አንዷለም የፓርቲው ምክትል መሪ ሆኖ በመመረጡ ደስ ብሎኛል። ግን ደግሞ እንደ እሱ ያለ ጨዋ አንደበት እና ቅን ልቦና ያለው ሰው በጥላቻና ቂም ከጨቀየ ፖለቲካችን ውስጥ በመግባቱ አዝኛለሁ

በእርግጥ የፕ/ር ብርሃኑ መመረጥ አልገረመኝም። ሰውዬው ከአመሪካ እስከ አውሮፓ፣ ከኤርትራ እስከ ኢትዮጵያ በገሃድ የሚታይ ታሪክ አለው። “ብርሃኑ ነጋ” የሚለው ስም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ራሱን የቻለ ታሪክ ነው። የዚህን ታሪክ ቀጣይ ክፍል ደግሞ በኢዜማ አማካኝነት የምናየው ይሆናል። እኔን ግን በጣም ያሳሰበኝ ነገር የአቶ አንዷለም አራጌ ምክትል መሪ ሆኖ መመረጥ ነው።

በፖለቲካ ባህላችን ውስጥ መከባበር ቀርቷል። የፖለቲካ ልሂቃኖች ከትችት ይልቅ መዘላለፍ፣ ከትብብር ይልቅ መጠላለፍ የበዛበት ነው። በእንዲህ ያለ ፖለቲካ ውስጥ የፓርቲ አመራር መሆን የጭቃ ማጥ ውስጥ እንደ መግባት ነው። የፓርቲ መሪ ሆኖ የማይሰደብ፣ የማይዘለፍ፣ የማይወረፍ፣ የማይንቋሸሽ የለም። የፖለቲካ ማጥ ውስጥ እስከከገባህ ድረስ ጭቃ መለጣጠፍ ያለና የነበረ ነው።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለረጅም አመት የኖረበት ስለሆነ ይሄን የፖለቲካ ማጥ ለምዶታል። በእርግጥ አቶ አንዷለም አራጌም እንደ ፕ/ር ብርሃኑም ባይሆን የረጅም ግዜ ልምድ አለው። ሆኖም ግን በግሌ ለአንዷለም አራጌ በጣም እሳሳለታለሁ። አንዷለም በሀገራችን በተለምዶ ከምናውቃቸው የፖለቲካ መሪዎች ይልቅ የሃይማኖት መሪ ነው የሚመስለው። ከአንደበቱ ክፉ ቃል አይወጣም። አንዷለም በጣም ጨዋ ሰው ነው።

አንዷለም አራጌን በተደጋጋሚ አግኝቼዋለሁ። ከሁለት ሳምንት በፊት ስቱዲዮ መጥቶ በነፃ-ውይይት ፕሮግራም ላይ ቃለ-ምልልስ አድርገናል። ፖለቲካችንን በጥላቻና ዘረኝነት የጨቀየ ነው። ይህ ጭቃ እንደ እሾክ በሚዋጋ ስድብና ዘለፋ የተሞላ ነው። አንዷለም ደግሞ ለአክብሮትና አድናቆት እንጂ ለስድብና ዘለፋ የሚመች አይደለም። ትችትና ዘለፋ ቀርቶ ለጥያቄ እንኳን የሚያሳሳ ነው።

እንዲህ ያለ ስብዕና ያለው ሰው የኢዜማ ፓርቲ መሪ ሆኖ ተመርጧል። አንዷለም የፓርቲው ምክትል መሪ ሆኖ በመመረጡ ደስ ብሎኛል። ግን ደግሞ እንደ እሱ ያለ ጨዋ አንደበት እና ቅን ልቦና ያለው ሰው በጥላቻና ቂም ከጨቀየ ፖለቲካችን ውስጥ በመግባቱ አዝኛለሁ። እጅግ በጣም የማከብረው ሰው በስድብና ጥላቻ በተካኑ ግልብ ብሔርተኞች ከወዲሁ ሲሰደብና ሲዘለፍ እያሰብኩ መሳቀቅ ጀምሬያለሁ። ስለዚህ የአንዷለም መመረጥ ለእኔ ሰቆቃ ነው።

ወዳጄ ሆይ… አዲስ የተመሰረተው ኢዜማ ፓርቲ ምክትል መሪ መሆንህን ስሰማ በደስታዬ ልክ ተሳቅቄያለሁ። የፓርቲ መሪ ሆነሃልና እንደ ወትሮዬ በይፋ አንተን ከማድነቅ እቆጠባለሁ። ነገር ግን መነኩሴ የሚያስገርም ቅን ልቦና አለህ። የሚያስደምም ሰብዕና ሰጥቶሃል። ግን ደግሞ ፖለቲካችን ጨቅቷልና ከአሁን በኋላ ከስድብና ዘለፋ የተገመደ የጭቃ ጅራፍ ያርፍብሃል። ስለዚህ ይህን የምትቋቋምበት ወፍራም… በጣም ወፍራም ቆዳ ይሰጥህ ዘንድ እመኝልሃለሁ። ስቃይና መከራውን ችለህ ለሀገርና ህዝብ ቀና የሆነ ነገር ታደርግ ዘንድ የምመኝልህ ይሄን በዘረኝነትና ጥላቻ የጨቀየውን የመዘላለፍና የመጠላለፍ ፖለቲካ ለመቋቋም የሚያስችል ወፍራም ቆዳ እንዲሰጥህ ነው!! ይኼው ነው!!!!

