የብጹዕ ዶክተር አቡነ ገሪማ የቀብር ስነ-ስርዓት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ዛሬ ተፈፅሟል

በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ሊቃነ ጳጳሳት እና ቤተሰቦቻቸው ተገኝተዋል።

ብጹዕ ዶክተር አቡነ ገሪማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ለረጅም ዓመታት በውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዋና ጸሀፊነት እና በአፍሪካ እና በዓለም አብያተ ክርስቲያናት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይም አገልግለዋል።

ብፁዕ አቡነ ገሪማ በባልቻ ሆስፒታል በህክምና ሲርዱ ቆይተው ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

አብመድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.