በዛሬው ዕለት የፈረሱ የጥላቻ ምሽጎች (የሸዋ አንድነት)

እነጃዋር የመሸጉበት የምስራቁ ክፍል የጥላቻ ምሽግ በዛሬው ዕለት ዶግ አመድ ሆኗል፡፡ ለዚህም አዲሱ አረጋን እናከብራለን፡፡ ጃዋር ከአሁን በሁዋላ የኦሮሞ ህዝብ ብሎ የሚያላዝንበትን ምላሱ ነው የተቆረጠው፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ የOMN የፕሮግራም ፎርማትም ሊቀየር ይችላል፡፡

ሌላው ትልቁ ነገር አኖሌ ጉዳይ ነው፡፡ ለአኖሌ መቆም ምክንያቱ የቡርቃው ዝምታ ነበር፡፡ አኖሌ በሸዋ ህዝብ ላይ ለተነዛው የፈጠራ ታሪክ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ይቁም ካልተባለ በስተቀር እነኦነግዬ በከተቡት ተረት አግባብ ትርጉም የሌለው ሆኗል፡፡ ትልቅ ድል ነው፡፡ እንግዲህ የጥላቻን ንግግር አታድርጉ ብሎ ህግ ያወጣው መንግስ የጥላቻ መሠረቶችን እንዲህ ሲንድ የሚያስመሠግን ነው፡፡ በእውነትለአዲሱ አረጋም ሆነ ለዚህ በጎ ሐሳባ ተባባሪ ለሆኑ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ነገር ግን ወለጋዎች የገነቡት የጥላቻ ምሽግ ግን ይቀራል፡፡ ኦሮሞ የሚባል ተረት ተረት፡፡ እንግዲህ እስከዛሬ የቡርቃ ዝምታን ሲያሞጎሱ የነበሩ ኦሮሞ የሚለው ተረት ለምን አሞገሱ አይባልም፡፡ ለበርካታ አመታት የተገነባው የጥላቻ ልማድም ለመናድ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ሊታሰብበት ግን ይገባል፡፡የቡርቃ ዝምታ ለምስራቁ ቡድን የጥላቻ ምሽግ ገንበቶ በብዙ ጥፋትና ክፋት እስከዛሬ ለብዙ ዜጎች ጉዳት የሆነው ድርሰት ባለቤቱ ተስፋዬ ገ/አብ እንደሆነ ሁሉ በብዙ ተረትና ምንም መረረት በሌላቸው ትረካዎች የታጀበው ኦሮሞ የሚባለው ማንነትም መሠረቱ ጆሀን ክራፍ እንደሆነ አሁን ላለበት ደረጃም ያበቃው የኦነግ በጥላቻ ላይ የተመሠረቱ ትረካዎችና ተረቶች መሆናቸውን ሁሉም ማወቅ አለበት፡፡ ዛሬ ለፈረሰው የነጃዋር ምሽግ ቱለማዎች ደስታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ምስጋናቸውንም ያቀርባሉ፡፡

የሸዋ አንድነት ለነፃነት፡፡
ቱለማ ታሪኩን ያድሳል፡፡

 አምቦ … አሞራው በሰማይ ሲያሽ ዋለ…”

ሰላም

***************************
አምቦ የነበረው የኦሮማራ መድረክ በኦሮሞ እና አማራ ጥል ላይ ህልውናቸውን የተመሰረተ ሁሉ ዳግም አንገታቸውን ያስደፋ ታሪካዊ ነበር፡፡ ኦሮሞ እና አማራ የፍቅር ድግስ ከደገሱ አሞራው በሰማይ ሲያንዣብብ በመዋሉ የሚጠበቅ ተግባራቸው ነው፡፡ ትናንትም አምቦ ሰማይ ላይ ሲያንዣብብ የዋለው አሞራ ከዚያ ሁሉ ድንቅ ተግባር፣ ከታሪካዊው የሁለቱ ሕዝብ ጥምረት ውስጥ ከአቶ አዲሱ አረጋ ካቀረቡት ጽሁፍ ላይ አንድ አረፍተ ነገር መዞ ወደ ማሕበራዊው ሚዲያ ይዞ በመሮጥ ዋና አጀንዳ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ቅንነት ቢኖር የአምቦው የኦሮማራ መድረክ ሊወደስ፣ ሊመሰገን፣ ሊበረታት ነበር የሚገባው ነገር ግን የኦሮማራ የፍቅር ሰማይ ላይ ዳመና ለማደመን ወዲያ ወዲህ መሯሯጡም ተገቢም አልነበረም፡፡ የኦሮሞ እና አማራ በአንድ ግንባር መሰለፍ ለዚህ ሀገር የጥንካሬ መሰረት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ስናየው ተስፋየ ገ/ብአብ የጮኸለት የግል ዝና ኢሚንት ነው፡፡ እውነት ለመናገር የተስፋየው የቡርቃ ዝምታ መጽሐፍ የድጋፍ ሰለፍ የሚወጣለት አይደለም፡፡

