የአንበሳ ቢራ ማስታወቂያ ታገደ

የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና የህትመት ሚድያዎች ሲተላለፍ የቆየውን የአንበሳ ቢራ ማስታወቂያ ሸማቾችን የሚያሳስት መልእክት ይዟል በሚል ምክንያት ከግንቦት 6 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም ሚድያ እንዳይተላለፍ ማገዱን አስታወቀ፡፡

ማስታወቂያው የታገደው የቢራ መጠጥ በሳይንሳዊ የፍተሻ ሂደትም ሆነ በኑሮ ልማድ ባለ እውቀት ብሩህ ተስፋ ላለው ልባም ተጠቃሚ ሊጠመቅ የሚችል መጠጥ ስለመሆኑ ምንም አይነት መረጃ በሌለበት ሁኔታ “ብሩህ ተስፋ ለሚታየው ልባም ፤ ለልባሞች ከልብ የተጠመቀ” በሚል እንዲተዋወቅ መደረጉ ስለንግድ ማስታወቂያዎች የተደነገገውን ክልከላ በመተላለፉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀፅ 19/8 መሰረት ሸማቾችን የሚያሳስት ይዘት ያለው ማስታወቂያ እንደሆነም ባለስልጣኑ ለኢቢሲ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

በአዋጁ መሰረት የንግድ እቃ ወይንም አገልግሎትን በመጠቀም የሚጠበቅ ውጤትን አሳሳች በሆነ መንገድ መቅረፅ ክልክል ሲሆን ከአዋጁ ጋር የማይጣጣሙ የንግድ እቃዎችን እና አገልግሎቶች ማስታወቂያዎች ሲተላለፉ ባለስልጣን መስሪያቤቱ የማገድ ስልጣን እንዳለውም አቶ አልቃድር ኢብራሂም የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሪክተር ለኢቢሲ አስታውቀዋል፡፡

የእገዳ ደብዳቤው ለሁሉም የኤሌክትሮኒክስ እና የህትመት ሚድያዎች እንደተሰራጨ እና እገዳውን በመተላለፍ የንግድ ማስታወቂያውን የሚያስተላልፍ ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆንም ባለስልጣን መስሪያቤቱ አስታውቋል፡፡

via EBC

1 COMMENT

  1. ” የአንበሳ ቢራ ማስታወቂያ ታገደ ”

    The sale and commercialization of traditional drinks like Tela, Tej and Katikala should be encouraged and supported, not ferenji drinks like Beer, Whisky and Gin.

    Askari TPLF was promoting and spreading all things ferenji, now that has to be reversed.
    Also, the poor population hasn’t the money to buy ferenji drinks like Beer. The little money the people have is better invested if it is spent first to buy basic food. Money spent on Beer and Chat is a wasted money and should be discouraged. The government has to make sure that poor people don’t waste their money for Beer and Chat. If necessary let Beer companies go bankrupt.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.