነት በመወጣት ህውሃትን ወደ መቀሌ  ገፍተው የፊትለፊቱን የስልጣን ወንበር ተቆጣጥረውታል።

‘Team Lemma ” ተብሎ የሚጠራውና በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አሕመድ ለህዝቡ የተደርጉ ተስፋ ሰጭ ፣ ሃገራዊ መልካም ንግግርና  ስልጣኑን እንደያዙ በወሰዷቸው የለወጥ እርምጃዎች አብዛኛው የኢትዮጲያ ህዝብ  አገራችን በሰላማዊ መንግድ ወደ ዲሞክራቲክ የፖለቲካ አስተዳድር ትሸጋግራልች በማለት ትልቅ አዲስ ተስፋ ኧደርገ። ብዙኋን ወገኖችም የዘውተር ጸሎታችን ደረሰለን አሉ። ወጣቶችም በአገርችን የወያኔን አስተዳድር የሚያፈርስ አብዮት ሆነ ብልው አሰቡ። አንዳንዶች ለውጥ ሳይሆን  ኢሕአዴግ ስልጣኑን ለመራዘም የሄደባቸው ጥገናዊ መሻሻል ስልጣኑን ከወያኔዎች ወደ የኦሮሞ ብሄር አቀንቃኞች ሽግግር አድርገው ወሰዱት።

የህዝቡ ታላቅ ተስፋና ደስታ ግን ከትንሽ ወራት አላለፈም። አዲሶቹ መሪዎች የወያኔውን ሓጢያት የነበርውን  ከማጋለጥና አንዳድን እርምጃ ከመውሰድ ውጪ የወደፊቷን ተስፋ የሚጣልባትን ሃገር የምተመሰረትበትን ንድፍ ወይም ስራ ግን አልሞከሩም። አስክፊውን የወያኔ መራሹን አገዛዝ የበሰበስ ቁስል  ሽቶ በተነከረ ጨርቅ ሸፈኑት እንጂ ወይ ቆርጠው አልጣሉት ወይም መልካም ህከምና አላድርጉለትም። ለህዝባችን 27  አመታት ያሰቃየውን  የከፋፍለህ ግዛው አገዛዝ  መሰራታዊ መንሴ ወይም መርዝ ግን መዝመዘው አላወጡትም።

ይህ የበሰበሰ የወያኔው አገዛዝ  ቁስል በተለይም ባሁኑ ወቅት በዘር ፖለቲካ አርማጆችና አክቲቭስቶች  የሆኑ  ባክቴርያና ቫይርስ ( bacteria and virus) ክፉኛ ተወሯል። ቁስሉም  እያመንዠ መጥፎ ጠረን ያለው መግል ይተፋል። በዚህም ሳብያ  ከ 4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጲያውያን ወግኖቻችን ተፈናቅለዋል፣ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ሞተዋል ንብረት ጠፍቷል እንዲሁም መላው የአገራችን ህዝብ  ወደፊት የርስ በርስ ጦረነት ልንገባ ነው በሚል ፍርሃት ተውጧል። ይህ በአገራችን በየቦታው የተከሰተው የጎሳ ግጭትና መፈናቀል መንሴው ባለፉት 27 አመታት  የተገንባው የዘር ጥላቻና  የጎሳ ፖለቲካ  መሰርቱን  ለማምከን፣ ህዝቡንም ላማሳውቅ፣ ለማንሳሳትና መፍቴው አካል እንዲሆን ስላላደርጉት በከፊል ሃላፊነቱን የሚወስዱት እነዚህ “የለውጥ መሪዎች” ናቸው።

