የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ዶ/ር ነጋሶ ከ1987 ዓም ጀምሮ ሀገራቸውን ለዓመታት በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል::

በጀርመን አገር በሕክምና እየተረዱ ነበር።

በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ላይ በደንቢ ዶሎ የግል ተወዳዳሪ በመሆን ፓርላማ መግባታቸውም ይታወሳል።

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከወጣትናቸው እድሜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲዘረጋ ሲደረግ በነበረው ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው።

ለዚህም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመሰለፍም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል።

በታሪክ ትምህረት ሦስተኛ ወይም ዶክትሬት ዲግሪያቸውን የያዙት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፥ እንደ ምሁርነታቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራትም የተለያዩ ግልጋሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል።

በተማሩት ትምህርትም የኦሮሞን ባህል፣ ታሪክ እና እሴት የሚያንፀባርቁ እና የኢትዮጵያን አንድነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ጥናቶችን አካሂደዋል።

ነፍስ ይማር!

ጌጡ ተመስገን

Negasso Gidada

From Wikipedia, the free encyclopedia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.