አቶ ለማ መገርሳ ወደ ፊዴራል መሄዳቸው ጠቃሚ እርምጃ ነው ባይ ነኝ  # ግርማ ካሳ

ከአምስት ሳምንታት በፊት ፣ አቶ ለማ መገርሳ በኦሮሞ ክልል መንግስት ካለው ሃላፊነቱ እንደሚነሳ ገልዤ ነበር።

” አቶ ለማ መገርሳ በፖለቲካ በጣም ከመዛሉ የተነሳ ሊለቅ ይችላል እየተባለ ነው። ከአስራ ሰምንት ጊዜ በላይ ነው ከኦነጎች ጋር ድርድር ያደረገው። እነርሱን ማግባባት ድንጋይ ላይ ውሃ ማፈሰስ ነው የሆነበት። በኦህዴድ ውስጥ ከጃዋር ጋር በቁርኝነት የሚሰሩት፣ ብዛት ያላቸው የአርሲ ሰዎች፣ እነ ጠይባ ሃሰን አላሰራ ብለዉታል ነው የሚባለው። የአቶ ለማ ትእዛዝና መመሪያ በዞን ወረዳና ቀበሌ አመራሮች ዘንድ የሚሰማ ብዙ ያለም አይመስልም” ብዬ ነበር የጻፍኩት።

ከቀናት በኋላ አርቲስት ታማኝ በየነ እነ ዶ/.ር አብይ አቅም የላቸውም ማለቱን ተመርኩዤ ፣ “ከታማኝ እለያለሁ፣ ዶ/ር አብይ አቅም አለው” በሚል ርእስ በፊዴራል ደረጃ ዶ/ር አብይ የወሰን ችግር ስላለበት እንጂ ከደፈረ ብዙ ሊሰራ እንደሚችል በመግልጽ አቶ ለማ መገርሳ ግን በኦሮሞ ክልል መንግስት ውስጥ ጽንፈኞች ስለበዙ ምንም የማድረግ አቅም እንደሌለው በማስቀመጥ፣ አቶ ለማ ወደ ፌዴራል ቢመጣ ፣ የበለጠ ሊሰራ እንደሚችልም ጠቅሼ ነበር።

በወቅቱ የሚከተለውን ነበር የጻፍኩት፡

“የኦሮሞ ክልልን የሚመራው አክራሪው የናዚ ድርጅት ኦህዴድ ነው። ስለዚህ፣ እነ ጠይባ ሁሴን እያሉ፣ አቶ ለማ በኦሮሞ ክልል መንግስት ውስጥ ለውጥ የማምጣት አቅም የለውም ባይ ነኝ። ለምን ሁልጊዜ በድምጽ ይሸነፋልና። አብዛኛው የኦህዴድ አመራር ለማ መገርሳን ከመስማት ይልቅ የሚሰማው፣ እነ ጃዋርንና ኦነጎችን ነው። በቀበሌ፣ በወረዳ ያሉ አመራሮች “ለማ ምን አገባው ነው ?” የሚሉት።

ስለዚህ ለማ መገርሳ አቅም የለውም። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም በቅርቡ ከሃላፊነቱ ሊለቅ ይችላል የሚል ጭምጭምታ ከአንዳንድ ማእዘናት የሚሰማው። አቶ ለማ ይለምናል፣ ይማጸናል፣ ለማግባባት ይሞክራል፤ ለሕዝቡ የሚበጀው ሰላም ነው ፍቅር ነው ይላል፤ ሰሚ ግን አላገኘም። እነ ለማ ከኦነጎች ጋር ብቻ፣ እነርሱን ለምነው እዚያ ሻግተዉበት ከነበረው ቦታ፣ ከኤርትራ እንዲገቡ አድርገው፣ ማረፊይ ሆቴል፣ ጽ/ቤት ሰጥተው፣ ከወገኖቻቸው ጋር አቀላቅለው፣ ለዚህ ዉለታቸው ምላሹ አመጽና ጦርነት ሆኗል። በጎ ነገር ባደረጉ፣ በነ አቶ ለማ ላይ ኦነጎችና የኦሮሞ ጽንፈኞች አመጸው፣ የኦሮሞ ክልል በወያኔ ጊዜ ከነበረው ሁኔታ አስር እጥፍ የባሰ እንዲሆን ነው ያደረጉት። እነዚህን ለኦሮሞ ሃሳቢ ነን የሚሉ ግን የኦሮሞ ጠላቶችን ለማግባባት፣ ለመማጸን አቶ ለማ ሞከረ፣ ደከመ። ከአስራ ሰባት ጊዜ በላይ ስምምነት ተደርሶ ስምምነቱ ጽንፈኞቹ ሊጠብቁ አልቻሉም።

በሌላ በኩል እዚያው በኦሮሞ ክልል መንግስት ውስጥ፣ ኦህዴድ ውስጥም ያልተደመሩ የክልሉ ባለስልጣናት አቶ ለማን አላሰራ እንዳሉትም ነው የሚነገረው።

አቶ ለማ በግርጥ ከሃላፊነቱ ቢለቅ ለርሱ ፣ ለሌጋሲው እንደውም በጣም የተሻለ ነበር የሚሆነው። ዶ/ር አብይ በፌዴራል ደረጃ ሃላፊነት ቢሰጠው፣ አብረው በጋራ ብዙ ሊሰሩ ይችላሉ ባይ ነኝ።”

አሁን በስፋት ከኢሕአዴግ ምክር ስብሰባ በኋላ አቶ ለማ መገርሳ ወደ ፊዴራል እንደሚመጡ እየተገለጸ ነው። የአቶ ለማ ወደ ፊዴራል መምጣት ለፌዴራል መንግስቱ ትልቅ ጉልበት የሚሰጥ ነው።

በኦሮሞ ክልል መንግስት ርእስ መስተዳደር ማን ሊሆን እንደሚችል በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። ሆኖም ምክትሏ ወ/ሮ ጠይባ ሃሰን ርእሰ መስተዳደር ከሆነች ፣ የክልል መንግስቱ በቀጥታ ከለማ ቲም ወይንም ፌዴራል መንግስቱ ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቱ አይቀሬ ነው የሚሆነው። በክልሉ ለሚኖሮ ኦሮሞ ላልሆኑ ማህበረሰባት አስደንጋጭና አስፈራኢ ዜና ነው የሚሆነው።

ሆኖም ከኦዴፓ አካባቢ ያሉ ምንጮች እንደገለጹት፣ የሸዋ ኦሮሞ የሆኑት ዶ/ር አለሙ ስሜ የኦሮሞ ክልል መስተዳደር ሊሆኑ የሚችሉበትም እድል በጣም የስፋ እንደሆነ ይነገራል። እነ ጃዋርም ከወዲሁ ዶ/.ር አለሙ ስሜ ላይ ዘመቻ የከፈቱትም ከዚህ የተተነሳ ሳይሆን አይቀርም። ዶ/ር አለሙ የመጀመሪያው የሸዋ ኦሮሞ የክልሉ ርእስ መስተዳደር ከሆኑ፣ እነ ጃዋር የክልል መንግስቱን የማሽከርከር አቅማቸው በ እጅጉ የሰባበራል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.