ወያኔ የቀበርውን መርዝ ለማምከንና መንጎ ለማውጣት ቁርጥ የሆነ  እርምጃ ካልተወሰደ  አሁን ባለው አካሄድ ግን መፍቴህ ስለማይኖር መርዙ ለብዙ ግዜ ይቆያል። ምንም እንኳ አዲሶቹ መሪዎች ላይ ላዩን  ለ ፖለቲካ ኢሊት መደቡ የሚያረካ  የጥገና ለውጥ እርምጃ የወሰዱ ቢሆንም  በተለየም እንደ መንግስት ሃላፊነት ተሰምቷቸው መውስድ የነበረባቸውን ፅኑ እርምጃ ዘንግተው ወይም  በድብቅ የሚያራምዱት ሴራ ያተርፉት በሃገራችን በተለይ ሁኔታ አስከፊ የዘርና የጎሳ ፖለቲካ አጀንዳነት የሚተፋው የሚሊዮኖች መፍናቀልና በሺዎች ማለቅ ስቃይና ፍራህትን  ነው። በተለይም የጎሰኞች ድርጅቶችን ከነሰራዊታቸው የጦር መሳራያቸውን ሳያስረክቡ አገር ቤት ያለጠያቂና ከልካይ እንዲገቡ በመፍቀዳቸውና የነዚህን ድርጅቶች ሚዲያ ጥላቻን የሃስት  እና ህዝብ ለህዝብ የሚያጋጩ ፕሮፕጋንዳን በዋና ከተማ ላይ ተቀምጠው እንዲያከናውኑ  መሪዎቹ የፈጸሙት ስህተት ወይም የሃገር ና የህዝብ ክህደት አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ጭንቅ ላይ ጥሎታል። በነዚሁ ከልካይ በሌላቸው አክራሪ ዘርኞች፣ የጥላቻ መስፎኖች ሰራዊታቸውን በድሃው ህዝብ ላይ ያደርሱት ወደር የሌለው መፈናቀል  ባስከፊው የወያኔ ህወሃት  27 አምታት አገዛዝ እንኳ አልተፍጸመም።

ኧዲሶቹ መሪዎች የወያኔውን  ሓጢያት፣ ቆሻሻ ከማጋለጥና አንዳንድ ቀዳዶችን ከመሸፋፈን ውጪ አገራችንን ወደ ፊት በሰላማዊ መንገድ የሚመራት የስራ ንድፍ  የላቸውም። በዚህም ምክናያት ህዝቡን መክራ ላይ በመጣላቸው እንደ መሪ ከሽፈዋል የኢትዮጲያንም ህዝብ  እንደመንግስት ለመምራት ፈተናውን ወድቀዋል። የለውጡን ማግስት ተከትለው ህዝብ የሰጣቸውን ድጋፍ ይዘው መድረግ የነበርበትን ዋና ጉዳይ ረስተውታል። ለ 44  አመታት ያህል   በወያኔው 27   በ ደርግ 17  አመታት የተሰቃየውን ህዝብ ና በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ እልቂትን ያስከተለውን ጥፋት በመመርመር በህዝቡ ዘንድ ያደረውን የሃዘንና ቂም ጥቁር ስሜት ለመፍታት ቤሄራዊ የእርቅ፣ የይቅርታና የህዝብ ለህዝብ ና የፖልቲካ ድርጅቲች መግባባት  ስራ በፍጹም አልተሰራም። ይህ በወቅቱ ቢደርግ ኖሮ ህዝቡም ለ 44  አመታት ያመሰውን ሃጢያት ሴራ መንግሎ ለይቶ በመነጋገር በይቅርታና በተገቢ ፍርድ ያለፈውን የሰቆቃ ምእራፍ በማያዳግም መልክ ዘግቶ የወደፊቱዋን ሀገራችንና የመንግስት አስተዳደር ለማምጣት የሚደርገውን የሽግግር ግዜ ቀላል ያደርገው ነበር። ይህ ባለ መድርጉ ከስልጣን የተገፉት እንዲይንሰራሩ፣ እንዲደራጁና  ሌሎች አዲስ አሰቃዮች ደግሞ ያለፈውን እያነሱ የወደፊቱን ባሮጌው እየቃኙ የሚመሩበትን የተንኮል ፖለቲካ እንደ ልባቸው ህዝቡ ላይ እንዲጭኑ ተመቻችቶላቸው የኢትዮጲያ ህዝብ የሚገባዋን የፖለቲካ ሽግግር እንዳያግኝ ባሁኑ ወቅት ሆኗል።

ባሁኑ ወቅት አስፈሪው ነግር የዲሞክራቲክ ፖለቲካዊ ለውጥ አልመጣም ሳይሆን ኢትዮጲያ እንደ ሃገር የመበታተንና የእርስ በርስ ግጭት ፈትና አደጋ ውስጥ የመግባት እድሏ ነው። ታዋቂ ሙሁራንና የፖለቲካ ተንታኞች ሀገራችን የመብታተን አደጋ እድል የገጥማት መሆኗንና ያሉትም መሪዎች እንደ መንግስት የከሸፈ መንግስት (Failed state) እንደሆነ ይመስክራሉ።

