የሙርሲ አወዳደቅ ምን እንማራለን (ሚኪ አምሀራ)


የግብጽን ሪቮሊዉሽንን ተቀብለዉ የመሩት ግራ ዘመም ፖለቲከኞች፤ ሊብራሎች፤ ሞደሬቶች ነበሩ፡፡ የእነዚህ እና የወጣቱ ጥርቅም ነበር ሙርሲን ከአቢዮቱ በኋላ ግብጽን እንዲመራ የተቸረዉ፡፡ ሙርሲ የግብጽን አንድነት ያመጣል የሚል በብዙ ሰዉ ዘንድ እሳቤዉ ነበር፡፡ ነገር ግን ሙርሲ ሳይዉል ሳያድር እነዚህ ወደ ስልጣን ያመጡት ወጣቶች፤ ሊበራሎች፤ ሞደሬቶች እና ሌሎች ፖለቲከኞችን ወደ ጎን እየገፋ Brotherhood ለሚባለዉ ድርጅት በግብጾች ዘንድ አክራሪ ሃይል ነዉ በሚል በማጆሪቲዉ ተቀባይነት የሌለዉን ድርጅት መደገፍ እና in the interest of the brotherhood ብቻ መስራቱን ተያያዘዉ፡፡ብዙ ለዘብተኛ የግብጽ ፖለቲከኞች በተለይም አቢዮቱን ዳር እንዲደረስ ያደረጉት በሙርሲ ላይ ማጎምጎም ጀመሩ፡፡

ሙርሲ ብዙዉ ሰዉ እየከዳዉ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ህዝቡ ጣህሪር አደባባይ እንዲሰበሰብ አደረገ እና ንግግር ለማድረግ ወደ አደባባዩ አመራ፡፡ እዛ ሰለፍ ላይ እኔ የእናንተዉ የህዝብ ልጅ ነኝ፡፡ እዚህ ስመጣ የቦንብ መከላያ ቬስት እንኳን አለበስኩም ምክንያቱም እኔ በህዝቤ እተማመናለዉ በማለት የጃኬቱን ቁልፍ ፈትቶ በማሳየቱ የግብጽ ህዝብ ማላገጫ አድርጎት ነበር፡፡ሆኖም ግን ህዝቡ ከንግግር ይልቅ የግብጽን ህዝብ አንድ የሚያደርግ ተግባር እንዲሰራ፤ ከጽንፈኛዉ የብራዘርሁድ ጋር ብቻ የሚያደርገዉን የፖለቲካ እንቅስቃሴ አካታች እንዲሆን ጠየቁት፡፡ ከዛም አልፎ በአመታዊ የግብጽ ወታደራዊ ትርኢት ላይ የቀድሞዉን የግብጽ ፕሬዝደንት አንዋር ሳዳትን ገዳይ በመጋበዙ እጅግ ብዙ ግብጻዉያንን አስቆጣ፡፡ ህዝቡም ግብጽ ወደ አላስፈላጊ የእርስ በእርስ ግጭት እና የኤክስትሪሚስት መፈነጫ ሆነች በሚል ከፍተኛ ተቃዉሞ በሙርሲ ላይ ማሰማት ጀመረ፡፡

ሙርሲ ቀስ በቀስ የራሱን ፓወር እያጣ የብራዘርሁድ ሰወች ሙርሲን አልፈዉ የፖለተካ ዉሳኔ ማስወሰን ጀመሩ፡፡ ሙርሲ እንዲሁ ቤተመንግስት ዉስጥ ያለ ሲምቦሊክ ሊደር ብቻ ሆነ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት ሙርሲን ሳያማክሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የዚህ ድርጅት ዋና ዋና ሰወች ዉሳኔ ይዘዉ ወደ ሙርሲ እና የእርሱ የፖለተካ ድርጅት አቀረቡ፡፡ አያስፈልግም የስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢልም ያቀረብነዉን ሃሳብ መቀበል ብቻ ነዉ ያንተ መብት በማለት ሙርሲ ሳይስማማበት ዉሳኔዉ ተወሰነ፡፡ ሙርሲ ህዝብ የማይፈልጋቸዉን እንዲሁም ሌሎች የአቢዮቱ አንቀሳቃሾችን ሳያማክር የሙስሊም ብራዘርሁድ አባላትን ብቻ እያመጣ መሾም በመጀመሩ ጉዳዩ ወደ ግብጽ ከፍተኛዉ ፍርድቤት ተወስዶም ነበር፡፡ በመጨረሻም ሙርሲን መርጠዉ መሪ ያደረጉት አካላት በሙሉ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ እንደገና መወትወት ጀመሩ፡፡ አቢዮቱም እንደተቀለበሰ እና ህዝቡ በፈለገዉ አቅጣጫ እንዲሁም ከተጠበቀዉ በተቃራኒ እየሄደ ነዉ በማለት መርጠዉ በሾሙት ሰዉ ላይ እንደገና ወደ አደባባይ መዉጣት ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም አቢዮቱን መጀመሪያ ላይ የመሩት ወጣቱ፤ ፖለቲከኞች፤ እና ሚዲያዉ አቢዮቱ መረጋጋት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ሳይሆን ያመጣብን ገዳዮች እና ጥንፈኞች የመንግስት መዋቅርን በመያዝ ግብጽን ሊያፈርሳት ነዉ በማለት ተነሱበት፡፡ ሙርሲ ይሄን ከህዝቡ የቀረበበትን ነቀፌታ ቢቀበልም በሙስሊም ብራዘርሁድ ሰወች ላየ ምንም የማድረግ ፓወር ስላልነበረዉ እስከመጨረሻዉ ምንም ሳይል ቤተመንግሰቱ ዉስጥ ተቀመጦ ይከታተል ነበር፡፡ በመጨረሻም ሙርሲ በራሱ ፓርቲ (FJP) ዉስጥ ያሉ ትቂት የብራዘርሁድ ጥንፈኞችን አደብ ማስያዝ አቅቶት እንዲሁ ቁጭ ብሎ በማየቱ የራሱ ሰወች ይዘዉት ወረዱ፡፡

ይህ የግብጽ ታሪክ የሆነ አገርን ታሪክ ነዉ የሚመስለዉ፡፡ ብቻ የየትኛዉ ሀገር እንደሆን ነዉ የረሳሁት፡፡ የሞዛምቢክ ሳይሆን ይቀራል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.