ይድረስ ለኢትዮጵያ ምቀኞች ፤ ሸረኞችና ሴረኞች -በያላችሁበት (ከ አባዊርቱ)

በሃቅ የምትሞግቱትን አያካትትም፤፤ እንዲሁም ወግ ባለው የምትተቹ ግለሰቦችና ቡድኖች፤፤ በጤና አይምሮ የምትቃወሙትን አያካትትም፤፤ እኔ የማወራው ስለሚከተሉት ነው፤፤
ምሁር ሆነው ለመተቸት ብቻ የሚተቹ
ጋዜጠኛ ሆነው ስራው የጠፋባቸው፤፤ ክህሎቱም የባረቀባቸው ወይም ነገሩ ገብቶአቸው ሆን ብለው ሙያቸውን ቁጭት መወጫ የሚያረጉ፤
ተቃዋሚ ሆነው ምኑን እንደሚቃወሙ የተዘበራረቀባቸው ብቻ ሳይሆን ሆን ብለው ለስልጣን ብቻ እስከሆነ ያላቸውን  አየር ላይ የሚወረውሩ፤፤ ያሻው ይቅለብ መሬት ሲወርድ ብለው ሆን ብለው ሲተራመሱ የሚውሉ፤፤
የለየላችሁ ፅልመቶችና ውላጆቻቸው
የለየላችሁ አክራሪዎችና ፅንፈኞች
በያላችሁበት የሰላምንና የአብሮነትን ሳይሆን የመጠፋፋትንና የመተላለቅን ቅዠት ስትቃዡ ለምትውሉና ለምታድሩ ማስታወሻ ይሁንልኝ፤፤
ወገኖቼ፤ መቼስ ወገን ለማለቱም ይከብዳል የጠላት ስራ ስለሆነ አንዳንዶች  የምትሰሩት ሁሉ፤፤ የሰሞኑ አዲሱ አረጋና ሺመልስ አብዲሳ ወደ አመራር ብቅ ማለትና በተለይ ተስፋዬ ግብረአብን ስም በክፉ መነሳቱ ያስቆጣችሁ ወይም አጉል የሚያስተቻችሁ ምኑ ነው? የለየላችሁን ፅልመቶችን አደለም የምጠይቀው፤፤ እናንተማ ይህን ማር እያላሰ አንድ ትውልድ ያጠፋብንን ሰውዬ በግሌ ፍርድቤት አቆመው ነበር እንኩዋንስ ውግዘት፤፤ ውግዘትማ አደለም ላለፉት 27 አመታት ቀርቶ ለሚቀጥሉት 27ስ ይበቃናል እንዴ? አንድ ቄሮ ትውልድ የፅልመት ውላጅ በፃፈው ድርሰት ብዙ ተባብለን ሃውልት ሁሉ ቆሞልን አልኖረም እንዴ? አዲሱ አረጋ ቢያወግዘው ይብዛ እንዴ? እንደው ይህ  ታሪኩ  ሳይወድበግዴታ የጠፋበት ወጣት ትውልድ ይበልጡኑ እንዳይታመሙ ከሚል መሳሳትና አርቆ አስተዋይነት ካልሆነ በቀር ህሊና ያለው ዖሮሞ ሁሉ እነ ኦቦ ለማና ዶር አቢይን ጨምሮ ይህን ከንቱ ሰውዬ በአደባባይ ይቅርታ ሁሉ ማሰጠየቅ ነበር፤፤ የሚገርመው አዲሱ አረጋና ተስፋዬ ገብረአብ አንድ ናቸው የምትሉም አላችሁ፤፤ እናንተ እንኩዋ ፅልመቶቹ ናችሁ፤፤ አገር የሚያውቃችሁ ፅልመት ያልሆናችሁ ግን ማንን ለመጥቀም ነው ይህ ሁሉ እነ አዲሱ ላይ አቃቂር ማውጣት? ዖሮማራውን? ኢትዮጵያን? እስቲ አስቡት በውስጠ ህሊናችሁ፤፤
የሺመልስ አብዲሳ መምጣት ያሳመማችሁ እንዳላችሁ ሴንስ አርጌዋለሁ፤፤ ይህ እንኩዋ ከግል አብዛኛውን የነኢሃፓና መኢሶን ትውልድ ስልጣን ናፋቂዎች የመጨረሻ የምኞት እድል ማብቅያው ሆኖባችሁ እንጂ የዚህ ልጅ የሚገርም ክህሎት የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ነው የሆነብኝ፤፤ በዚህ አጋጣሚ የዶር አቢይንና የኦቦ ለማን አካሄድ ለሚጠራጠሩ ወገኖች ማርከሻ መድሃኒትም ሳይሆን አይቀርም ይህ ልጅ፤፤ እስቲ አንድ የሚያስተች ወይም የሚያሽሙዋጥጥ ምን ንግግር አደረገ አምቦ ላይ? የሺመልስንስ ላንዱ ድሮን በመለስኩት ትንሽ ጨምሬ ልሰናበታችሁ ለዛሬው፤
«ኢትዮጵያ የ ኢያሪኮ ግንብ አይደለችም፤፤ በ ጩኅት አትፈርስም»
 የሰንጋፈረሰኞቹ ልጅ ሺመልስ አብዲሳ፤
 በዚህ ንግግሩ ለስራ እንነሳ
 መቆዘሙ ያብቃ ባለፈው አበሳ
 የፅልመትን ሴራ ጭራሽ ሳንረሳ
 ብሎ በማለቱ አቡዋራው ይነሳ???
 የኛን አቃፊነት ለምትጠረጥሩ
 አብረን ስንላችሁ ለምትዘረዝሩ
 በጥቂት ፅንፈኞች ሁሉን ላልወከሉ
 ኩርፊያችሁ አይሎ ያሻቹን ብትሉ
 ያ ታላቁ ለማ ሺሜን ሰጠን አሉ
 የተጠበቀ ነው የላይ ድንቅ ቃሉ፤፤
 ኢትዮጵያዊነትን ስታቀነቅኑ
  ጨለማው ተገፎ ደምቆ ሳለ ቀኑ
  በነአዲሱ ይሾፍ? አወይ ሰው ብኩኑ!!!
  እናም ወገኖቼ ትውልደ ኦሮሞ
  አማራው ከሰሜን ደቡብ ሳይቀር ጋሞ
  ትግራይ ሆንክ ጉራጌ ወይም ወላይታው
  ምቀኛን ተዋጋ ጭራሽ ፋታ አትስጠው
  ለምዬ ኢትዮጵያ ሁሉም ተጠሪ ነው፤፤
  ቅንነቱ ካለ ፊታችን ብሩህ ነው