ተስፋየ ገ/አብ ለምን ተነካ ብሎ ከመንገብገብ በፊት “የቡርቃ ዝምታ”መጻፍ ለምን ዓላማ እንደተጻፈ መለስ ብሎ መፈተሸ ያስፈልጋል፡፡ አቶ መለስ ጫካ ውስጥ ባረቀቀው የህወሐት ማኒፌስቶ “ኦሮሞና አማራ በአንድነት ከቆሙ የእኛ ህልውና አከተመ ማለት ነው፡፡ ይህ እንዳይሆን ሁሉም አማራጮች መጠቀም አለብን “ የሚል አረፍተ ነገር እንዳለበት የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ኦሮሞ እና አማራ ልዩነታቸው አጥበው ሕብረት ከፈጠሩ ትናናሽ መንግስታት መቀመጫ ስፍራ ስለማይኖራቸው አቶ መለስ “ሁሉንም አማራጮች መጠቀም ይገባናል “ ሲሉ በማኒፌስቷቸው ያስቀመጡት አካል ነው የተስፋየ ገ/አብ “ የቡርቃ ዝምታ” መጽሐፍ፡፡

ተስፋየ ገ/አብ “ የቡርቃ ዝምታ” የጻፈው በወቅቱ በበረከት ሰምኦን በሚመራው የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ስር ሆኖ ሀሳብም ቀለብም እየተሰፈረለት ነው፡፡አሳትሞ ያሰራጨው በአቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ስር የሚተዳደረው ሜጋ አሳታሚ ነው፡፡ ዓላማውም ግልጽ እና ግልጽ ነው ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ዛሬ መኖር እንዳይጀምር፣ ነገውን እንዳማያትር የትናንት ብሶቱን እያከከ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ በሀገር አንድነት የማይደራደር ጀግና ሕዘብ ስለመሆኑ ለአድዋ ድል የፈጸመውን ጀብዱ መጥቀስ ብቻ በቂ ነው፡፡ይሄን ለሀገር አንድነት ለሕዝቦች ነጻነት የከፈለውን የጀግንነት ደማቅ ታሪኩን እንዲረሳ እና በጨቋኝ መደቦች የደረሰበትን በደልና ግፍ ለዓመታት እንዲያመነዥክ በማሰብ ነው የተስፋየ ገ/አብ “ የቡርቃ ዝምታ” እና ሌሎች መጽሐፍት በሕወሐት ስንፓንሰርነት እየታተሙ ለገበያ የቀረቡት፡፡ ለእኔ “ የቡርቃ ዝምታ” ደራሲ ተስፋየ ገ/አብ ሳይሆን ሕወሐት ነው፡፡ ሕወሐት ጠግባ የምትበላው አማራ እና ኦሮሞ ርስ በርስ ሲበላሉ በመሆኑ በማኒፌስቶዋ እንዳለችው መጽሐፍ አሳትሞ ማሳራጨትን ጨምሮ ሁሉን አማራጮች ተጠቅመዋል፡፡