ስዩም ተሾመ

4 COMMENTS

 1. Look Berhanu and his likes are going to use his face to promote their new G7 party that betrayed its fighters.

  Andualem has paid his share. But it does not mean he has noble idea now. He is just helping this useless party. Sad.

  You can see how Berhanu is again mischievous. He used Andualem and Yeshiwas to rob the Amara people Again

 2. ስዩም ተሾመ
  If you can not take the heat leave the kitchen ይባላል :: አንድ ሰው የፖለቲካን መሪነት ሲቀበል አብሮ የሚመጣውን ጣጣ ማስተናገድ ይኖርበታል:: ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና::ሽንጡን ገትሮ መታገል ነው::በመከራ ስለተፈተነ የፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች እንቶ ፈነቶ መሸነፍ የለበትም

  Girma
  እኔ እንደ አንድ አማራ ኢትዮጵያዊ በኢዜማ መመስረት ስጋት የለኝም:: ለየሺዋስ አሰፋም ታላቅ አክብሮት አለኝ:: ፕሮፌሰር ብርሀኑ የትናንት ፖለቲከኛ ስለሆነ ወጣቶቹ ወደፊት ይተኩታል ብዬ አምናለሁ:: ብቻውን በአማራ ላይ በዚህ ወቅት የሚፈጥረው ተፅእኖ አይኖርም:: እንደኔ ፍላጎት ቢኖር አብንና አዜማ እንዲሁም አዴፓ በጋራ የኢትዮጵያዊነት ራእያቸው የተራራቁ አይደለም:: ባይጠላለፉና በሚያቀራርባቸው አላማዎች ዙሪያ ቢሰሩ ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ድርሻ ይኖራቸውል:: ለምሳሌ ለኢትዮጵያ ፕሬዜዳንታዋ የመንግስት መዋቅር እንዲኖር ሶስቱም ፓርቲዎች አንድ አመለካከት አላቸው:: 3 ቱም የሚያውለበቡት አረንጏዴ/ ቢጫ/ ቀይ ሰንደቅ አላማ ነው:: አዴፓ በአደባባይ ወጥቶ ባያደርገው የክልሉ ህዝብ ግን መለያው አድርጏል::
  በኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋና አንድነት ይታየኛል:: ህውሀት የበተናትና የዘረፋት ሀገር አገግማ በአፍሪካ ኮከብ ሀገር እንደምትሆን አልጠራጠርም

 3. ” በእርግጥ የፕ/ር ብርሃኑ መመረጥ አልገረመኝም። ሰውዬው ከአመሪካ እስከ አውሮፓ፣ ከኤርትራ እስከ ኢትዮጵያ በገሃድ የሚታይ ታሪክ አለው። “ብርሃኑ ነጋ” የሚለው ስም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ራሱን የቻለ ታሪክ ነው። የዚህን ታሪክ ቀጣይ ክፍል ደግሞ በኢዜማ አማካኝነት የምናየው ይሆናል። ”

  What is that supposed to mean ?

  While writing pieces for readers we should try to be as less secretive as possible.

  Well, my views about Prof. Berhanu are contradictory. If he is the guy behind ESAT, then he contributed more than most in the fight against TPLF. And ESAT was at times the only opposition against TPLF. There is a reason why TPLF hates ESAT.

  That said, i am opposed to the Professor’s pro-Eritrea (as it concerns the Asseb region, my only problem with Eritrea) and pro-West views and tendencies. He also seems to have tribalist tendencies. That is without considering his role within the Qinijit coalition and suspicions about contacts with foreign powers.

 4. Well, i was surprised when i learned that, of all people, Berhanu Nega was elected to be leader of the new party.

  Then i thought, oh, USA is starting to put its people in key positions in Ethiopia.

  Guys, we must oppose and prevent pro-USA and pro-West Ethiopians from holding key positions in the country. We must do that in the interest of national security. All of us know that USA and the West are the biggest enemies Ethiopia ever encountered, who were responsible for overthrowing the governments of Haile Selassie and Derg, and for imposing the Askari TPLF regime.

  Ethiopians who sympathize with the West should not be allowed to hold key positions in the country.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.