የእነ አዳነች አበቤ አፓርታይዳዊ አስተሳሰብ እና ክሹፍ መረጃቸው (ጌታቸው ሽፈራው)

የእነ አዳነች አበቤ አፓርታይዳዊ አስተሳሰብ እና ክሹፍ መረጃቸው

( “ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ቅርንጫፎች (የፌደራል ተቋማት) ኃላፊዎች ኦሮሞ መሆን አለባቸው”)

የገቢዎችና ጉምሩክ ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ቢቢሲ ላይ ቀርበው ስለተቋማቸው ለማስተባበል ጥረዋል። ይሁንና ሌላ ተጨማሪ ስህተት ፈፅመዋል። ሕዝብ አያውቅም ብለው አሳሳች መረጃዎችን ተናግረዋል። ከእነዚህ መካከል አንደኛው “አብዛኛው የጉሙሩክ ቅርንጫፎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ነው ያሉት ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሞጆ፣ አዳማ፣ ጅማና ሞያሌ የፌደራል ጉሙሩክ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች በመኖራቸው በነዚህ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የክልሉን ቋንቋና ባህል የሚያውቅ አመራር መመደቡን አረጋግጠዋል።” ሲል ቢቢሲ ዘግቧል። ይህ ሀተታ ሀሰትም እውነትም አለበት። እውነታው አሥራት ላይ እንደተነገረው አብዛኛዎቹ የጉምሩክ ኃላፊዎች በኦሮሞዎች የተያዙ መሆኑ ነው። ወይዘሮ አዳነች ይህን ለማስተባበል ሲባል አብዛኛዎቹ ቅርንጫፎች ኦሮሚያ ውስጥ ስለሚገኙ ነው ብለዋል። አብዛኛዎቹ ቅርንጫፎች ኦሮሚያ ውስጥ ስለሆኑ ነው ያሉት የአመራሩን ስብጥር ማስተባበል ስለማይችሉ ነው። ይህ አደባባይ የወጣ ሀቅ ሆነባቸው። ስህተቱ ግን ብዙ ነው። ሁለቱን ብቻ ልጥቀስ።

1) ገቢዎችና ጉምሩክ የፌደራል ተቋም ነው። የፌደራል ተቋም ደግሞ የሚሰራው በኦሮምኛ ሳይሆን በአማርኛ ነው። የሚቀጥረው ቅርንጫፉ የተከፈተበት አካባቢ የተወለደን ሳይሆን የትኛውንም ኢትዮጵያዊ ነው። ቅርንጫፎቹ የተከፈቱት ለኦሮሚያ ሲባል ሳይሆን ለኢትዮጵያ ያስፈልጋሉ ተብለው ነው። አሰራሩም ኦሮሚያ ላይ ኦሮሞ ብቻ መመደብ አለበት አይለም። ይህ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ከሕወሓት የተረከቡትን ተቋም ወደ ኦዴፓ ማዞራቸውን ማስተባበል ስለማይችሉ ያቀረቡት ውሃ የማይቋጥርና የማይረባ መልስ ነው። ከመልሳቸው ስህተትነት ባሻገር ግን በየቦታው ኦሮሞ መድበው ሲተቹ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ የፌደራል ተቋማት ውስጥ ከኦሮሞ ውጭ ሌላ ሊመደብ አይችልም ማለት የለየለት አፓርታይዳዊ አመለካከት ነው። ሌላ ሊባል አይችልም!

2ኛ) ኃላፊዎቹ የአካባቢውን ቋንቋ ባገናዘበ መልኩ ቢቀጠሩ ኖሮ በርካታ ኦሮሞዎች በሌሎች ቅርንጫፎች በኃላፊነት ባልተቀመጡ ነበር። ከመቼ ወዲህ ነው ጅቡቲ ኦሮምኛ መናገር የጀመረችው? የጅቡቲ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ኦሮሞ አይደሉም እንዴ? ረዳታቸውስ ምንድን ናቸው? የጋላፊ ስራ አስኪያጅ ገላን ሰበቃ በዳኒ አፋር ሆነው ነው የተመደቡት? ኦሮሞ አይሉም እንዴ? ምክትላቸው ከበደ ቤኛ በደዳዳስ አፋር ሆነው ስማቸውን ወደ ኦሮሞ ስም ቀይረው ነው ኃላፊ የሆኑት ሊሉን ነው? የሀዋሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ፍቃዱ ወልደሰንበት ጉዳ ኦሮሞ አይደሉም እንዴ? ወይዘሮ አዳነች አበቤ ባሉት የስህተት አመክንዮ መሰረት ሲዳማ ወይስ ወላይታ ጠፍቶ ነው? ኦሮሚያ ውስጥ ከኦሮሞ ውጭ ኃላፊ መሆን አይችልም። ሌላ ቦታ ግን ኦሮሞ ኃላፊ መሆን ይችላል ከተባለ ደግሞ አስተሳሰቡ ከአፓርታይድነትም በላይ ነው። የቅኝ ግዛት አይነት መሆኑ ነው።

