መተከል ላይ እየተጨፈጨፉ ስላሉ አማሮች… (ገብርዬ)

1) በቦታው ያላችሁ አማሮች ሰብሰብ ብላችሁ መመከት ይኖርባችኋል። መመከት ተፈጥሯዊ መብት ነው። ይህን መብታችሁን ተጠቀሙ። ራስን ከጥቃት መከላከል ወንጀል አይደለም።

2) የአማራ ልዩ ኃይል አማራውን የመታደግ ግዴታውን መወጣት አለበት። የአማራ ብሔራዊ መንግሥት አመራሮችም ለዚህ ተልዕኮ አመራር በአስቸኳይ ልትሰጡ ይገባል። ልዩ ኃይሉ ከጭፍጨፋው ጀርባ ያሉ የአካባቢው አመራሮችንም ማንቁርታቸውን ይዞ ለፍርድ ማቅረብ አለበት።

3) ለአካለ መጠን የደረሰ፤ ራስን ለመከላከል የአካልና የአዕምሮ ሁኔታው የሚፈቅድለት አማራ ሁሉ (ወንድም ሴትም) እንደሕዝብ የተደቀነብንን እልቂት ለመከላከል የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ አለበት። ፍትኅን ከገዳይ እንደመለመን ዓይነት መዋረድ የለም።

4) ወንድማችን የሺሀሳብ አበራ እንደሚለው«ፍትኅ የጉልበት ሎሌ ናት»። አንድ ወቅት አይሁዶች እንዲህ እንደእኛ የማንም ወበከንቱ ማላገጫ ነበሩ። ተደራጅተው ጉልበታቸውን ማፈርጠም ስለቻሉ ግን ዛሬ ላይ እንኳን እስራኤላዊ ዜጋን የእስራኤል ኤምባሲን አጥር እንኳን በሁለት ዓይኑ ደፍሮ የሚያይ የለም። ይህም የሆነው በትግላቸው ባስመዘገቡት ድል እንጂ በዕድል አይደለም። ዓለም ለደካሞች ቦታ የላትምና አማራ ሆይ መጠንከር ምርጫህ ሳይሆን ግዴታህ ነው።

5) ሙሾ ይሰለቻል። «እኒያ ነፍራቆች ለቅሶ ጀምሩ» የሚሉን በዝተዋል። ለቅሶ መናቅን እንጂ መከበርን አይሸምትም። ቆምጨጭ ማለት ብቻ ነው ያለን ምርጫ። ሞት እንደሆነ ለምደነዋል። የአማራ መሞት እኮ ዜና አይደለም። ሞት አዲሳችን አይደለም። እናም ቆምጨጭ እንበል! ሊገለን የሚመጣ ትርፍ ነፍስ የለውም። ገዳያችን ነፍሱ ብረት ለበስ አይደለችም። በቃ ቆምጨጭ ብለን እንመክት! መመከት ራስን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብት ነው። እኛ ገፍተን ሄደን ጡር እንሥራ እንጂ ደጃችን ድረስ ሊገለን የመጣን መመከት በሰውም በእግዜርም ኩነኔ የለውም! እናም ይህን ያህል ሰው ተገደለ ብለህ አትንገረኝ። አማራ ነኝ የሚል፤ የአማራ ጉዳይ ይገደኛል የሚል በየትኛውም ቅርፅና አድማስ ያለ አደረጃጀትም እየተጨፈጨፈ ያለው ወገናችን የሚፈልገው ድጋፍ ከንፈር መጠጣ አለመሆኑን መረዳት አለበት! ወገኔ የሚፈልገው ጨፍጫፊዎችን ልክ የሚያስገባለት ነው። ሕዝቤ የሚፈልገው ለጨፍጫፊዎቹ አመራር የሚሰጡትን የፊጥኝ አስሮ ለፍርድ የሚያቀርብለት ነው።

እጣፈንታችንን በራሳችን እጆች እንጽፋለን!

1 COMMENT

  1. I hate war and violence in any form or shape. Often, it is advisable to prevent war and conflict. The preventive strategy and measure differs based on reality on the ground. Does the same action would be appropriate? If it can prevent future war or violence I do not care wether proportional or draconian.
    Those people need to be protected or need to made able protect themselves.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.