በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከሰሩት በጎ ስራወች መካከል

በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ከነበሩት ታላላቅ ሰዎች መካከል አንዱ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በፋሲካ አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል።

ዶ/ር ነጋሶ ከፖለቲካ ሕይወታቸው ውጭ እራሳቸው የቤት መኪና እንኳን ተከልክለው አዲስ አበባ ላይ ከሕዝብ ጋር እየተጋፉ ታክሲ ለመጠቀም ቢገደዱም፣ በተቻላቸው አቅም ሁሉ ወገናቸውን ከመርዳትና ከማገልገል ተቆጥበው አያውቁም። በዚህ በኩል የጓደኛዬ የጋዜጠኛ አርአር ተስፋማያም ልጅ የሆነችው ኢየሩሳሌም በፅኑ ሕመም ታማ ወደ ውጭ አገር ሄዳ ሕክምና ካልተከታተለች በቀር ሕይወቷ አደጋ ላይ እንደሆነ ሃኪም ቢገልፅም ቤተሰቧ የሕክምናዋን ወጭ የሚሸፍን ጥሪት ስላልነበራቸው በጭንቅ ላይ ሳሉ ይህንን ባጋጣሚ የሰሙት ዶ/ር ነጋሶ ተሯሩጠው የሚያስፈልገውን ሁሉ በማሟላት ሕክምናዋን እንድትከታተል አድርገው፣ ዛሬ በፍፁም ጤንነት ከአባቷ ጋር አሜሪካ ውስጥ ትኖራለች።

በዚህም የተነሳ አር አያ የዶ/ር ነጋሶን ስም ሁሌም ከፍ እንዳደረገና እናዳመሰገነ ነው የኖረው። ምን እሱ ብቻ ! ኢየሩሳሌም እጅግ ጎበዝ ልጅ ስለሆነች ከዓመት ዓመት በትምሕርቷ የምታስመዘግበውን ከፍተኛ ውጤት በማየት እኔም ይህንን ባየሁና በሰማሁ ቁጥር ዶ/ር ነጋሶን አመሰግናለሁ። ዛሬ ላይ ሃዘኑ እንዴት አድርጓቸው ይሆን? ደውዬ እንዳልጠይቃቸው አልሰሙ እንደሆን ብዬ ሰጋሁና ተውኩት። እግዚአብሔር ለቤተሰቦቻቸውም ሆነ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናቱን ይስጣቸው!! የርሳቸውንም ነፍስ ይማርልን !!

ዶ/ር ነጋሶ የተወለዱት ጳጉሜ 3 ቀን 1943 ዓ.ም በድሮው የወለጋ ጠቅላይ ግዛት፣ በቄለም አውራጃ በደምቢዶሎ ከተማ ሲሆን፣ ይህ ፎቶ የአገራችን ፕ/ት ሳሉ በአንድ አጋጣሚ ተገናኝተን ለማስታወሻ የተነሳነው ነበር።

ቅዱስ ሃብት

 

Negasso Gidada

From Wikipedia, the free encyclopedia

3 COMMENTS

 1. በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ከነበሩት ታላላቅ ሰዎች መካከል አንዱ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በፋሲካ አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ ጉዳይ ሆኗል።

  Really?
  Who puts the tribal fiefdoms and so called constitution in Ethiopia?
  Who was the architect of kilil?
  Lest we forget, a false witness will go to hell.
  He died yesterday and you want to tell us he was hero today.

  RIP Gidada about a thousand to go. The miracle of Ethiopian God is always at work if I may add.

 2. ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
  Dear Kidus Habt;
  Have you ever ask your friend journalist Araya Tesfamariam if he ever thanks and appreciated all those who helped him when he beg for help during his dangerous life in India who helped him to come to America? Please ask your friend? will you? I really do not want to come up to the media, but please Neggasso might have a hand on it- Araya’s appreciating Negasso every second of his life for what Negasso did for him is not guaranteed to others who helped him after Negasso in his and his daughter very hard time in India where he was been torture, bitten, harrassed and protected him from being homeless with his daughter and also helped him to immigrate to the US where he is living now and ignore all those people helped him on his difficult time. Please stop here before going detail! I do not want to deal with such fellow any more!
  ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

 3. እንደዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ እፍረት ጠፋ ማለት ነዉ? የኢትዮጵያ ህዝብ ነጋሶን የሚወደዉ ስለበተነዉ ነዉ? ወይስ መለስ ይገደል የሚለዉን ሳያነብ በመፈረሙ ነዉ? ወይስ ኢትዮጵያን በነገድ ብትንትኗን ስላወጣት ነዉ? የእጁን ሳያገኝ አመለጠ በሰራዉ ስራ ይለበለብ ነበር፡አረ ትንሽ እፈሩ ሰዉን ከናንተ የባሰ ዶማ አድርጋችሁ አትዩት ማገናዘብ የሚችል ነዉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.