ሌላኛው የወይዘሮ አዳነች አበቤ የስህተትና ማወናበጃ መረጃ “በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ በነዚህ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች አብዛኞቹ ምክትል ኃላፊዎች የሌላ ብሔር ተወላጆች ናቸው።” የሚል ነው። ወይዘሮ አዳነች ለቢቢሲ ይህን መረጃ ሲሰጡ እየፈፀሙ ያለውን አፓርታይዳዊ አሰራር በአመክንዮ ማሸነፍ ስላልቻሉ የሀሰት ማስረጃ ማቅረብ አዋጭ ሆኖ ሳያገኙት አልቀረም። ነገር ግን አያዋጣም። መረጃው የሚለው ከወይዘሮ አዳነች የተውሸለሸለ መልስ ተቃራኒውን ነው፣ እውነቱ ሌላ ነው። ወይዘሮ አዳነች ኃላፊዎቹ የአካባቢውን ቋንቋ የሚችሉ መሆን ስላለባቸው እንደተመደቡ ቢገልፁም ይህ ሀሰት መሆኑን አፋር፣ ጅቡቲ፣ ሀዋሳ የተመደቡት ዋና ስራ አስኪያጆች ኦሮሞ መሆናቸውን ስናይ ለቢቢሲ የሰጡትን መረጃ ክሹፍ ያደርገዋል። ወይዘሮ አዳነች አበቤ ታዲያ በዚህ ሀሰት አልተመለሱም። ኦሮሚያ ውስጥ ባሉት ቅርንጫፎች ምክትሎቹ የሌላ ብሔር ናቸው ብለዋል። ይህኛውም ሌላኛው ክሹፍ መረጃ ነው። ሀሰት ነው። ለምሳሌ ያህል ናዝሬት ላይ አስቴር አዱኛ ምክትል ናቸው። ሞጆ ላይ ግርማ በንቲ ምክትል ናቸው። ኦሮሞ ናቸው። በሌሎቹም ተመሳሳይ ነው።

ወይዘሮ አዳነች አበቤ ዝም ቢሉ ይሻላቸው ነበር። የመጀመርያው ነገር ኦሮሚያ ውስጥ ያሉ የፌደራል መስርያ ቤቶችን ከኦሮሞ ውጭ አይመራቸውም ማለት የለየለት አፓርታይዳዊ አስተሳሰብ ነው። እነ አዳነችን የመሰሉ ብሔርተኞች አዲስ አበባም የኦሮሚያ ነች እያሉ ነው። በዚህ ሰበብ ኦሮሚያ ክልል የሚገኙት ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ውስጥ ያሉትን የፌደራል ተቋማትንም ሌላ ብሔር ድርሽ አይልባቸውም ሊሉን ነው። ቤተ መንግስቱም እነሱ በስግብግብነት “ፊንፊኔ ኬኛ” ከሚሏት አዲስ አበባ ውጭ ቅርንጫፍም ምንም የለውምና ከኦሮሞ ውጭ ማንም ወደ ቤተ መንግስት መግባት አይቻለውም ማለት ነው። እንደ አዳነች አበቤ የዛሬ አፓርታይዳዊ አስተሳሰብ ከሆነማ ከአሁን በኋላ ኦሮሞ ብቻ ነው “ስዩመ እግዚያብሔር”

ሌላው ግን በምክትል ያሉት የሌላ ብሔር ተወላጆች ናቸው የሚለውና የአካባቢውን ቋንቋ በመቻል ነው የሚለውም የሀሰት መሆኑን ተመልከተናል። ከዚህ ባሻገር ግን ብዙ ሰራተኛ ቅሬታ አላቀረበም የሚል መረጃውም በሀሰት ተሰጥቷል። ይህ የለየለት ውሸት ነው። ከ600 የማያንሱ ሰራተኞች ቅሬታ አቅርበዋል። ቅሬታው የተወሰኑ ሰዎች ነው የሚባለውም የአፓርታይዳዊ አሰራርን መሸፈን ካለመቻል የመጣ የጭንቀትና የድርቅብዬ መረጃ እንጅ በርካቶች ለተቋሙ ቅሬታ አቅርበው። የተወሰኑት ብቻ “ቅሬታው ተቀባይነት አግኝቷል” ሲባሉ በርካቶች አላገኘም ተብለዋል። አዳነች የሚሉት ሌላ እውነት ሌላ ነው።

