የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ ሄሊኮፕተር በቦሌ ቡልቡላ አከባቢ መኖሪያ ቤት ላይ ወደቀ

ባለቤትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ አንድ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በመብረር ላይ ሳለ ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ መውደቁ ተገለፀ ፡፡በሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም

ከሜድሮክ ግሩፕ በገኘነው መረጃ ሂሊኮፕተሩ ሁለት መንገደኞችን ይዞ ጉዞ የጀመረ ቢሆንም አንዱ ሞተሩ ላይ ችግር ስለገጠመው ለማረፍ ወደ ኤርፖርት ሲመለስ በሁለተኛው ላይም ችግር እንደ ገጥሞት ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ መውደቁ ታውቋል፡፡

በመንገደኞቹም ሆነ በአብራሪዎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱም ተነግሯል፡፡

“በልጄ ሰማንያ የሙት መታሰቢያ ቀን ቤቴ ላይ ሄልኮፕተር ወደቀ” ~ አቶ ጥላሁን ወንድማገኝ – ባለቤትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነው ሄሊኮፕተር ቤታቸው ላይ የወደቀው አንድ አባት !

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.