የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ)ጋዜጣዊ መግለጫ

የጋጥ ወጦች ድርጊት ትግላችንን እንድናጠናክር ያደርገናል

የአዲስ አበባ በለአደራ ምክር ቤት ከህዝብ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈፀም ላለፉት 35 ቀናት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል፡፡ በዚህ ጊዜ 3 ህዝባዊ ስብሰባዎችና አንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ሞክሮ፣ ሁሉም በአዲስ አበባ መስተዳድር ተፅዕኖ ተደርጎባቸው፣ ሁለቱን ለመሰረዝ ተገዷል፡፡ አንዱ ጋዜጣዊ መግለጫም ቢሆን፣ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅም መልኩ ክልከላ ተደርጎበታል፡፡
ይህ ሁሉ መንግስታዊ ህገ ወጥነት አግባብ እንዳልሆነ፣ የምክር ቤቱ ሰብሳቢና ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በተገናኙበት ጊዜ ተማምነውዋል፤ በቀጣይነትም፣ መስተዳድሩ ከህገ ወጥ ተግባራቱ ተቆጥቦ ህዝባዊ ስብሰባዎች ያለምንም ተፅዕኖ እንዲደረጉ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡
ይህ ስምምነት ሰኞ ዕለት ተደርሶ፣ በማግስቱ፣ ማክሰኞ፣ ለመስተዳድሩ በገባ ደብዳቤ፣ በቀጣዩ ቅዳሜ ሚያዚያ 5/2011 ዓ.ም በ24/መገናኛ በሚገኘው ኮከብ አዳራሽ የቦሌና አቃቂ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ እቅድ መያዙን፣ ለዚህም የፖሊስ ጥበቃ እንዲደረግ ተጠይቋል፡፡ ሆኖም፣ እስከ ዓርብ ድረስ የመስተዳድሩ ምላሽ በመጥፋቱ፣ ለራሳቸው ለምክትል ከንቲባው በቴክስት እንዲያውቁት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም፣ ዓርብ ዕለት በተሰጠ የቃል ምላሽ፣ በህጉ መሰረት ስብሰባ ለማድረግ እንደ ማይከለከል፣ የፖሊስ ጥበቃ ለማድረግ ግን መስተዳድሩ ፈቃደኛ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህ ተስፋ ባለመቁረጥ፣ ስብሰባውን በራሳችን ኃይል እያስጠበቅን ለማከናወን ወስነን በቦታው ላይ የተገኘን ቢሆንም፣ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በመኪና ተጭነው የመጡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣቶች፣ በቡድን በቡድን ተደራጅተው በአካባቢው ከመሰማራታቸውም በላይ፣ ወደ ስብሰባው አዳራሽ በመምጣት ሁከት ለመቀስቀስ ሞክረዋል፡፡ ይህንን ለፖሊስ ብናሳውቅም፣ በመጨረሻ ላይ፣ “ጥበቃ አይደረግላችሁም” የሚል እጅግ አሳፋሪና ኃላፊነት የጎደለው ምላሽ ተሰጥቶናል፡፡ በዚህ የጋጥ ወጦች ስልት ስብሰባ እንዳናደርግ በእጅ አዙር ጋሪጣ ተደቅኖብን፣ ራሳችንን ለመከላከል በቂ ኃይል ቢኖረንም፣ የህዝብ ደህንነትንና የሀገረን ሰላም በማስቀደም ስብሰባውን ሰርዘናል፡፡
እንደዚህ ዓይነቱ ጋጥ ወጥ አካሄድ፣ በባለአንጣነት እየተፈረጀ ላለው ለአዲስ አበባ ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተጀመረው የዲሞክራሲ ሽግግር አደገኛ በመሆኑ፣ አስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ አጥበቀን እንጠይቃለን፡፡
የማስተካከያው እርምጃ ቢወሰድም ባይወሰድም ግን፣ ሰላማዊ ትግላችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለወዳጆቻችንም ሆነ ለተቀናቃኞቻችን ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ቁርጠኝነታችንንም በቀጣይነት በምንወስዳቸው ሰላማዊ የተግባር እርምጃዎች እናሳያለን፡፡

የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት

ሚያዚያ 7/2011 ዓ.ም አዲስ አበባ

5 COMMENTS

 1. ” በዚህ ተስፋ ባለመቁረጥ፣ ስብሰባውን በራሳችን ኃይል እያስጠበቅን ለማከናወን ወስነን በቦታው ላይ የተገኘን ቢሆንም፣ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በመኪና ተጭነው የመጡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣቶች፣ በቡድን በቡድን ተደራጅተው በአካባቢው ከመሰማራታቸውም በላይ፣ ወደ ስብሰባው አዳራሽ በመምጣት ሁከት ለመቀስቀስ ሞክረዋል፡፡ ይህንን ለፖሊስ ብናሳውቅም፣ በመጨረሻ ላይ፣ “ጥበቃ አይደረግላችሁም” የሚል እጅግ አሳፋሪና ኃላፊነት የጎደለው ምላሽ ተሰጥቶናል፡፡ በዚህ የጋጥ ወጦች ስልት ስብሰባ እንዳናደርግ በእጅ አዙር ጋሪጣ ተደቅኖብን፣ ራሳችንን ለመከላከል በቂ ኃይል ቢኖረንም፣ የህዝብ ደህንነትንና የሀገረን ሰላም በማስቀደም ስብሰባውን ሰርዘናል፡፡ ”

  What a shocking situation, what a criminal method !

