ዋና አላማዉን የሳተዉ የጤና ባለሙያወች ጥያቄ

ሰሞኑን ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎች የጤና ባለሙያወች ጥያቄ ማንሳታቸዉ ይታወሳል፡፡ ጥያቄያቸዉን በጥሞና ስከታተለዉ ቆይቻለዉ፡፡ አብዛኛዉ በሚባል ሁኔታ ከደሞዝ፤ ብሎም የተሻለ ኑሮ መኖርን እንዲሁም የሚከፈላቸዉ ከትምሀርት ቆይታቸዉ እና ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር ያልተመጣጠነ መሆኑን እና ጠቅለል ባለ ሁኔታ በራሳቸዉ የግል ዙሪያ ማተኮሩ ታዝቢያለዉ፡፡ የሃገሪቱ የጤና ሲስተም እንዲሁም አጠቃላይ ፖሊሲዉ እጅጉን ችግር ያለበት በፕሮፖጋንዳ ካብ የቆመ የጤና ፖሊሲ ነዉ ያለን፡፡ በእርግጥ በተወሰኑ ዘርፎች ለዉጥ መምጣቱን አይካድም፡፡ ነገር ግን አጠቃላይ ፖሊሲዉ ብሎም መሬት ላይ ወርደን ያለዉን ነገር በምናይበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ሪፎርም እንደሚያስፈለገዉ አያጠራጥርም፡፡ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ በዋነኛነት መሆን ያለበት ፖሊሲዉን በማሻሻል የራሳቸዉንም የህብረተሰቡንም የጤና ሁኔታ የሚቀይሩበት አካሄድን መምረጥ ነዉ፡፡ ጥያቄዉ ከተነሳ አይቀር ከደሞዝ እና ከኮስት ሸሪንግ በላይ መሄድ አለበት፡፡ ደሞዝ መጨመሩ ከባድ ላይሆን ይችላል ነገር ግን የሲስተሙ ወይም ያለን ፖሊሲ እስካልተቀየረ ድረስ ነገ በግሽበት ለሚበላ ገንዘብ ያን ያህል ለዉጥ አያመጣም፡፡ምናልባት ወጣት የጤና ባለሙያዎች የፖሊሲ ኦሬንቴሽን የሌላቸዉ ሊሆን ስለሚችል ጥያቄዉን እዛ ላይ ለማድረስ ሊቸገሩ እንደሚችሉ ብገነዘብም በሲስተሙ ዉስጥ ለረዥም ጊዜ የሰሩ ባለሙያወች ግን የጥቅማጥቅም እና የቤት አበል ብቻ ላይ አተኩረዉ ማንሳታቸዉ እንድታዘባቸዉ አድርጎኛል፡፡

