የማምቡክን ግጭት የሚያጣራ የምርመራ ቡድን ወደ አካባቢው መግባቱ ተነገረ

 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዳንጉር ወረዳ የተከሰተውን ግጭት የሚያጣራ የምርመራ ቡድን ዛሬ ወደ አካባቢው መግባቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፥ ግጭት የተከሰተበት የዳንጉር ወረዳ ማምቡክ ከተማና አካባቢው በፌደራልና ክልል የጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ውሏል።

ግጭቱ የተከሰተበት አካባቢ ዛሬ ማምሻውን እየተረጋጋ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሌሎች አንዳንድ የወረዳው ቀበሌዎች ዛሬ ረፋድ ላይ ተመሳሳይ ግጭት መከሰቱን ጠቁመው፥ አሁን ላይ የተጎዱ ሰዎችን እና የወደመውን ንብረት ትክክለኛ መጠን ለመግለጽ እንደሚቸገሩ አስታውቀዋል።

በነገው እለትም ትክክለኛውን የጉዳት መጠን ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንደሚያደርጉም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል በአካባቢው የተከሰተውን ችግር በጋራ ለመፍታት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ፥ የሁለቱ ክልል መንግስታት ዜጎችን ከጉዳት ለመጠበቅና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በጋራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ኤፍ ቢ ሲ

1 COMMENT

 1. This is bullshit: የማምቡክን ግጭት የሚያጣራ የምርመራ ቡድን ወደ አካባቢው መግባቱ ተነገረ

  These attacks happen for months or years.

  How many times does the dubious Abiy government intend to do that ?

  The Abiy government can not be trusted any more, and sending an investigation group is just a delaying tactic.

  The solution should be either,

  1. the Amara region takes this formerly Gojam province to ensure law and order or

  2. the Abiy government resigns, as it is incapable of ruling the country and ensuring law and order.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.