  This is not a government, this is a government of thugs or a mafia group.

  1. ODP officials are scared of the people gathering to express their views. So, they simply forbid the gathering.

  2. When the Balderas group remembered the ODP thugs of their democratic right to gather, then the ODP thugs thought, ‘how could we allow them to gather but prevent the gathering ?’
  Then they got the idea to allow the gathering but deny police protection.
  They denied police protection because they intended to contact violent oromo guys and to tell them to go to the meeting place and disturb the gathering.

  3. At the date of the gathering the ODP thugs transported the violent oromo guys to the meeting place and told them to go inside and disturb the gathering. The ODP police assured the violent oromos that they will rescue them if they are in danger.

  You see, what a government ODP is ?
  This is fascism and barbarism, not a civilized way of conducting business. And Abiy and Lema knew all about that. These violent oromo guys that the police brought are the equivalent of the Blackshirts, a paramilitary wing of the National Fascist Party of Mussolini, and SA of Hitler.

  What happened in Addis Abeba is a dangerous development. Unbelievable that Abiy and Lema ordered that. Why are they so much scared of the gathering of the people in Addis Abeba ?
  To which hidden plan of Abiy and Lema are the people in Addis Abeba a threat ?

  And compare the Professor’s trust in Abiy to what ODP, led by Abiy, did in the gathering. Were the Professor forced to that ?

  ” የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ከየት ወዴት? “ዶ/ር ዓቢይ የሚሄደው በሁለት ሐዲድ ነው። የኢትዮጵያን አንድነት ያምንበታል። የመጣው ከዚያ ቢሆንም፤ የጎሣ ፖለቲካን አያምንበትም።” – ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ”

 2. About the SA of Hitler:

  SA – Sturmabteilung

  The Sturmabteilung, literally Storm Detachment, was the Nazi Party’s original paramilitary. It played a significant role in Adolf Hitler’s rise to power in the 1920s and 1930s. Its primary purposes were providing protection for Nazi rallies and assemblies, —-> disrupting the meetings of opposing parties <—-, fighting against the paramilitary units of the opposing parties, especially the Red Front Fighters League (Rotfrontkämpferbund) of the Communist Party of Germany (KPD), and intimidating Romanis, trade unionists, and, especially, Jews – for instance, during the Nazi boycott of Jewish businesses.

  Source: wikipedia

 3. መገንዘብ የሚያስፈልገው ጉዳይ

  1ኛ.ይህ ቡድን በአዲስ ኗሪ ህዝብ ውክልና የተሠጠው ሳይሆን ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው የአንድ ወገን ሠዎች ስብስብ ነው ፡፡ ይህም ማለት የህዝብ ውክልና የለውም፡፡

  2ኛ.በየትኛውም የመንግስት አካል ምንም አይነት ህጋዊ እውቅና ያልተሠጠው አላማው ና ምንነቱ በግልፅ የማይታወቅ ህገ ወጥ ነው፡፡

  3ኛ. የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደነዋሪ ዘር ሳይለይ የሚሠባሰብበት ሳይሆን የአማራ ተወላጅ ብቻ የተሠባሠበበት የዘረኞች ስብስብ ነው፡፡

  4ኛ. አሁን በስልጣን ያለውን መንግስት ና መዋቅር ህጋዊነት የማይቀበል ና እራሡን እንደመንግስት ያስቀመጠ የለየለት አናርኪ ቡድን ነው፡፡
  5ኛ, አዲስ አበባ የአማራ ከተማ እንጂ የበሔር ብሔረሰብ መኖሪያ ተማነቷን አይቀበልም፡፡ ለዚህ ማሳያ ኦሮሞ አዲስ አበባ አይገባም ብለው ግርግር በመፍጠር ብዙ ሠው ያለቀበትን ኩነት መስታወሱ በቂ ነው፡፡

  ስለዚህ በግልፅ ቋንቋ የባለ አደራ ፖለቲካ የአማራ ፅንፈኞች የዘር ፖለቲካ ስለሆነ ይህ ለማንም የማይጠቅም ወደ ሁከትና ብጥብጥ የሚያመራን ማንም የማያሸንፍበት አካሔድ በመሆኑ መላው የአዲስ አበባ ኗሪ የሴራው ፖለቲካ መሣሪያ ና ሰለባ ከመሆን እራሱን መጠበቅ አለበት ፡፡

 4. ይገርማል——-/+/

  ይሄ ዛሬ አዲስ አበቤ ነኝ ፤ ባለአደራ ነኝ ያዙኝ ልቁኝ እያለ የሚፎክረው የሚያስቸግረው ትላንት በፀረ ወያኔ ትግል ወቅት ቢቀሰቀስ ቢቀሰቀስ ቢባልም ቢሰራ ” አረ ጎራው ” ‘ እረ ደኑ ” “በእናትህ ና ባባትህ ወኔ” ቢባል በ97 ያረፈችበት የወያኔ ልምጭ አንስቴዚያ ሆና 13 ዓመት ያስተኛችው እና ቄሮ መጥቶ እስኪቀሰቅሰው ድረስ እንቅልፍ ላይ የነበረ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.