የአማራ ክልልን ሰላምና ደህንነት ሙሉ በሙሉ በክልሉ የጸጥታ ሀይል ለማስጠበቅ እየተሰራ መሆኑን ጀነራል አሳምነው ጽጌ ተናገሩ፡

ዛሬ ሶስቱ የመንግስት አካላት ባካሄዱት የምክክር መድረክ ላይ የአማራ ክልል ህዝብ ሰላም እና ደህንነት በአስተማማኝ መልኩ እንዲጠበቅ የጸጥታ መዋቅሩ ሰፊ ስራ መስራት እንዳለበት ተነስቷል፡፡

በዚህም የክልሉ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ጀነራል አሳምነው ጽጌ የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማስከበር የክልሉን የጸጥታ ሀይል የማጠናከር ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥ የክልሉን ሰላም ሙሉ በሙሉ በክልሉ የጸጥታ ሀይል ለማስጠበቅ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፌደራል የጸጥታ ሀይል ቁጥጥር ስር የነበረ መሆኑን የገለጹት ጀነራል አሳምነው ከዛሬ ጀምሮ ግን የክልሉ የጸጥታ ሀይል ገብቶ ከፌደራል ሀይል ጋር በጋራ መስራት ጀምሯል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ሁሉንም የክልሉ አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በክልሉ መንግስት የጸጥታ መዋቅር ስር በማድረግ ህዝቡ የሚፈልገውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እየተሰራ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው ተናገረዋል፡፡
ውጤታማ ስራ ለመስራትም ወጣቱ ከክልሉ የጸጥታ ሀይል ጎን በመሰለፍ እና ምክንያታዊ በመሆን ለህግ የበላይነት መረጋገጥ አጋዥ እንዲሆን ጀነራል አሳምነው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Amhara Communications

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.