ዛሬ VOA ላይ የሰማዋትን መርዝ ንግግር ለጋራችሁ፦(አያሌው መንበረ)

የኦሮሚያ ክልል ፀጥታና ደህንነት ቢሮ ም/ሀላፊ ከአማራ ክልል አቻው ጋር በሰሞኑ በከሚሴና ሸዋ ጉዳይ “የአድማጭ ጥያቄ” እየመለሱ ነበር።

አንድ አድማጭ/ጠያቂ እንዲህ አለ፦

“ኦዴፓ ኦነግን እየተንከባከበው ነው፣ትጥቅ ፈቷል የተባለው ድርጅት ከየት እንዳመጣው በማይታወቅ መልኩ ዘምናዊ መሳሪያ ታጥቋል፣ባንክ ይዘርፋል፣ሰው ገድሎ ያቃጥላል…ወዘተ።ይህም የሚያሳየው ኦዴፓ አመራሮች ኦነግን ወይ ትጥቅ ሳይፈታ ነው ያስገቡት (ድርድሩ ላይ እነርሱ ብቻ ስለነበሩ የድርድሩ ሂደት አይታወቅም) ወይም አመራሩ ራሱ የኦነግ ደጋፊ ስለሆነ ነው ፍላጎቱ ነው ማለት ነው።ድርድሩ ላይም የፌደራል መንግስት መሳተፍ ነበረበት” የሚል ሀሳብ ይሰነዝራል።

የኦሮሚያ ፀጥታም ኦነግን የኦሮሞ ህዝብ ጠላት መሆኑን ጭምር ከገለፀ በኋላ (ይህ አቋም ድርጅታዊ ከሆነ ጥሩ ነው) “የታጠቁ ሀይሎች ሲገቡና በድርድሩ ወቅት ወደየ ክልላቸው ነው የገቡት።በዚህ መሰረት ኦነግም ኦሮሚያ፣ደህሚትም ትግራይ ነው የሄዱት፣#ግንቦት_ሰባትም_አማራ ክልል ነው የሄደው እንጅ አዲስ አበባ አልመጣም” ብሎ ቁጭ አለ።

ይህ የአንድ ክልል ቢሮ ሀላፊ ግንቦት ሰባት የአማራ ክልል ፓርቲ አድርጎ እየነገረን መሆኑ ነው።በጣም ነው የደነገጥኩት።ኦዴፓ “የዜግነት አቀንቃኝ ነኝ የሚለውን (እርግጥ ስላልሆነ እኛም አንወደውም) ግንቦት ሰባትን የአማራ ፓርቲ ነው” ብሎ አቋም ይዟል ማለት ነው።ያለዚያማ አዲስ አበባ ሳይሆን አማራ ክልል ላለው እንዲቀር የተደረገው አይለንም ነበር።ይህ አካሄድ ድሮ ህወሃት ብአዴንን ለመክሰስ “የብአዴን አመራር አንዳንዱ የግንቦት ሰባት ነው” ትለው የነበረው በኦዴፓ ቤትም አቋም ተያዘበት ማለት ነው።እዚህ ጋር ግንቦት ሰባት ለሚባል የነጋዴዎች ስብስብ እየተከላከልኩ ሳይሆን ኦዴፓ እየሄደበት ያለው መንገድ ምን ያህል ገራሚ እንደሆነ ለመጠቆም ነው።
በዚህ ላይ ሆነን ስንሰገመግመው የአርበኞች ግንባር ወታደሮች ወረታ ታጉረው የቀሩትና ወደአዲስ አበባ እንዳይመጡ፣ማዕከላዊ መንግስቱም እንዳይደግፋቸው የተደሩጉት “ግንቦት ሰባት የአማራ ፓርቲ ነው” የሚል አቋም በእነ አብይና ለማ ስለተያዘ ነው ማለት ነው።

ጋዜጠኛዋም ይህንን ዝም ብላ ሳትጠይቅ ማለፏ ገርሞኛል።

ለማንኛውም ኮሎኔል አለበል አማረ በጣም በግሩም ሁኔታ በቁጥብ አገላለፅና በበሰለ አተያይ ውይይቱን ተወጥቶታል።

3 COMMENTS

 1. ታዲያ ምን ይገርማል፣ በግንቦት_ሰባት ስም የትጥቅ ትግል ዉስጥ የነበሩት ተዋጊዎች ባብላጫው ከአማራ ክልል (ጎንደር) የወጡ ናቸው እኮ! ይህችን ሰንካላ ምክንያት እንኩዋ ለፖለቲካ ንግድ!??

 2. ” ዛሬ VOA ላይ የሰማዋትን መርዝ ንግግር ለጋራችሁ፦(አያሌው መንበረ) ”

  WARNING !

  VOA is mouthpiece of the USA government/CIA !

  * የኦሮሚያ ፀጥታም ኦነግን የኦሮሞ ህዝብ ጠላት መሆኑን ጭምር ከገለፀ በኋላ (ይህ አቋም ድርጅታዊ ከሆነ ጥሩ ነው) “የታጠቁ ሀይሎች ሲገቡና በድርድሩ ወቅት ወደየ ክልላቸው ነው የገቡት።በዚህ መሰረት ኦነግም ኦሮሚያ፣ደህሚትም ትግራይ ነው የሄዱት፣#ግንቦት_ሰባትም_አማራ ክልል ነው የሄደው እንጅ አዲስ አበባ አልመጣም” ብሎ ቁጭ አለ።

  Well, that is rather funny. G7 is a Pan-Ethiopian group, like Andinet, Meiad and Semayawi.

  But TPLF used to call G7 an Amara group. It seems, tribalist ODP shares also that view of TPLF. That exposes that ODP is too tribalist to be allowed to lead or be member of an Ethiopian government. ODP tribalists have first to be put in re-education camps and be decontaminated from their tribalism poison before being allowed to rule the country.

  I think, beside G7, TPLF called all other Pan-Ethiopian groups, including those mentioned above, Amara. That could be explained by the TPLF fear that its tribalist system wouldn’t survive if it recognizes Pan-Ethiopian groups. TPLF is not willing to accept Pan-Ethiopian groups. That the ODP also behaves the same way is another reason why it has to leave the government, since ODP and Abiy gained Ethiopians’ support because they preached Ethiopiawinet. This ODP behaviour is yet another proof that Abiy and his ODP lied to Ethiopians.

  And why did G7 simply accept the tribe label ?
  Why didn’t it protest ?

  This situation is one more reason to demand the immediate resignation of the Abiy government and his ODP and the immediate installation of a transitional government of patriotic Ethiopians to save the ancient African country from disintegration.

 3. ከኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ
  ጋዜጠኛዋ በሚገርም ሁኔታ ለአበበ ገረሱ የተጠየቀውን ጥያቄ ብዙ ዝባዝንኬ ለሚያወራው አለበል አማረን እንዲመልሰው አሳልፋ መስጠትዋ የሚገርም ነው። አለበል አማረ ከእውነታው ውጭ የሚዋዥቅ ስለሆነ ንግግሩ ሁሉ ማቆሚያ የሌለው በፍሬ ከርስቺ የተሞላ ስለሆነ ሌላ የአማራ የጸጥታ ሰው ቢቀርብ ኖሮ የተለየ ክርክር እናደምጥ ነበር። አበበ ገረሱም ሆነ አለበል ሁለቱም ለዚህ ቦታ የሚመጥኑ ስላልሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢደምጡ የተሻለ ነበር። ወይ አገሬ!
  የኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.