በእርግጥ ወይዘሮ አዳነች አበቤ ከእነ ስህተቱ አመለካከታቸው አንድ ሀቅ አምነዋል። አብዛኛዎቹ የተቋሙ ቅርንጫፎች ኦሮሚያ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል። በዚህም አላበቁም። ኃላፊ የሚሆኑትም የአካባቢውን ቋንቋና ባህል የሚያውቁ ናቸው ብለዋል። በግልፅ ኦሮሞዎች ማለት ነው። በዚህ መረጃቸው አብዛኛዎቹ ኃላፊዎች እነማን እንደሆኑ ሀቅን ለማስተባበል ሲለፉ ነግረውናል።

6 COMMENTS

 1. Betam yemigerimewu oromiya wust sra lemeketer ke kebele yedigaf debdabe titeyekalek ye digaf debdabewu lay zerik tekotro yitsafal ehe malet oromigna kuankua menager bichawun beki ayadergikim

 2. በክልሎች ያሉ የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች የክልሎችን የሥራ ቋንቋ ወደ ጎን በመተው በአማርኛ ይሰራሉ የሚለውን የሀገሪቱ ህገመንግስት አንቀፅ ብትነግረን ጎበዝ!!! ፈልገን አጣን።
  ግን ማወቅ ያለብህ በኦሮሚያ ውስጥ የ FDRE ህገመንግስት እስካለ ድረስ ለመስራት A/Oromoo is mandatory!

 3. ወሬው የተጻፈው በአማርኛ በመሆኑ እንደ ገመዳ በተውሶ ቋንቋ አልንተባተብም። ይሁን እንጂ እንደ ገመዳ ያሉት የመከራ ክምር አምራቾች ራሳቸውን በውጭ አስጠግተው በሰላም አብሮ ለዘመናት የኖረን ሰው ሲያተራምሱ ማየት ያናድዳል። ጠባቡ የኦሮሞ የፓለቲካ እይታ “ኦሮሞን ለኦሮሞዎች” ይለናል። አለም ወደ ተባለቀ ውህደት ገብታ እያለ የኦሮሞ ተገንጣይ አቀንቃኞች እንዳልተማረ ከብት እረኛ ዛሬም አጎዛ እንደለበሱ ናቸው። የሚያስቡት፤ የሚጨፍሩበት፤ ወገኔ ነው የሚሉት እንደ ጥንቱ ፊውዳላዊ አገዛዝ ዘሩ ተቆጥሮ ነው። በመሰረቱ በአንዲ ሃገር ላይ አንድ አግልሎ ሌላውን የሚጠቅም የአፓርታይድ አሰራር የተጀመረው በሻቢያና በወያኔ ነው። የኦሮሞ የፓለቲካ አቅራሪዎችም የዚሁ እድፋም ፓለቲካ እይታ ተካፋዮች ናቸው።
  የእነ አዳነት አበቤ የፓለቲካ እይታም ጭፍን እንዲሆን ያደረገው የዚሁ የእኛን በእኛ የሚለው የፓለቲካ ዘይቤ ነው። የክልል ፓለቲካ አሳፋሪ ፓለቲካ ነው። በግድ ቋንቋየን ልመዱ እኔን ምስሉ ማለትም ጭፍንነት ነው። እኔ ኦሮሞ ነኝ የሚለው ወገን ለምን ሃገራዊ፤ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ እይታ እንደማይኖረው ሊገባኝ አይችልም። አሁን ማን ይሙት በሃበሻው ምድር እኔ ንጽህ ኦሮም፤ ትግራ ፤ አማራ ወይም ሌላ ዘር ነኝ ብሎ የሚቆምና በሳይንሳዊ መንገድ ይህኑ ነገር የሚያመሳክር አለ? መልሱ የለም ነው። የፓለቲካ ቱልቱላ ለመንፋት ለአማራ ህዝብ ፤ ለኦሮሞ ህዝብ ፤ ለትግራይ ህዝብ ወዘተ ቁሜአለሁ እያለን በስሙ ለመነገድ ካልሆነ በስተቀር ህዝባችን ዝብርቅ ነው። ቋንቋም መግባቢያ እንጂ ወያኔና ሻቢያ እንደሚሉት ጨቋኝ አይደለም። እንደ ገመዳ ያሉት የውጭ አፍቃሪዎችና ዘረኛ የፓለቲካ አሽቃባጮች በእንግሊዝኛ ቋንቋ ምላሽ የሚሰጡት አማርኛ ጠፍቷቸው ሳይሆን በቋንቋው ላይ ካላቸው ጥላቻ የተነሳ ነው። በአለማችን ላይ ቋንቋ ሰዎችን ጨቁኖአል ከተባለ እንግሊዝኛ ቀዳሚው ነው። እንግሊዞች ያለኮሱት እሳት የለምና! ዛሬ በህንድ/ በፓኪስታን/በኢራቅና በየመን በእስራኤልና በፓለስታየን ያለው እሳት እነርሱ ከዘመናት በፊት የለኮሱት ነው። ግን የውጭ ናፋቂው፤ ጥቁር ቆዳውን ፍቆ ነጭ መሆን ለሚሻው አማርኛ የጨቋኞች የጡት ቆራጮች ቋንቋ ነው። ኦሮምኛ ደግሞ የተጨቆኑ ሰዎች ቋንቋ። አታድርስ ነው። በዚህ የፓለቲካ ውስልትና የሚያተርፍ ማንም የለም። እድሜ ለወያኔና ለሻቢያ ሃገራችንን አፈራርሰው ዛሬ ላለችበት አብቅተዋታል። ተማሪው በተመደበበት ሂዶ የማይማርባት ሃገር፤ ለዘመናት የኖረው ኗሪ ዘሩ ተቆጥሮ ክክልሌ ውጡ የሚባልባት ምድር፤ ሁሉን የሚያግባባ የራሱ ፊደል ያለው የሃገሪቱ ቋንቋ እያለ ለዘመናት ታፍኖ ወያኔ ለራሱ የመኖሪያ ብልሃት ሁሉም በየጎጡ ባንዲራ አውለብላቢ በማድረጉ ዛሬ ሰው ከሰው የማይግባባበት ሃገር ተፈጥራለች። ኦሮምኛ ካልተናገርክ ሥራ የለም። ቀበሌ ዘርህን ቆጥሮ አንተ/አንቺ ኦሮሞ አይደለህም/ሽም በዚህ ቦታ የመስራት መብት የለህም/ሽም የሚልባት ይህች ምድር ትቅርብኝ። የገቢዎችና ጉምሩክ ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ኦሮሞዎችን በዙሪያዋ ማሰባሰቧ ከወያኔ የተማረቸው የዘረፋ ስልት ነው። ያው በጊዜው እርሷና በጎኗ የተሰለፉት ሁሉ ሰካራም እንደረገጠው ጣሳ በወቅቱ ይረጋገጣሉ። የሃገሪቱ የዘር ፓለቲካ ታሪክ ያሳየን ይህኑ ነው። እስከዛው በሌላው ደም/ በሌላው መፈናቀል እና ሞት ኪሳቹሁን አሙቁ። ኦሮሞነት የሚጣፍጠው ሲጋሩት ነው። የተናጠል የእኔ ብቻ ፓለቲካ በአፍንጫየ ይውጣ። እንደ ገመዳ ያሉት ወስላቶች የሚያንጸባርቁት ሃሳብ ምድር ላይ ያለውን ሳይሆን የቀን ህልማቸውን ነው። ቆሻሻ አይታ/የማይድን በሽታ/የዘር ፓለቲካ!!

