የተከበሩ አቶ ሌንጮ ለታ ዛሬም ፋወል ሠርተዋል! (ሀይሉ AT)

“የብሔር ፌደራሊዝምን ለማፍረስ መሞከር ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው” ይሉናል የተከበሩ አቶ አቶ ሌንጮ ለታ::

የተከበሩ አቶ አቶ ሌንጮ ለታ ሐገርና መንግስታዊ የፓለቲካ ሥርዐት የተምታታባቸው መሠለኝ:: የናዚ አረመኔያዊ ሥርዐት እ.አ.አ በሜይ 7, 1945 ሲፈርስ ጀርመን ለሁለት ተከፍላለች:: የኮርያ ጦርነት ሲገባደድ ሰሜንና ደቡብ ሆና ተከፍላለች:: ጀርመንም ትሁን ኮርያ ለሁለት የተከፈሉት መንግስታዊው የፓለቲካ ቅርፅ በመቀየሩ ሣይሆን ዓለምን በሁለት ጎራ ከፍለው ይናጩ የነበሩትና በፀረ-ሂትለርና አጋሮቹ (triple Alliance) ላይ ህብረትን የፈጠሩት ምዕራባውያን እና የስቪየት ህብረት (triple ententes) የጦርነት ማግስት ውሳኔና ፓለቲካዊ ሴራ እና የአካባቢ ተፅዕኖ ክፍል በመቀራመት በማድረጋቸው (Sphere of Influence) እንጂ በጀርመንና ኮሪያ ሕዝብ ጥይቄ አልነበረም::

እውቅ የዓለማችን ግፈኛ የፓለቲካ ሥርዐቶች ማለትም በጀነራል ፍራንኮ የሚመራው የስፓኒሽ ወታደራዊ አምባገኖች፣ በሙሶሎኒ የሚመራው የጣሊያን ፋሺዝም፣ በፓል ፓት የሚመራው የካምቦዲያ ኪሜር ሩዥ፣ በጀነራል ፒኖቼ የተመሩት የቺሌ አምባገነኖች ወ.ዘ.ተ ተንደዋል:: እነዚህ አምባገነን ፋሽስቶች ሲወድቁ የተወገደው መንግስታዊ ቅርፃቸው እንጂ ሐገሮቹ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ቺሌና ካምቦዲያ እንደ ሐገር አልፈረሱም:: አምባገነናዊ ወይም ፋሽስታዊሥርዐት ሲገረሰስ ሐገሮች የሚበተኑ ቢሆን የፀረ-ፋሽስታዊ አምባገነኖች ባላስፈለገ ነበር:: ህወሃት ከፓለቲካ እርከቡ ተወግዷል:: “ህውሃት ከሌለ ኢትዮጵያ ያበቃላታል” ይሉን ነበር:: “የጎሣ ፌደራሊዝም” መንግስታዊ ሲስተሙ አሁንም አለ:: ኢትዮጵያም አለች::

የተከበሩ አቶ ሌንጮ ለታ እንደ ማርሽ የተቀላቀለባቸው መንግሥታዊ የሥርዓት ቅርፅና ሉዐላዊ ሐገር መካከል ያለው ልዩነት ነው:: እነዚህ ሥርዐቶች ይቀያየራሉ:: ሥርዐቶቹ ሲፈርሱ ግን ሐገር የፓለቲካ ሥርዐት እይደለምና አይፈርስም:: የሕዝብ ትግልም ዓላማው መብትና ነፃነት ለማስከበርና ለማስፈን እንጂ ሐገርን አፍርሶ አዲስ ሐገር ለመፍጠር አይደለም::

በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዴሞክራሲያዊ አግባብ ድምፁን ሰጥቶና ይሁንታውን ችሮ የገነባው የፓለቲካ ሥርዐት ኢትዮጵያ ምድር ላይ አልታየም:: ነባር ሥርዐቶችም በሕዝቡ ላይ የተጫኑ ናቸው:: “የጎሣ ፌደራሊዝም ከፈረሰ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” ሲሉን ከ46 ዓመት በላይ በፓለቲካ ትግል ዙሪያ ሲያረጁና የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔያዊ አፓርታይዳዊ ሥርዐት ስር እንዲማቅቅ ያስቻለውን “ሕገ መንግስት” አብረው ሲያረቁና ሲያፀድቁ ሕዝብ አልመረጠዎትም:: “የጎሣ ፌደራሊዝም ከፈረሰ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” የሚሉን ኢትዮጵያን “የሚያፈርሱና የሚመሰርቱ” ባለሙሉ ሥልጣን ፓለቲከኛ ሆነው ባልመረጠዎ ሕዝብ ሥም መናገር ያቁሙ:: ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ነውና::

ኦነግን ከመሰረቱበት እ.አ.አ ከ1973 ጅምሮ ለ46 አመት ከርስዎ ስንስማውና አብሮ ባረጀው ትርክቶ አያደንቁሩን:: ለእርስዎ የባላባት ቦታን የሚሰጥዎት “የጎሣ ፌድራሊዝም” ሥርዐት ከፈረሰ ኢትዮጵያ ትፈርሣለች እያሉ አያስፈራሩን:: ‘ውጪ ከጣህ ጅብ ይበላሃል’ እንደሚባል ህፃን አያባቡን::

ኢትዮጵያ ሐገሬን እንኳን ወዳጅ “የጎሣ ፌድራሊዝም” እና የርሶ የአፈጮሌ (demagogue) የማታ ተረት የጣሊያን ወረራ ኢትዮጵያን እላፈረሰም:: አይስጉ::

ክፉዋን የሚደግስ የጎጠኞች የራስ ቅል እንጂ ሐገሬ ኢትዮጵያ አትፈርስም!

2 COMMENTS

 1. ጃል ሀይሉ

  አቶ ሌንጮ አውነታቸውን ነው ፡፡

  እንዳአንተ አይነት የደናቁርት መንጋ የድሮ የሻገተ የአንድ ቋንቋ ፤ አንደሐገር ፤ አንድ እምነት አስተሳሰብ ይዞ አሁን ሐገሪቱ የደረሰችበት አውነታ ተነጋግሮ መተማመን ና መፍትሔ መፈለግ አጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡

  አትዮጵያን በሚያክል የተለያየ ብሔር የተለያየ እምነት ና የተለያየ አስተሳሰብ ትልቅ ሐገር ውስጥ ሀገር ና ህዝብን እንደግል ንብረት ማሰብና የኔ ብቻ ሐሳብ ትክክል ብሎ መድረቅ የድንቁርና መጨረሻ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ፡፡ የአስተሳብ የድኩማንነት የተጠናወታቸው የአማራ ኢሊቶች የሚያስቡት ና የሚያልሙት ትላንት ስለነበረችው አማራ የነገሠባት ሀገር ብቻ በመሆኑ የሌላውን ለመስማት ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው ፡፡

  ለማንኛው አቶ ሌንጮ ያሉት ትክክል ነው፡፡ የቋንቋ ፌድራለዝሙን የሚቃወሙት ከብዛታቸው ጩኸታቸው የበዛ ከአማራ ወገን የሆኑ ጥቂት ሠዎች ናቸው፡፡ ለተቀረው ፌድራሊዝሙ የህልውና ና የማንነት ጉዳይ ነው ና ይፈልገዋል፡፡ የአሁኑ ፌድራለዚም በምን ይሁን በምን ከፈረሰ ግን ብሔረተኝነት በገነነበት ሁኔታ ይህች ሐገር መፈራረሷ አይቀሬ ነው ፡፡ ማንም ሊቆጣጠረው የማይችል የራሳቸው ሀይል ያደራጁ የሚያፈነግጡ የብሔር መንግስታት ይፈጠራሉ ፡፡ ከዚያ አለቀ ፡፡ ያንተ አንድ ሐገር ፤ አንድ ቋንቋ ፤፡አንድ ምናምን ውሀ በላው፡፡