 የተስፋየ ገ/አብ “የቡርቃ ዝምታ” ውስን ገዥ መደቦች ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የፈጸሙትን ግፍ እና በደል አማራ የሚል የወል ስም በመጥራት …”የገደለህ፣ ያፈናቀለህ፣የገረፈህ፣ የበደለህ” አማራ ነው ብሎ እንዲያስብ በተጠና አካሂያድ፣በውብ ቋንቋ የሚተረክብት መርዘኛ መጽሐፍ ነው፡፡ ‘’የአማራ ሕዝብ ምን አደረገኝ ብሎ የኦሮሞን ሕዝብ ይበድላል?….ምንስ አቅም አለው?’’ ሕዝብ ፈጽሞ ሕዝብን አይበድልም፡፡ ያለፉቱን ጨቋኝ ገዥ መደቦች የአማራ ሕዝብ ሂዱና የኦሮሞን ሕዝብ በድሉልኝ ብሎ እንደላካቸው አድርጎ በመጽፍ መተረኩ ያው ዓላማው ያው ተነታረኩ ነው ፡፡ የአማራ ሕዝብ ኦሮምያ ክልል ከሄደ የሚሄደው ለመኖር ነው፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር አባላት ጋብተው፣ ተዋለደው፣ ርስ በርስ ተጋምደው በኦሮምያ ክልል ይኖራሉ፡፡ ገዥ መደቡ እንደ ኦሮሞ ሁሉ የአማራውም ጠላት ነው ፤ለዚያም ነው የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ሆኖ አምባገነኖችን ለመገርስስ አብሮ የታገለው፡፡ገዥ መደቦች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የፈጸሙትን ግፍም የአማራ ሕዝብ በራሱ ላይ እንደተፈጸመ አድርጎ እንደሚቆጥረውም ለማሰብም ቀና ልቦናን መክፈት ይበቃል፡፡ ከዚህ የነጠረ እውነታ ይልቅ ሁለቱ ሕዝቦች የጎሪጥ እንዲተያዩ የሚያስችሉ ትርክቶችን በአቶ መለስ ፊታውራሪነት ሲጋቱ ኖረዋል፡፡ ሁለቱ የሀገሪቱ ዋርካ የሆኑ ሕዝቦች ከነ ተስፋየ ጥልፍልፍ ሴራን አሸንቅጥረው ጥለው በአንድነት ሲቆሙ ሕወሐት እንደፈራችው አሽቀንጥረው ጥለዋታል፡፡ የቡርቃ ዝምታን የሕወሐት ልብወለድ መጽሐፍ የኦሮሞ ታሪክ አድርጎ ለመተንተን መሞከርም የኦሮሞ ሕዝብን ታሪክ፣ ድል፣ ስኬት፣ ጀግንነት በደንብ ካለማጥናት የመነጨ ስለሆነ የሚያስተዘዝብ ጉዳይ ነው ፡፡

 ታዲያ እውነቱ ከሆነ ‘’አቶ አዲሱ ምን አጠፉና እና ነው ትችት የበረከተባቸው?” ምክንያቱ ግልጽ ነው ፡፡
አምቦ ሰማይ ላይ ሲያንዣዥብ የዋለው አሞራ ደማቁን የአምቦውን የኦሮማራ መድረክ ላይ አንድ አረፍተ ነገር በአፉ ይዞ ማሕበራዊ ሚዲያው ላይ ጆፌውን በመጣል የእነ መለስን ማኒፌስቶ መተገብር ሌላ ሚስጥር የለውም፡፡
አምቦ ሰማይ ላይ የፈካውን የኦሮማራ ፍቅር በቡርቃ ዝምታ ወሬ ለማዳመን ከመሞከር ዝም ማለት የአባት ነው፡፡

1 COMMENT

  1. በኦፒዲኦ እና ብአዴን መካከል ድሮም “የጥላቻ ምሽጎች” አልነበሩም። በአንድ አመት ተረሳ?? ሁለቱ የወያኔ ተላላኪ ድርጅቶች ተሰባስበው ቢማማሉ መሃላቸው ያለውን ይስልጣን ሽኩቻ ያረግብ እንደሆን እንጂ፣ ስምምነታቸው ህዝብን አያስማማም፣ ጥላቸውም ህዝብን አያጣላም። በህዝቦች ማሃል ያለ አለመግባባት ደግሞ በአዋጅ አይፈታም!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.