ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢቫንካ ትራምፕን አነጋገሩ


ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የምትገኘውን የአሜሪካውን ፕሬዝደንት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ውይይታቸውም የሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም ላይ እስከ 2025 ድረስ 50 ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢኒሽየቲቭ ይፋ ማድረጋቸውን አስታውሳለች ፡፡

ይህ ባለፈው የካቲት ይፋ የተደረገው ፕሮግራም በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር ኢቫንካ ትራምፕ ገልፃለች ፡፡

የሴቶችን አቅም ማጎልበት፤ የሴቶችን የሥራ ፈጣሪነት እድል ማስፋትና ለሴቶች አጋዥ የሆኑ ህጎችና ደንቦችን ማጠናከር የሚሉት የፕሮግራሙ ማጠንጠኛዎች እንደሆኑ ነው በማብራሪያዋ ያመለከተችው፡፡

ከዚህም አንጻር በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚከናወኑ ተግባራት የሚደነቁ መሆኑን የጠቀሰችው ኢቫንካ ትራምፕ ይህን ሂደትም አሜሪካ በተለያየ መንገድ እንደምትደግፈው ተናግራለች፡፡

ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የተያያዘችውን የለውጥ ሂደትም አድንቃለች፡፡

በፕሬዝደንት ትራምፕ የተቀረጸውና በአለም ላይ ያሉ ሴቶችን ለመደገፍ ያለመው ኢንሽየቲቭ ጥሩ እርምጃ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ፕሮግራሙ ሴቶችን ማዕከል እስካደረገና ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያሸጋግር እስከሆነ ድረስ ተቀባይነት የሚኖረው ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሴቶችን አቅም ለማጎልበት በአዲስና በተለየ የለውጥ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም ሴቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከገቡ በኋላ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በመፍታት ትምህርታቸውን በስኬት ጨርሰው እንዲወጡ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት መደረጉን ነው ያብራሩት፡፡

በሴቶች ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የተሻለ ስራ መፈጸም የሚቻልባቸው ጉዳዮችም ላይ በስፋት እንደሚሰራበት ጠቅሰዋል፡፡

ምንጭ :- ፕሬዘዳንት ፅ/ቤት

1 COMMENT

 1. ” ውይይታቸውም የሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር፡፡

  ኢቫንካ ትራምፕ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም ላይ እስከ 2025 ድረስ 50 ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢኒሽየቲቭ ይፋ ማድረጋቸውን አስታውሳለች ፡፡

  ይህ ባለፈው የካቲት ይፋ የተደረገው ፕሮግራም በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር ኢቫንካ ትራምፕ ገልፃለች ፡፡ ”

  That is not good, and reflects an Euro-centric mindset.

  No self-respecting government or country in Africa should get involved in activities that show ferenjis as humanitarians. That is misinforming the Ethiopian/African public and also insulting them.

  The appropriate image of ferenjis in Africa should be that of parasites, deceivers, oppressers, killers, etc.

  It is much better to give more publicity to CIA crimes in Ethiopia/Africa. Otherwise those African governments who support such activities will get the label Western puppets.

  And this concern for women is ill-motivated, perhaps suggested by CIA.
  It is sure to divide non-white societies, it is an attempt to advance the cause of USA imperialism by promoting it, etc.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.