“በፖለቲካውም ባይቻል፤ በስፖርቱ ዓለም የዘር ልዩነት እንዲጠፋ እንሻለን።” – ፍቅሩ ኪዳኔ

አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ፤ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኛ፣ ደራሲና የቀድሞ ዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዳይሬክተር፤ በቅርቡ ለህትመት ስላበቁት “የስፖርት ጨዋነት ምንጮች” መጽሐፍና በሸራተን አዲስ “የስፖርት ጨዋነት ምንጮች” የውይይት መድረክ ተሳታፊዎች በጋራ ስላስተላለፏቸው ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ ይናገራሉ።

2 COMMENTS

  1. አይ ወንድሜ ፍቅሩ የጥቁር ህዝብ ችግሩ የራሱን ጠልቶ በመጤ ነገር መስከሩ ነው። ዛሬ በአውሮፓና በሌሎቹ ሃገሮች ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው ምርጥ ተጫዋቾች በነጩ ህዝብ እየተሰደቡና እየተዘለፉ መጫወት አቅቷቸው በእምባ ሜዳውን ጥለው ሲወጡ፤ ዝንጀሮነትን ለማሳየት ሙዝ ሲወረወርባቸው ሌላም ሌላም እናያለን። የሚገርመው ግን የሃበሻው ኳስ አፍቃሪ በውጭ ሃገር ክለቦች የተለከፈና በሽንፈታቸው ቤት የሚያፈርስ፤ እምባ የሚረጭ መሆኑ የእኛን ተልካሻነት ያሳያል። በመሰረቱ ዓለም የተሰመረችው ነጩን አለም ለማገልገል ነው። በፓለቲካው፤ በኢኮኖሚው፤ በእስፓርቱ ሁሉም ነገር የተመቻቸው ለእነርሱ ነው። ያ የሆነው ደግሞ በሌላው ዓለም ህዝብ ቁማር በመጫወት ራሳቸውን በማበልጸጋቸው ነው። ዛሬ ኢራቅ፤ ሊቢያ፤ ሶሪያ… ነገ ደግሞ በሱዳንና በከባቢ ሃገሮች ላይ ጉልበት ያላቸው ሲያተራምሱን እኛም የእብድ ገላጋይን ተከትለን ወገናችን እየገደልንና እያፈናቀልን ሆ እንደምንል ያለፈና የአሁን ታሪካችን እማኝ ነው።
    በመሰረቱ ፓለቲካና ስፓርት አንድ ናቸው። አንድ ከሌላው የሚለየው በታጠቁት ትጥቅ ብቻ ነው፡ ሁለቱም ትርምስን ይወዳሉ። ሁለቱም ሙሰኞች ናቸው። ዛሬ ጉቦ ባለመስጠታቸው መጫወት ሲገባቸው ቁጭ ያሉ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ተጫዋቾች ስንቶች ናቸው? ፓለቲካ አፈኛና ጠበንጃ አንጋችን እንጂ አርቆ አሳቢን ታሳቢ አያደርግም። ስፓርትም እንዲሁ ነው። ግብግብን፤ ሳይጎዱ ወድቆ መንከባለልን። ያለተፈጸመውን በደል ተበደለኩ በማለት ሌላውን መክሰስን፤ ዳኝነትን መጋፋትን የመሳሰሉ ገጸ ባህሪያት አለው። በክልልና በጎጥ ወይም በሃይማኖት ዙሪያ ባይፋለሙ በቲፎዞዎች መካከል ፍትጊያ መኖሩና የሰው ህይወትም የተቀጠፈበት ጊዜ እንዳለ ታሪክ ያመላክታል። ለነገሩ በዘርና በጎጥ በተከለለቸው ከቁራሽ ተራፊ ኢትዮጵያ እንኳን በዘር፤ በቋንቋ፤በሃይማኖት ተከፋፍሎ መፈነካከት እንዳለ እያየን ነው። አይ ስፓርትና ፓለቲካ … ያው ናቸው። 22 ሰዎችን አስከትላ የምትነጥረው ቂሪላ ስፓርትን ለሰላምና ለበልጽግና ተምሳሌ ለማድረግ ፓለቲካውን ከስፓርቱ ለይቶ ማየት አይቻልም። በሃገርና በውጭ የምናየውም ይህኑ ሽኩቻ ነው። እውቁ ኢትዮጵያዊ ፍቅሩ ኪዳኔም ይህን ጉዳይ አሳምሮ ያውቃል።

  2. ጋሼ ፍቅሩ ኪዳኔ -ከካታንጋ ካምቦሎጆ እስከ ቺካጎ አሜሪካ ለሃገራችን ስፖርት ስለምትሰጠው ዘገባና ምክር አድናቂህ ነኝ:: ዛሬ ደግሞ የትውልድ ሃገራችን ብርቱ ችግር ዘረኝነትን ከፖለቲካው ሰፈር ከቤተመቅደሱ ሳይቀር መርገም የሆነብንን በስፖርቱ መድረክ መፋለምህን ላደንቅ ብቅ ብያለሁ:: የጥንቱ ነጸረገብረአብ ከአጼው መሪነት የይድነቃቸው መሪነት ይሻላል ብሎ ለአርባ ጅራፍ እንደበቃው ዛሬም ሳትፈራ የሃገራችን ቀውስ ፈጣሪና አባባሽ ዘረኞችን በያለንበት መፋለማችንን እንቀጥል:: እናት ኢትዮጲያ ተስፋዋ ይፈጸም!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.