በምዕራብ ጎንደር ተጠርጣሪዎችን ይዘው ለማሳለፍ የሞከሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል፤ ምርመራም ተጀምሮባቸዋ

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ቁጥር አንድ በሚባለው አካባቢ የብሔር ግጭት በመፍጠር ወንጀል፣ ተጠርጥረው የሚፈለጉ አምሥት ግለሰቦችን በመኪናቸው ሸራ አልብሰው ወደ መተማ ወረዳ ለማሻገር የሞከሩ አራት የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአካባቢው ኅብረተሰብ በቁጥጥር ሥር ውለው ለፖሊስ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ተወካይ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዓባይ አሻግሬ ለአብመድ እንዳስታወቁት በቁጥጥር ሥር የዋሉት የመከላከያ ሠራዊት አባላት በቋራ ወረዳ ቁጥር 4 ነፍስ ገበያ አካባቢ ሠላም በማስከበር ተግባር ላይ ለሚገኙ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ደመወዝ ለመክፈል ሄደው ከፍለው ሲመለሱ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ኮሎኔል አንገሶም አርአያ የ33ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አዛዥ፣ መጋቤ ሃምሳ አለቃ አባድር አብራሽ ሾፌር፣ አስር አለቃ ደጀን ቡልቶ የሒሳብ ባለሙያ እና ወታደር ሳምራዊት ገብረእግዚአብሔር የሒሳብ ባለሙያ መሆናቸውን ዋና ኢንስፔክተር ዓባይ ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሌሎች አምሥት በብሔር ግጭት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ሁለት ክላሽ፣ 322 ጥይት፣ 157 ሺህ 900 ብር፣ ዘጠኝ የክላሽ ካዝና፣ ሁለት የወገብ ትጥቅ እንደያዙ ለሥራ በሚገለገሉበት ተሽከርካሪ ደብቀው ወደ መተማ ወረዳ ጉባይ ቀበሌ ሲያጓጉዙ ነው ሚያዝያ 25 ቀን 2011ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 አካባቢ ሁሉም በኅብረተሰቡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡

ኅብረተሰቡ በተደራጀና ሥነ-ምግባር በተሞላበት አግባብ በሕግ ማስከበር ተግባር የተሠማሩ ሰዎች ሕግን ሲተላለፉ ሕግን ለማስከበር ያደረገው ተግባር የሚመሠገን መሆኑን የገለጹት ተወካይ ኃላፊው ‹‹በእርግጥ የአካባቢው ኅብረተሰብ ለሕግ መከበር ቁርጠኛ የሆነና የሰለጠነ ነው፤ ከዚህ በፊትም አምሥት ብሬን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለፖሊስ አስረክቧል፡፡ የደቦ ፍርድ የማይፈጽም ሕጋዊና ሕግ አስከባሪ ኅብረተሰብ ስላለንም ደስተኞች ነን›› ብለዋል፡፡

ድርጊቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትን የማወክል እንደሆነ ያስረዱት ዋና ኢንስፔክተር ዓብይ ‹‹የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድርጊቱ የግለሰቦች መሆኑን በመግለጽ በፖሊስ ምርመራ እንዲካሄድባቸው ፈቅዷል፤ ምርመራውም ተጀምሯል›› ነው ያሉት፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ኮሎኔል አንገሶም አርአያ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ሠላም ለማስከበር በሚደረገው ጥረት በተደጋጋሚ በመፈጸም ውስንነት በዞን ጥምር ኮሚቴ ሲገመገሙ እንደነበርም ተወካይ ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

አብመድ

3 COMMENTS

  1. ANGESOM ARAYA, the left over of Weyane cought in broad day light doing Weyanes dirty job.
    I hope his excellence Lemma Megersa will rip out the last roots of Weyanes from the Ethiopian miletry, until then Ethiopia won’t have peace, it’s just a simple math.

  2. አንበሶች የአገሬ ልጆች በርቱ፡፡ ስትደራጁ ፍትህን በራሳችሁ ጥረት ታረጋግጣላችሁ፡፡ ሌላው አሰደሳች ነገር በሰለጠነ ሁኔታ መሆኑ ነዉ፡፡ እንዲህ ነው አመራ ስልጣኔውን የሚያሳየው፡፡ እንደሌላው እንደ ከብት መንጋ አይነዳም፡፡ የሚሰራውን ያውቃል፡፡ በተረፈ መገንዘብ ያለባቸሁ ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ ከወያኒ መንግስት ጀምሮ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የላትም፡፡ ከ 2 ዓመት በፊት የነበረው የወያኔ ጉጀሌ ሚሊሻ አሁን ደግሞ በቅንጅት የኦነግና የህውሃት ሚሊሻዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ሀይል ሞትን እንጂ ሰላምን እነዳትጠብቅ፡፡ አማራን ሊያጠፋ የተሰማራ ሀይል ስለሆነ ምንጊዜም በንቃት መከታተል ያስፈልጋል፡፡ በመጨረሻ መፍትሄው መደራጀት፤መደራጀት አሁንም መደራጀት ብቻ ነው፡፡

  3. ብራቮ የጎነደር ህዝብ ይህ አይነቱ የህዝብ የነቃ ክትትል በሁሉም አከባቢ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡
    መከላከያ ሰራዊትም ውስጡን በደንብ መፈተሸና የማጥራት ስራም ውሎ ሳያድር ማከናወን አለበት፡፡ ሰው ህሊና ሲያጣ፣ በእብሪትና ሴጣናዊ በሆነ ነዋይ ሲመራ በህግ ህሊና እንዲገዛ ማድረግ ይገባል፡፡

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.