 2. “እባብን ያየ በልጥ በረየ” የሚለው ልክ እንደ እባብ ወገኖቻችንን የሚያባላው የጎሳ ፌደራሊዝም ያመጣብንን ጣጣ በማሰብ ጤናማ የብሄሮችን ተገቢ ጥያቄ ማጣጣል የለብንም:: ብሄር የአንድ ማህበረሰብ ከቤተሰብ በመነሳት የሚከሰት ስብስብ ስለሆነ ብሄርን ማጥፋት የሰውን ድምር ህልውና ማጥፋት የሚል እንድምታ ስለሚኖረው የኦቦ ሌንጮ ትንታኔ የሚወገዝ አየደለም::ሆኖም ግን የጥላቻ የብሄርም ሆነ የግለሰብ እንቅስቃሴ ጎጂና አጥፊ ስለሆነ መታረም መታገድ ይገባዋል:: ኦቦሌንጮና መሰሎች በነፍሳቸው ተወራርደው ከደርግ ዘመን ጀምሮ ያደረጉትን የህዝብ መብት ማስከበር ትግል በማክበር በተሳሳቱበት ገንቢ ትችት ማቅረብ በጎ ሂና ያላቸው ሁሉ ሃላፊነት ነው::የብሄሮች መብት ጥያቄ Question of Nations and nationalities በአግባቡ ባለመመለሱ ለውድቀት ለመፈራረስ የበቁት የዩጎስላቪያ ችግሮች በማየት መማር ይኖርብናል:: የብሄር ጥያቄ በግራና በቀኝ በክፉ ሊውገረገር አይገባውም:: ብሄር ማለት የሰው ዘር ስብስብ አንዱ ደረጃ ሲሆን ያንን በተገቢው መንገድ ማንነቱ ባህሉ ቋንቋው በመከበር በሰላም ሊተገበር ይገባዋል:: በተቃራኒው የብሄር ጥላቻ አንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ በማለት የተደባለቀን ህዝብ ለመለያየት አንዱ ብሄር ዘር በሌላው ላይ በክፉ እንዲዘምት የሚያደርገው እኩይ ስራ ሃገራችንን በሃገር ውስጥ መፈናቀል ቀዳሚ ሊያደርጋት መብቃቱን መካድ አንችልም:: ካለንበት ውጥንቅጥ ወጥተን ሌላ ተጨማሪ መፈናቀል መተላለቅ እንድንድን በሰላምዊ ውይይት በመግባባት መነጋገር የገባን ዘንድ በጎ ህሊና ያላቸው ሁሉ ሊመክሩ ድምጻቸውን ሊያሰሙ ይገባል::
  የኤርትራ ጉዳይም የታሪክ ምሁሩ በቅንነት እዚህ እንደሚናገሩት ሳይሆን ጥቂት የማይባሉ ዛሬም በኢትይዖፒያ ላይ ከፍ ያለ ጥላቻ ያለቸው ስላሉ በጥበብ እንደእርግብ የዋህ እንደ እባብ ልባም በመሆን ሁሉን በጥበብ መፈጸም ይኖርብናል::
  ትግራይ ትግሪኛ ብሎ ወልደአብ ወልደማሪያም የጀመረው ትግል የብሄር ትግል አካል ሲሆን በጠማማ ፍልስፍና የመገንጠል ጥያቄ በማስከተል ራሷን ማስተዳደር ቀርቶ በሃገርነት መቆም የማትችል ኤርትራ ከኢትዮጲያ ተነጥላ መታመኛዋ አቅርቦት በአዲግራት ገብሬዎች ሲዘጋ ያላስፈላጊ የድንበር ግጭት በባድመ ተንሰቶ ከሁለቱም ድሃ ሃገሮች በልዩ መሳሪያ ያለቁት ወገኖቻችን ሊረሳ የማይችል ትምህርት ሰጥቶናል::ኢጭአት የተባለውን የብሄር ድርጅቶች ማሀበር ትቶ ከወንድሙ ፓስተር ጉዲና ቱምሳ ጋር ኦነግን የመሰረተው ባሮ ቱምሳ በራሱ የባሌ ኦሮሞውች የታረደውም የብሄር የጎሳ ፖለቲካ አደገኛነት ለሁሉም መሆኑን ያስተምራልና ከታሪክ እንማር::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.