ኢትዮጲያውያንን ለ 28 አመታት ሲያውካቸውና ሲያፈንቅላቸው ያለው መሰረታዊ መንሴ የዘር የጎሳ ፖለቲካ ነው። የጎሳ ፖለቲካ በ ህገ መንግስቱ ሰፍሯል። ይህ ችግር ያለብት ሀገ-መንግስት ዋናው ተልኮ የህውሃትን ከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ  አገዛዘን  ህጋዊ  ለማዳርግ የተቀመጠ የመንግስት ህግ ነው። እሱን ተመስርቶ የተተከለው በጎሳ ላይ የተመሰረተ የሃስት ፊዴራላዊ አስተዳድር  ወያኔው ለግጭት እንዲያመች ባሰመረው ወሰን   ተንተርሶ፤ በጎሳ  ፖለቲካ የተጠመቁትን ወገኖችና ተከታዮቻቸውን አውሮ፣ ህዝብ ለህዝብ እንዲጋጭና  “ይሄ የኔ ነው የአንተ አይደለም'” ወድሚለው አስትሳስብ ና እምነት አስድሮ ብሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖችን እንዲፈናቃሉ አድርጓል። በተለይ ይህን አደግኛ መርዝ  በተጋነነ ና በሃስት ያለፈ ግዜ ታሪክ ትንታኔና ፕሮፓጋንዳ  እንዲሁም “አሁን ተራው የኛ ነው” የሚል አስተሳስብ ተጨምሮበት አገራችንን ወደ ገደል አፋፍ አድርሰዋታል።

ይህን ታልቅ አደጋ ከማንኛውም ጎሳ የምንወለድ ወገኖች፣ ባለሞያዎች፣ የእምንት ተከታዮች፣ የተለያየ ፖለቲካ አምለካከት ያለን ሰዎች፣  ጾታና እድሜ  ያለን ሰዎች፣ በተለይ ወጣቶች  የትንዣብበውን አገር የመፈርስ አደጋ ጊዜ ሳንወስድ ሳይመሽብን  ማወቅና፣ በመከታታል፣ በመተባበር ማክሸፍ አለብን። አንዴ ከተፈርካክስንና የእርስ በርስ ጦረነት ውስጥ ከገባን ማብርያ ወደሌለው እልቂት እንግባና ራስችንንም ልጆቻችንም  በቀድሞዋ ዩጎስላቪያ፣ ሶምሊያ፣ሩዋንዳ፣ የመን እና በበርማ (Mynamer) ያሉ የሮሁንጊያ (Rohingya) ሰዎች እጣ ተካፋይ እንሆናለን።

በሚያሳዝን ሁኔታ ለ 28  አመታት ህወሃት መራሹ መንግስት  የዜግነት ፖለቲካ የሚያቀነቅኑ ድርጅቶችን፣መሪዎችን ና ተከታዮችን እያሳደደ ሲውቅጥ፣ ሲርገጥ፣ሲያስር፣ ሲገል በመኖሩ  በኢትዮጵያዊነት የዜግነት ፖለቲካ አስተሳሰብና መደራጀት እጅግ የተመታ ከመሆኑም አልፎ አሁን እንኳ ለውጥ መጣ ከትባለ ቦኋላም እንዲደክምና እንዲክፋፈል ተደርጎ የሚነክሱበት ጥርስ፣ የሚናገሩበት ምላስ እንዳይኖራቸው ተደርጓል።  ሃገራችን የጎሳ ፖለቲካን የሚያቀነቅኑ አገዛዙም ላይ ባሉና በተቃውሞ ጎራ ያሉት ሁሉ  የመስፍንነት ቦታቸውን ይዘዋል። የህዝቡ ዋና ፍላጎት በሰላም፣ በፍትህ ሁሉም ሰው ዜጎች ሁሉ  እኩል እድል የሚያገኙበትን ወንድምና እሁትማማቾች  የሚሆኑበትን  የመንግሰት ስርአት  ነው።

የጎሳ ፖለቲካ በተፈጥሮው ጸረ-ዲሞክራቲክ ነው። የተመሰርተው በልዩነትና ሌሎችን በማግለል ወይም ጥላቻ ነው። ይህን እንደገና ባገራችን ማራመድ ለሌላ ጥፋት ማዘጋጀት ነው።  በኢትዮጲያ ያሉ ጎሳ  ሁሉ ቋንቋቸው፣ ባሃላቸውና  ልምዳቸው  አገር ይበልጥ ለማሳድግ በሚጠቅም መልኩ ነው እንጂ መያዝ ና መደራጅት ያለበት የልዩነት መሰርት ሆኖ የጎሳ ፖለቲካ ማራመጃ መሆን አለንበረበትም።