አንድ ሁለት የፖሊሲ አቅጣጫዋች
———
1. የጤና ባለሙያወች ሀገሪቱ የጤና መድህን (Health insurance) ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲኖረዉ መወትወት ብሎም አማራጭ እና አዋጭ የጤና መድህን ፖሊሲ ለመንግስት በማቅረብ የህብረተሰቡን ጤና ማሻሻል፡፡ ለምሳሌ መንግስት ሁለት health insurance schemes አምጥቶ ነበር፡፡ 1) community-based health insurance (ለኢ-መደበኛ ሰራተኞች ለምሳሌ ለገበሬዎች፤ ለግል ሰራተኞች በየወሩ premium በመክፈል)፡፡ 2) Social health insurance (በመደበኛዉ ሴክተር ለሚሰሩ ሰራተኞች ከደሞዛቸዉ በመቁረጥ የሚሰጥ የጤና መድህን) ነዉ፡፡ መንግስት ለመደበኛ ሰራተኛዉ ብሎ ያመጣዉን የጤና መድህን አሰስካሁን ተግባራዊ አላደረገም፡፡ የ community based health insurance በመጠኑም ቢሆን እየተተገበረ ነዉ፡፡ ነገር ግን የዲዛይን፤ የፋይናንስንግ፤ የአገልግሎት አሰጣት ችግር ከመሰረቱ አለበት፡፡ በመሆኑም እኒህን ሁለት የጤና መድህን ፖሊሲወች ወይ ባግባቡ እንዲተገበሩ ማድረግ አለበለዚያ በሌላ ሲስተም መቀየር የህዝቡንም የጤና ባለሙያዉንም ኑሮ ያሻሽላል፡፡ ይህ ማለት አንድ ሰዉ በታመመ ጊዜ ንብረቱን አይሸጥም (financial risk ዉስጥ አይገባም)፡፡ ይህ የጤና መድህን ፖሊሲ ሲተገበር የጤና ባለሙያዉ ከመንግስት ጋር ስለ ክፍያ አከፋፈል፤ ስለ ሚሰሩበት ሰአት እና መሰል ጉዳዮች ከፍተኛ ድርድር ማድረግ እና የክፍያ ስርአቱን (physician remuneration) ደሞዝ ብቻ ሳይሆን mixed approach መጠቀም፡፡ ለምሳሌ salary and capitation or Salary and fee for service or something else፡፡ የጤና መድህኑ ምናልባት በመጠኑ ለግል ሴክተሩ ክፍት በማድረግ የጤና ባለሙያዎች እና ባለሃብቶች በቡድን ሁነዉ የራሳቸዉን ድርጅት በመክፈት የጤና አገልግሎት ወይም የጤና መድህን እንዲሰጡ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከዛም አልፎ የግል ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸዉ የጤና መድህን ሽፋን ሲለሚገቡላቸዉ ለጤና ባለሙያወች ተጨማሪ የገቢ ማግኛ ዘዴ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ የ MK ካምፓኒ 2 ሺህ ሰራተኛች ቢኖሩት በቡድን ከተደራጁ የጤና ባለሙያወች የጤና መድህን ይገዛላቸዋል ወይም 4 እና 5 ሃኪም ለካምፓኒዉ በትርፍ ሰአቱ እንዲሰራ ይቀጥራል ማለት ነዉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የጤና ባለሙዎች ከሆስፒታል አስተዳደር እና ማኔጅመንት ጀምሮ እስከ መድሃኒት አስመጭ ድረስ ሪፎርም እንዲደረግ መደራደር እና በሲስተሙ ዉስጥ ተገቢዉ ደምጽ እንዲኖራቸዉ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡

