ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የውጭ ሀገራት ገንዘብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በቶጎ ጫሌ የጉምሩክ ጣቢያ አንድ መቶ 80 ሺ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የ3 ሀገራት ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር የዋለው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ ሲመነዘር ከ8 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፍተሻ ጣቢያው ገንዘቡ የተያዘው አብዱርሃማን ቃሲም አደን እና አብዱልቃድር አብዱላሂ አናን ከተባሉ ተጠርጣሪዎች ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከያዙት ገንዘብ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ትላንት በተሽከርካሪ ላይ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

በዚህም ወቅት ተጠርጣሪዎቹ 182 ሺህ 247 የአሜሪካን ዶላር፣ 110 ሺህ 920 የዩናይትድ አረብ ኢሚሬት ገንዘብ እና 235 ሺህ 375 የሳኡዲ ሪያድ በእጃቸው ይዘው እንደነበር ተገጿል፡፡

ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር

1 COMMENT

  1. አይ ሃገር ትላንትም ዝርፊያ አሁንም ዝርፊያ። ዛሬም ሰውን ማፈናቀልና ኡኡታ የበዛባት ሃገር እነ ሰለሞን ደሬሳ፤ እነ ጸጋዬ ገ/መድህንን የመሳሰሉት አርቆ አሳቢዎች ባፈራቸው ሃገር ዛሬ በዘር ላይ የተሰለፈ ዓለም አቀፋዊ እይታ የሌለው መጽሃፍትን ሳይሆን ቆንጨራና ማስማርን በጣውላ ላይ የመታ ስብስብ ሰው የሚያምስበት ምድር። በሰላም ስም የገባውና በጅምላ ስሙ ኦነግ ተብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ህዝቦች ነጻ አውጪ (በውስጡ ከ7 ባላይ የሆነ ክፍፍል ያለበት ድርጅት) ባንክ ሲዘርፍ፤ ሰው ሲገድል፤ ምድሪቱን በእሳት ሲለኩስ የሚታየው የራሱ መኖር እንጂ ለህዝባችን ትላንትም ዛሬም አያስብም። እንደ በቀለ ገርባ ያሉ ጠባብ ብሄርተኞች አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠው ስለ ዲሲ የመሬት ስሬት ላይስተምሩን ይቃጣሉ። በአንዲት ሃገር አምኖ በተጠቃለለ መልኩ ለህዝባችን ትሩፋትና ሰላም መስራት ለዘረኞች አይዋጥላቸውም። የሚያስቡትና በጎጣቸው፤ የሚተነፍሱት በተውሶ ሳምባ በመሆኑ እርቆ መሄድና መመልከት አይቻላቸውም።
    እውቁ ገጣሚና የመድረክ ሰው በሃይሉ ገ/እግዚአብሄር በቅርቡ ባቀረበው “አዲስ ባሬስታ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ” የመድረክ መጣጥፍ ዋዛና ቀልድን ታኮ ያቀረበው የዛሬዋን የሃገራችን ጉድ በጠራ መንገድ አቅርቦታል። ዪ.. ቱቭ ላይ ፈልጎ ማዳመጥ ነው። ከዚህ ባሻገር በትግራይ ለምን መንገድ ለማጽዳት ወጣቹሁ ተብለው የተደበደቡና ታፍሰው እስር ቤት የገቡ ወገኖቻችን የሚያመላክተው የወያኔን ጽልመት ነው። ወያኔን ምንም የሚቀይረው ነገር የለም። ለምን ጠ/ሚሩ በጠራው የጽዳት ዘመቻ ላይ ለምን ወጣችሁ ተብለው በወያኔ ጄሌዎችና ወታደሮች ድላና ሰደፍ የተወገሩትና ለእስር የተዳረጉት ወገኖቼ ዛሬም በአፈና ውስጥ እንዳሉ ያመለክታል። ለአንድ የስናይፕር ጠበንጃ አስታጥቆ ሌላው ለመከላከያ የሚያርስበትን በሬ እየሽጠ ትጥቅ ለመታጠቅ ሲሻ ሃገሪቱ በጦር መሳሪያ ግዢ ተጥለቀለቀች ይሉናል። አምታች ፓለቲካ። አንድ ተሰዳጅና ተገዳይ ሌላው ገዳይ የሆነበት። ታዲያ እንዲህ አስረሽ ምቺው ላይ ባለች ሃገር ሰው ያለውን ከሃገር ሊያስወጣ ቢሞክር ይፈረዳል፡፡ ለዛውም የተመዘበረ ሃብት፡፡ ሃገሪቱን ባህርማዶ ለማሻገር ያልሞከሩትም ግኡዝና የማትንቀሳቀስ ሆናባቸውን ነው፡፡ በሃገር ውስጥ ግን ምድሪቱን ለባለሃበት እየተባለ መቸብቸቧ የት ቀረና!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.