ባሁኑ ወቅት  በጎሳ ላይ ያለተመርኮዘ ብቸኛው የመንግስት ወዋቀር የአገር መከላከያ ሃይል ነው። ምንም እንኳ በወያኔው ዘመን  የከፍተኛ አመራሩን የያዙት የቀድሞ ወያኔዎች ቢሆኑም በተለይም ከኮሎኔል ማእርግ በታች ያሉት ወታደሮች ግን ከየትኛውም ኢትዮጲያ ክፈልና ጎሳ የተወጣጡ በኢትዮጲያውነታቸው  የአገር መከላኪያ  የሆኑ፣ የሰለጠኑ ወታደሮች ናቸው። ያገር መከላከያ ሀይል አገራችንን ከውጭና ከውስጥ ከፍተኛ አደጋ የሚከላከልና የኢትዮጲያን  ህልውና የሚጠብቅ  ነው። አገራችን አሁን የተደቀነባትን የመበታተን አደጋ  ለመምከትና ለማስቀረት ያገር መከላከያ ሀይል ወታድሮች ከፍትኛ ቤሄራዊ ሃላፊነትና ግዴታ አለባቸው። ባሁኑ ወቅት አገራችን  በጎሳ ፖለቲካ ባበዱ ዘርኞች እይተናወጠች ያለችበት ሰአት ሲሆን ያለው መንግስትም የደከምና ተገቢውን የፖለቲካ ሽግግር ለማደርግ የተሳነው ወቅት ላይ ነን።

ጠቅላይ ሚንስቴር  ዶ/ር አብይ አህመድ የአገር አንድነትን፣ ዲሞክራሲ ምርጫ እንድሚደርግ ተስፋ የተሞላ  ደጋግመው ዲስኩር ቢያድርጉም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከዚህ የተለየ ነው። የሚናግሩትን ወደ ተግባር ለመለውጥ የተሳናቸውን ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም፤ ነገር ግን 27  አመታት የገዛው የ ኢሕአዼግ የፖለቲካ መዋቅር እስክታች ድርስ የተዘርጋው  ቆልፎ ይዞ እጃቸውን እይጠመዘዘ ሊያሰራቸው አለቻሉም፤ ወይም  አሁን የሚመሩት የጎሳ ድርጅታቸው ኦድፒ (ODP)  በአክራሪ ዘረኞችና በኦነግ ፖለቲካ አራማጆች ውስጥ ውስጡን ተቦርቡሮ  ስልጣናቸውን እይተቀናቀናቸው ሊያሰራቸው አልቻለም፤ ወይም  በሶሻል ሚዲያ ና አሁን ደግሞ በግልጽ መደበኛ ሚዲያ ይዘው  ወጣቱን “ቄሮ” የሚባለውን አመራሩ ስውር የሆነውን ሃይል  ይዘው ዘረኘነትን፣ ጎሰኘነተን፣ አገር መክፋፈልንና ማምሰን የተያያዙትን አክቲቪሶቶችና ጎስኞችን ፈርተው መራመድ አልቻሉም፤ ወይም ምንም እንኳ ብዙ ሰው በዚያ መልክ ባይገምታቸውም የተደበቀ አጀንዳ አላቸው። ብዙ ሀዝብ ግን የሰጡትን ሀገራዊ የቃል-ምኞት  አምኖ እንዲስካልቸው ትልቅ ተስፋ አድርጎባቸዋል። እርግጠኛውን ማወቅ አለተቻላም። እሳቸውም አልተናገሩም።

የተደቀነው እልቂት  ለመቅረፍ ያለው አማራጭ ሁለት ነው። ዶ/ር አብይ አሕመድን   ሙሉ ስልጣን ኖሮቸው ከነ ሙሉ ሃላፊነትቸው የተጀምረውን የሽግግር እርምጃ በሃቅ ላይ ተመስረተው ሌሎች የለውጥ ሃይሎችን ተቃዋሚ የነበሩትን ሁሉ ያካተተ ሽግግር መንግስት በመምራት አገራችንን እንዲያድኑ የመከላኪያው ሃይል  ሙሉ ድጋፉን መስጠትና ከጎናቸው ተሰልፎ ለውጡን ተግባራዊ ማደረግ፤

ወይም የመከላከያ ሀይሉ የመንግስት ስልጣንን ለተወሰነ አጭር ግዜ ወስዶ ለ 28  አመታት የረበሸነንና አሁንም ጥፋት ለሆነው ዋና መንሴ  ከስር መሰረቱ መንግለው  ካወጡ ቦኋላ በሃቅ ለተመርጠ የህዝብ መንግስት ማስረከብ ነው።