2. ከመንግስት በኩል የጤና መድህን በጠቅላላ በሀገሪቱ ግዴታ ሁኖ ከቀን ሰራተኛ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ሽፋን የሚያገኙበትን ፖሊሲ/ስትራቲጅ ማምጣት አለበት፡፡ social health insurance through premiums የማይሰራ ከሆነ ሌላ አማራጭ መፈለግ ለምሳሌ health insurance through general taxation (እኛ ሀገር ላይ አያዋጣም) ወይም ደግሞ mixed (opening the insurance system to both the public and the private sectors)፡፡ መንግስት የጤና ባለሙያወችን ክፍያ ሰርአት ሲያበጅ የጤና ባለሙያወች ለክፍያ ስርአቱ የሚሰጡት ግበረ መልስ (behavioral response) ምን ሊሆን ይችላል ብሎ ማጥናት ይጠበቅበታል፡፡ ለምሳሌ በደሞዝ ብቻ ሲሰሩ ሰራተኞች የሚጠበቅባቸዉን ያህል ያለመስራት ይታያል (lower level of service delivery). Fee for service (በእያንዳንዱ ባከሙት ሰዉ ልክ ተሰልቶ የሚከፈል) ለምሳሌ የሰራተኞችን የስራ ትጋት (service production) ከ 20 እስከ 40 በመቶ እንደሚጨምረዉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የዚህ አካሄድ አንዱ ችግሩ ከመጠን በላይ መስራት (over delivery of services) ስለሚኖር ለጤና ባለሙያዉ የሚከፈለዉ ክፍያ ስለሚበዛ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት ዋጋ ይንራል ብሎም ሀኪሞች ብዛት ለማከም ከሚኖራቸዉ ጉጉት የተነሳ በሽተኞችን ጊዜ ወስደዉ በትክክል consult ላያደርጉ ይችላሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ከከፍተኛ ክፍያ ጋር ተያይዞ ኢኮኖሚስቶች እንደሚሉት ሰወች ከ work ወደ leisure time ሊያተኩሩ ይችላሉ፡፡ ያ ማለት ሰወች ትቂት ሰርተዉ ብዙ ገንዘብ ካገኙ ቀሪ ሰፊ ሰአታቸዋን ለመዝናኛ ጊዜ ያዉሉታል፡፡ According to the economists’, leisure is a normal good where people want to consume more of it (income effect ይይባላል)፡፡ በእርግጥ ይሄ ሁሌም እዉነት አይሆንም ለምሳሌ አንዳንዱ ሰዉ ሰርቶ ብዙ ብር የሚያገኝ ከሆነ ብዙ ሰአት ይሰራል (substitution effect) የመዝናኛ ሰአቱን ከመጨመር ይልቅ የሚሰራበትን ሰአት በመጨመር ገቢ ይሰበስባል፡፡ እነ አሜሪካ እና አዉሮፓዉያን የሚያጋጥማቸዉ የሀኪሞች እጥረት በዚህ ምክንያት ነዉ፡፡ የሀኪም ቁጥር ማነሱ ብቻ ሳይሆን ሀኪሞች ለ leisure time የሚመድቡት ሰአት መብዛቱ ነዉ፡፡ ኢትዮጵያ ይሄን ታሳቤ ያደረገ ቅይጥ የክፍያ ስረአት ለምሳሌ salary with capitation or fee for service ዘዴን በመጠቀም ሃኪሞችንም በመጥቀም ህብረተሰቡንም የተሻለ ሰርቪስ እንዲያገኝ ማድረግ ይቻላል፡፡መንግስት ከዚህ በተጨማሪ ጠንካራ ሪጉሌሽን ሊኖረዉ ይገባል፡፡ በዚህ መልኩ አንደኛ ዜጎች ለጤና የሚያወጡት ገንዝብ (out of pocket fee) ከ 45 ፐርሰነት በላይ ደርሷል፡፡ ይሄን ወደ 30 እና 20 በመቶ ለማዉረድ ታርጌት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሁለተኛ የጤና ባለሙያወች ባልተጋነነ መልኩ ሌላዉ ስራተኛ ከሚያገኘዉ አማካኝ ወርሃዊ ገቢ ከፍ ያለ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ ሶስተኛ ሀገሪቱ አሁን ላይ ለጤና የምታወጣዉ ከአመታዊ የምርት መጠኗ ወደ 5 በመቶ እየደረሰ በመሆኑ እነዚህን ፖሊሲዎች በመተግበር የመንግስት ወጭን መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ባጠቃላይ ግን ህበረተሰቡ መሬቱን ሸጦ የሚታከም ከሆነ ሀገሪቱ ከድህነት አዘቅት ስለማትወጣ የጤና ፖሊሲያች በእጅጉ መቀየር አለበት ሃኪሞችም ጥያቄዉን ከደሞዝ በላይ በመዉሰድ ከራሳቸዉ አልፈዉ ለህብረተሰቡ መታገል አለባቸዉ፡፡

ይህ ግን በአንድ አመት የሚሰራ ስራ አይደለም፡፡ ብዙ አመታትን የሚፈልግ ስራ መሆኑን መገንዘብ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ሲስተም ነዉ የሚለወጠዉ፡፡ከዛሬ ጀምሮ መታገል ግን ተገቢ ነዉ፡፡ Build a system/ an institution that favors you and the people. መልሱን ምታገኙት እዚህ ላይ ነዉ፡፡

