የብሄራዊ ባንክ ገዥ ኢትዮጵያ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን ለመጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ አይደለችም አሉ

ኢትዮጵያ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን እንድትጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ እንደማትገኝ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ዋና ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አስታወቁ።

ዶክተር ይናገር ደሴ በተያዘው ዓመትም ሀገሪቱ በቂ ሊባል የሚችል የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዳላት ገልጸዋል።

የዕለት ተዕለቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚመራው ከወጪ ንግድ፣ ከብድርና እርዳታ፣ ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና ከዳያስፖራው በሀዋላ ከሚላክ የውጭ ምንዛሬ መሆኑንም አስታውሰዋል።

በየጊዜው የሚከፈሉ የውጭ ዕዳ ክፍያዎች፣ ለግል ዘርፉ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ ለነዳጅና ለመድሐኒት ግዥና ለመሳሰሉት ወጪዎችም በዚሁ እንደሚሸፈኑ ተናግረዋል።

ዶክተር ይናገር አንድ ሀገር የውጭ ምንዛሬን በመጠባበቂያነት የምታስቀምጠው ችግር ሲገጥማት አውጥታ ለመጠቀም እንጂ የዕለት ተዕለት ኢኮኖሚውን ለመምራት አለመሆኑንም አብራርተዋል።

በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ከላይ የተጠቀሱት የውጭ ምንዛሬ ምንጮች ያልተቋረጡ በመሆኑ የመጠባበቂያ ክምችት ለመጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ ሀገሪቷ ያለመግባቷን ገልጸዋል።

በተያዘው ዓመትም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ምንጮች የተሻለ የውጭ ምንዛሬ በመገኘቱ ከባለፉት ዓመታት በተሻለ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያዋ ክምችት መኖሩንም አረጋግጠዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች አምራች ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን ያህን የውጭ ምንዛሬ ማቅረብ ባይችልም ኢኮኖሚውን አሁን ባለበት ሁኔታ ማስቀጠል የሚያስችል በቂ የውጭ ምንዛሬም አለ ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት የተቀዛቀዘውን የወጪ ንግድ ማሳደግ ግን ዋነኛው የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት የሚያስችል በመሆኑ በተለይ በግብርናው ዘርፍ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ምንጭ፦ኢዜአ

1 COMMENT

 1. ” የብሄራዊ ባንክ ገዥ ኢትዮጵያ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችቷን ለመጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ ውስጥ አይደለችም አሉ ”

  What does this mean: የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ?

  Why does the country need foreign currencies (currencies of the enemy like USD, Euro and Pound) ?

  You guys need to think outside the box.

  Our goal should be to replace the present global financial system with another. The BRICS countries are working on that project for years.
  The present USA imposed global financial system, where the USD is the dominant currency for international trade, is highly anti-Ethiopian and anti-African, and needs to be abolished ASAP !

  We need to stop using ferenji currencies (USD, Euro & Pound) for,

  1. international trade

  2. international loans

  Also, we need to stop taking orders from ferenji controlled institutions like,

  1. IMF

  2. World Bank

  3. Wall Street and

  4. Ferenji governments
  .

  The present Euro-centric global order has to go ASAP !

  To hell with Euro-centric international organizations like IMF, World Bank, Wall Street, UNO and company !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.