የናቶች ድካም በዓመት አንድ ቀን ታስቦ የሚውል አይደለም

ዛሬ የእናቶች ቀን ነው ይሏችኋል ። መንገድ ዳር አበባ የሚሸጠው ለጉድ ነው ። ሱቅ ገብቼ $9.99 እገዛው የነበረ አበባ ዛሬ $14.99 ሆኗል ። ሱቆች ከመጠን በላይ መልካም መልዕክት ያላቸውን ካርዶች ለገበያ አቅርቧል ። ዋጋቸው $3.99 እስከ $6.99 ነው ። ሲከፈት Happy mother’s day የሚዘፍነው ደግሞ ወደድ ይላል ። የቸኮላቱ አይነት ተውኝ ። ዋጋውም ከሌላው ግዜ ወደድ ይላል ። ቢሆንም ግን ሁሉም አቅሙ ሚፈቅድለትን ገዝቶ ከአበባ ፣ ከካርድ ጋር አድርጎ ለናቱ ያበረክታል።

ታላላቅ ምግብ ቤቶች ቀደም ተብለው ተይዘዋል ። የቤተሰብ ምግብ ቤቶች (family’s restaurant ) ተብለው የሚጠሩት ሁሉ ዛሬ ጥቅጥቅ ይላሉ ። በነገራችን ላይ እነዚህ የቤተሰብ ምግብ ባቶች አብዛኛውን ግዜ የሚገለገሉባቸው ብዙ ቤተሰብ እና ልጆች ያላቸው ናቸው ። በነፃነት ምትመገቡበት 
 እናቶች የዛሬን ቀን ለማክበር ፀጉር ቤቶችም ተጨናንቀዋል ። ቀደም ብለው የተያዙ ቀጠሮዎች ብቻ ሳይሆን ድንገት ዘው ብለው ፀጉሬን ለመስራት ነበር የሚሉ ተገልግጋዮች ትንሽ ሊያስጠብቃችሁ ይችላል ቢባሉም እንጠብቃለን በማለት ማረፊያ ቦታ ተኮልኩለው የወሩን መጽሄት ያገላብጣሉ ግማሾቹ ስልካቸው ላይ ተደፍተዋል ። ዛሬ ልብስ ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች ፣ ፀጉር ቤቶች ፣ ቸኮላት ሻጮች ፣ አበባ እና ካርድ ሱቆች ትልቅ ገቢ የሚያገኙበት ቀን ነው ።

እማዬ ዛሬ የናቶች ቀን ነው እና አንቺ ቁጭ በይ እኔ ቀኑን ሙሉ ያንቺን ስራ ልስራ የሚል ወዴት አለ ? ያው ሚገዛውን ገዝቶ እና ቀጠሮ የያዘበትን ሰዓት ጠብቆ ይመጣና እራት ጋብዞ ያበቃል ። ይህ ነው የናቶች ቀን ።

ከላይ የዘረዘርኩት የውጭ አለሙን ነው ።

የኔን ልንገራችሁ ። እናቴ እቤት ስትመጣ ምንም እንድትሰራ አልፈቅድላትን ። መቼም ትምጣ ፣ በስንት ሰዓት ትምጣ ፣ ስንት ቀን ትቆይ ፣ ምንም መስራት አትችልም ። ስከለክላት ለምን ማለትዋ አይቀርም ። የኔ መልስ ግን ባጭሩ “አይሆንም” ነው ። እሷ ለኔ ነፍስ እስካውቅ ድረስ የምትችለውን ሁሉ አድርጋልኛለች ። በልጅነት ግዜዋ ብዙ ልጆች አሳድጋለች ። አሁን እኔ ነፍስ አውቄ የራሴን ቤት ማስተዳድር ስለሆንኩ እናቴ እኔ ቤት ሁሌም የክብር እንግዳዬ ናት ። ንግስት ናት ። ከምንም በላይ ደግሞ ክብር አለኝ ። ነፍስ አውቄለሁ ብዬ አልዘባነንም ። እናት ሁሌም አስተማሪ ናት እና ሁሌም አዲስ ነገር ከሷ እማራለሁ ። እናቴ እኔ ቤት ባረፈች ወይንም በመጣች ቁጥር ለኔ የናቶች ቀን ነው ። ቡና አብረን እንጠጣለን ። ምሳ እንበላለን ። ከተማ ወጥተን እንዞራለን ። ሲደክመን እቤት ገብተን እናርፋለን ። የሆድ የሆዳችንን እንጫወታለን ። ኧረ ስንቱ ።

ታዳያለሽ አትበሉኝ እና የኢትጵያ እናቶች ግን ምርጥ እና ወደር የሌላቸው አይደሉ ? እስኪ ከታች ያሉትን ምስሎች ልብ ብላችሁ ተመልከቱት ። መንገድ እየተጓዙ ልጅ ማጥባት ፣ በጀርባ እንጨት በትከሻ ልጅ ፣ እንጀራ ለማብላት በእሳት መለብለብ ፣ ውሃ ለማጠጣት ወገብ መስበር ። ቤቷ እንዳይጎል ደፋ ቀና ብላ ከዛም ከዚህም ተዳፍታ ፣ ገበናዋን ደብቃ ስንቱን ችላ ልጆችዋን አብልታ አጠጥታ አጥባ ታስተኛለች ። ከዛ በኋላ ነው የሷ እረፍት ።

ታዲያ ለዚች እናት በአመት አንድ ቀን ግፍ አይሆንም ?

መንበረ ካሳየ

1 COMMENT

  1. Who is this guy who tries to culturally subvert Ethiopians by reporting about a ferenji holiday ===> መንበረ ካሳየ ?

    Is he a CIA spy ?

    Oh, by the way, ESAT used to do that too.

    Is he aware that what he is doing could have consequences for him ?

    Ferenji culture is being wiped out around the world. Those people like መንበረ ካሳየ who dare to go against this global trend could face problems.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.