 4. I read Getachew’s article with interest because it succinctly expressed fact that has been demonstrated by the current group of leadership. More of such practice is the new phenomenon being exercised by the currently quiet but active radicals (underground) including Jawar and the rest of ONEG elites. Be ware, much more is on the horizon and we need more of Getachew’s like nationalists exposing such practice in the making.

 5. Gemmadda said,
  ,……..They try to impose their default identity (Amaharaism as Ethiopianism) on the others…………

  this is a wrong assertion, Amhara has been the punch bag of ethno fascist groups for 40 years simply because the amhara stood their ground as staunch ethiopians. Generations of amharas have died for this country , defended its borders along with guragghies, sidamans, oromos, afaris, gambelan, Amhara=Ethiopia. this is something the ethno fascists thugs cannot take away from the amhara.
  from north to south, east to west within the borders of ethiopia, the amhara have paid the price , for the territorial integrity and security of ethiopia., for doing this ethno fascists call amhara ‘neftegna’. Neftegna means defender.
  some call the amhara as ‘chauvenist’. why? because the amhara are proud of their victorious achievement of our ancestors in defending ethiopia and making it the only country in africa to remain free and independent throughout its history. . Amhara’s survival and strength is a guarantee for the future of ethiopia.

 6. እዉነቱን እንነጋገርና መስሪያ ቤቱ 100% በአማሮች ቢያዝ ኖሮ እንኳን እንዳሁኑ እሪ ማለታችሁ ቀርቶ ድምጻችሁም አይሰማም ነበር! የአሁኑ ቀረርቶአችሁም፣ እንደለመድነው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሁሉ የአማራዎች የግል ክለብ ለምን አልሆኑም ነው ጭቅጭቃችሁ! የስራ ቋንቋው አማርኛ ቢሆንም አማራ ቢበዛ የህዝቡ ሩብ ስለሆነ በየእርከኑ የሚገባውም የስራ ቦታም ሩቡ ብቻ ነበር! አሁን ያለው ስታቲስቲክስ የሚያሳየው ግን የዚያን እጥፍ ነው። እናም ገና ብዙ መቀነስ ይኖርበታል ማለት ነው! የብልጠት ለቅሶአችሁ ታዉቆበታል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.