1 COMMENT

 1. የመልዕክትህ ተደራሲዎች ዉስጥ የሚከተሉት ለምን አልተካተቱም??
  አዋቂ ነን ብለው የሚያስቡ አላዋቂዎች፣
  ዲሞክራሲ ማለት ራሳቸው የስልጣን ኮርቻ ላይ ሲፈናጠጡ ብቻ እንደሆነ የሚያስቡና ሁሉም በነርሱ አንጎል የሚያስብ የሚመስላቸው የድሮ ስርዐት ናፋቂዎች፣
  እነርሱ ካልጻፉት ወይም እነርሱን ካላወደሰ ታሪክ ታሪክ የማይመስላቸው ደነዞች፣
  ታሪክ እንደእግዜር ቃል የማይሻር የማይሻሻል የሚመስላቸው ቂሎች፣
  ሚኒሊክ መልዐክ እንደሆነና 45ኛውን ታቦት በስሙ ለመቅረጽ የሚመኙ ህልመኞች፣
  አሁንም ምድር ዝርግና የዩኒቨርሱ ማዕከል እንደሆነች፣ የምድራችን ማዕከል ደግሞ አቢሲኒያ እና አማራ እንደሆኑ የሚያስቡና የሚጽፉ የድንጋይ ዘመን ፈላስፎች፣
  ወዘተርፈ… (ምድራችን በአዕምሮ ድኩማን የተሞላች ስለሆነች የተቀሩትም )

  ምናልባት አንተም ከተራ ቁጥር 1 ዉስጥ ራስህን መድበህ ይሆናል፣ ልበወልድ የጻፈን “አንድ ትውልድ ያጠፋብንን ሰውዬ” ብለህ ታቅራራበታለህ! “ታሪኩ ሳይወድ በግዴታ የጠፋበት ትውልድ” ያንተው ትዉልድ መሆኑን አንተው ህያው ምስክር ነህ! ስለአኖሌ የታሪክ ተመራማሪዎችን ግኝት ከዛሬ 5 አመት በፊት አንዱ የጻፉትን ayyaantuu.org ላይ አንብብ *Aanolee: ‘a tragedy on which Ethiopian sources are silent’ By Mohammed Ademo, April 8, 2014

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.