መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት ብቻም ሳይሆን አቅምም እንዳለው ተገለጸ

መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት ብቻም ሳይሆን አቅምም እንዳለው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን የገለጹት በሁለተኛው የአዲስ ወግ የውይይት መድረክ ላይ ነው

በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ሕጋዊ የሕግ አስከባሪ ነው ለዚህም የሚያስከብርበት የሕግ አውድና የሚያስፈፅምበት ጠንካራ ተቋማት መኖራቸው የአመራሩን የሕግ የበላይነትን ማክበር ወይም በሕግ የመገዛት አዝማሚያ አመላካቾች መሆናቸውን አስረድተዋል።

መንግስት የዜጎች ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ፈጣን ምላሽ እየሰጠ አይደለም በማለት ከተሳታፊዎች ለተነሳው ጥያቄም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከማንም በላይ መንግስት ትዕግስተኛ መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነት ብቻም ሳይሆን አቅምም እንዳለው አስረድተዋል።

ምንጭ:-ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.