ሚክይ አምሃራ

1 COMMENT

  1. የጤና ጥበቃ ባለሞያዎች ጥያቄ እንደማንኛውም የሞያ ማህበር ጥያቄ መለየት የለበትም ።አንድ የሞያ ማህበር የአባሎቻቸውን ጥቅም ለማስከበር ጉዳትን ለማስቀነስ ፣የስራ ሂደትን አግባብ ባለው ከህብረተሰቡ ሂደትና ደረጃ አገናዝቦ መጠየቅና መብትን ማስከበር ነው። የኢትዮጵያን የጤና ጥበቃን ይዞታ ከሌላው አለም በተለይ የአሁኑን የአውሮፓንና የአሜሪካን ይዞታ ማመላከት ወይም አወዳድሮ ይሄ ነው ለማለት ፣በአሁኑ ይዘቱ ፈጽሞ አይቻልም ።ጠቃሚውና ከታቀደም የሰለጠኑት ሐገራት በጅምሩ እንዴት አደረጉት የሚባለውን መቅሰም ይቻል ይሆናል።ለዚህም የህብረተሰቡን እድገትና የታሪካው ሂደቱን ማገናዘብ ተገቢ ነው።
    የጤና መድህን እንዴት ይጀመራል የሚለው ጥያቄ እንደኢትዮጵያ ባለው ሐገር ለብዙ ጊዜ ፈር ለቆ ለተመሰቃቀለ ሂደት መሰረታዊ ለውጥ ሂደት መደረግ እንዳለበት አነጋጋሪ አይደለም። በተወሰነ የጤና ሞያተኛው እንደ ንግድ የገንዘብ ምንጭ የሚታይበት ሁኔታ ሲሆን ይህደግሞ የአብዛኛውን የጤና ባለሞያዎች ግንዛቤ አይደለም።
    ወደ ዋናው ነጥብ ስንመጣ። የደሞዝ ጭማሪና ጥቅማ ጥቅም ጥየቃ ባለንበት የኢትዮ ኑሮ ሁኔታ አስገራሚ የሚሆንበት ምክንያት ተገቢ አይደለም።የገንዘብ ሐይል ውድቀት በየወሩ በሚመዘገብበት ሐገር፣መሰረታዊ የሰርቶ መኖር ፣ቤት መከራየት፣የቀን ተቀን ወጪን መሸፈን፣ቤተሰብ የመቆርቆር ብሎም ቤተሰብን መርዳት በሰፊው ህዝብ ያልተቻለበት ዘመን ፣የደሞዝ ጭማሪ መጠየቅ አሰገራሚነቱ ለምን እንደሆነ በራሱ አስገራሚ ነው። አስስገራሚ መሆን የነበረበት ኢትዮጵያን የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እሳቤው ነው።ጠግቦ በስነ ሥርአት የማኖርን ህብረተሰብ የዓለምን ሃብታም ለህክምና ለመሰብሰብ ቀርቶ ተራውንም ቱሪስት በስነስርዓቱ ማስተናገድ ያልተቻለበት ሐገር ነው።
    የጤና ባለሞያዎች ከሌላው ሞያ ልዩ አይደሉም።እንደማንኛውም ሞያ ይሄንን መርጠው ለመኖር ይገለገሉበታል። በእርግጥ በሕይወት ላይ ያላቸው ሐላፊነት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ከገቢ ጋር የተያያዘውን የመኖር ፍላጎት ግንዛቤ አለማስገባት ጥያቄውን አያሳንሰውም። ለምን ጭማሪ አስፈለገ ብለው የተዘረዘሩትን ምክንያቶች ወደጎን ትቶ ጭማሪ ፍራንክ ብቻ ፈለጉ ብሎ ጥያቄውን ማራከስ ፣የችግሩን ምንጭ ከአሁን ይልቅ ለተነጎዲያ ማስተላለፍ ነው።
    ይህ የጤና ጥበቃ ክፍል አንዱ ችግር ነው። ለሁሉም መሰረታዊ ለውጥ ከሌለ መልስ እንደማይኖር ቢታወቅም ፣የሚመጡ ጥያቄዎችን በጊዜው መመለስ ግን ግዳጅ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.