“እነ ለማ መገርሳ ‘ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው’ ሲሉ፤ ሕይወታቸውን ቀብድ አስይዘው ነው።” – ፕሮፌሰር ሰለሞን አዲስ ጌታሁን

“የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ከየት ወዴት?”  በሚል የመነጋገሪያ አጀንዳችን፤ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የለውጡ ጅማሮ ያበረከታቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች፣ የገጠሙትን ተግዳሮቶች፣ ያሳደራቸውና ስጋትና ተስፋዎች አስመልክቶ ከፕሮፌሰር ሰለሞን አዲስ ጌታሁን፤ በማዕከላዊ ሺካጎ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር፤ ታሮካዊ ምልከታቸውን ያንጸባርቃሉ።

 

1 COMMENT

  1. የብሄሮች መብት ጥያቄ Question of Nations and nationalities በአግባቡ ባለመመለሱ ለውድቀት ለመፈራረስ የበቁት የዩጎስላቪያን ችግሮች በማየት መማር ይኖርብናል:: የብሄር ጥያቄ በግራና በቀኝ በክፉ ሊውገረገር አይገባውም:: ብሄር ማለት የሰው ዘር ስብስብ አንዱ ደረጃ ሲሆን ያንን በተገቢው መንገድ ማንነቱ ባህሉ ቋንቋው በመከበር በሰላም ሊተገበር ይገባዋል:: በተቃራኒው የብሄር ጥላቻ አንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ በማለት የተደባለቀን ህዝብ ለመለያየት አንዱ ብሄር ዘር በሌላው ላይ በክፉ እንዲዘምት የሚያደርገው እኩይ ስራ ሃገራችንን በሃገር ውስጥ መፈናቀል ቀዳሚ ሊያደርጋት መብቃቱን መካድ አንችልም:: ካለንበት ውጥንቅጥ ወጥተን ሌላ ተጨማሪ መፈናቀል መተላለቅ እንድንድን በሰላምዊ ውይይት በመግባባት መነጋገር የገባን ዘንድ በጎ ህሊና ያላቸው ሁሉ ሊመክሩ ድምጻቸውን ሊያሰሙ ይገባል::
    የኤርትራ ጉዳይም የታሪክ ምሁሩ በቅንነት እዚህ እንደሚናገሩት ሳይሆን ጥቂት የማይባሉ ዛሬም በኢትይዖፒያ ላይ ከፍ ያለ ጥላቻ ያለቸው ስላሉ በጥበብ እንደእርግብ የዋህ እንደ እባብ ልባም በመሆን ሁሉን በጥበብ መፈጸም ይኖርብናል::
    የነለማ “በነፍሳቸው መወራረድም” በጥያቄ ውስጥ ያለ ነው:: ለማ መገርሳ በዲሞግራፊው ቀመር በልቡ ያለውን ያውጣ ወይስ በቅንነት ይናገረው በፍሬያቸው የሚያታይ ነው:: በዚያው ስብሰባ ላይ አዲሱ አረጋ “ታከለ ኡማ ብዙ የሚያደርግልን በሚዲያ የማይነገር አለ” ያለው በምኞት ይሁን ወይንስ በነአብይ ቅንብር ይህ በፍሬያቸው በሁደት የሚጣራ ነውና የሃገራችን በሳል 42 ምሁራን የላኩት መልስ ከአብይ አህመድ በተግባር ሳይገኝ በተደረገው በጎ ሂደት ብቻ ተደላድለን ሳንቆም በመጠየቅ በቅን በመሳተፍ ጽንፈኞችንም በመፋለም ልንተጋ ይገባል::ኢጭአት የተባለውን የብሄር ድርጅቶች ማሀበር ትቶ ከወንድሙ ፓስተር ጉዲና ቱምሳ ጋር ኦነግን የመሰረተው ባሮ ቱምሳ በራሱ የባሌ ኦሮሞውች የታረደውም የብሄር የጎሳ ፖለቲካ አድገኛነት ለሁሉም መሆኑን ያስተምራልና ከታሪክ እንማር::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.