በተለያዩ የአለም አገራት የቤሄራዊ መከላኪያ ሃይል እርምጃ በመውስድ አገሮች ከመፍርስና ከመበታተን እንዳዳኑ  የሚታወቅ ሲሆን  በሌላም በኩል የ ወታደራዊ አምባገነን ለመመስረትም የሚደርገ የመንግስት ግልበጣዎችም አንዳሉ እናውቃለን።  ይህንንም  አወቀን  ልምዱን መማርና ተግባር ላይ ማዋል ይገባል። አገራችን አሁን ያልቸበት  ግን አገር የሚበታትንና የሚያጠፋ አደጋ እጣ ፈንታ ሁኔታ ላይ ነን።

በመጀምረያ ደርጃ  የአገር መከላከያ ሃይል ዶ/ር አብይን  ሙሉ ስልጣን ኖሮቸው ሌሎችንም ይዘው ሽግግሩን እንዲመሩ ሙሉ ድጋፍ እንዲሰጣቸውና የኢሕአዴግን ስርአት መዋቅር እንዲያፈራርሱና የከፋፈልህ ግዛው መሰረትን፣ የዘር ፖለቲካን በህግ ማስቆም፣ የወያኔውን ህግ-መንግስት እንዲያፈርሱና ባዲስ ህገ-መንግስት ህዝብ የተሳተፈበትን እንዲያጸድቅ፤ በዘር ና ጎሳ መደራጀትን በህግ መከልከል፣  የሚያደርገውን እውነትኛ የሽግግር እርምጃ እንዲወስዱ ማስደርግ ሲሆን ፤  ሌለው  ሁለተኛው አምራጭ ግን፤

ሁለተኛው አምራጭ ዶ/ር አብይ አሕመድ  ይህን ለማከናውን ዝግጅቱና ፍላጎቱ ከሌላቸው፣ የአገር መከላከያ ሀይል ከ 1-2  አመታት ግዜ በጊዜያዊነት የመንግስት ስልጣን ይዞ አገራችንን ከመበታተን አደጋ የሚያድናትን እርምጃ በመውሰድ በልዩነትን፣ በዘርኝነት እየደረሰ ያለውን መፈናቀል፣ ግድያ የንብርት ጥፋት የዳረገንን የዘር ፖለቲካ መንሴና ወዋቅር መንግሎ እንዲበጣጥሰውና በህዝብ ለተመርጠ መንግስት ስልጣኑን ማስረከብ ይሆናል።  ምንም እንኳ ይህ ለሌላ ወታደርዊ አምባገነን ላይ ሊጥል የሚችል አደጋ ቢኖርበትም  የቆምንበትን የምነኖርበትን አገርን ለማቆየት ግን ይርዳል።

አገራችንና ህዝቧን እንድናድን፤  የሰላምና፣የአንድነት፣ የፍትህ ና የፍቅር ሀገር እንድትሆን አምላክ ይርዳን።

1 COMMENT

  1. ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ጥሩ አማራጭ አይደለም:: ዴሞክራሲ በሌለበት አገር ሥልጣን ይዞ በሰላም የለቀቀ ማንን አይታችኋል? የአገራችን መከላከያ ወጥ ያለው አይደለም፤ በዘር ኮታ የተዋቀረ ነው:: ገለልተኛ ሆኖ መቀጠሉ ይበጃል:: እንደእኔ ቢከፋም ቢለማም ገዢው ፓርቲ ከእርስ በርስ ሽኩቻና መጠላለፍ ተላቆ በጋራ መፈናቀልን ለማስቆምና የዴሞክራሲ ግንባታ እቅድ አውጥቶ ስብሰባውን በሰላም ቢጨርስ ይበጃል:: አሁን ያለው መንግሥት መምራት አልቻለም የሚሉት አባባሎች ሙሉ ለሙሉ ከቅንነት የመነጩ ናቸው ማለት ያስቸግራል:: የአገራችን ፖለቲከኞች ሥልጣን ኮርቻ ላይ ለመውጣት ሲሉ እርስ በርስ መበላላት ልማዳቸው ነውና ሕዝብ ወይ በትክክል ምሩ ወይ ራሳችሁን በጡረታ አግሉ ብሎ በጋራ ወጥቶ ቢጠይቅ ይሻላል:: አትርሱ:- አገራችን ውስጥ ብዙ የጦር መሳሪያና እያዳንዱ ክልል ልዩ ኃይልና ሚልሺያ ያለባት ናት::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.