ሰሞነኛው የወያኔ ዘፈን፣ የመቀሌ ሁካታና ጫጫታ! (ሀይሉ )

የመርዘኛው የጎሣ ፖለቲካ መገለጫ ማንኛውም የጎሣ አባል ከጎሣው ውጪ ለሚፈፀመው ወንጀል ጎሣዊ ሽፋን መስጠት ነው። ጥላቻ፤ ፍቅር፤ አሣቤ ሁሉ የማህበር ነው። ህሊናም ማሰብ የሚፈቀድለት አንዲሁ በጋራ የራስ ቅል ነው።

ጌታቸው አሰፋ የሕዝብ ደም በእጁ ላይ ነው። ለዚህ ነብሠ ገዳይ መሟገት ወንጀልን መሸፈን ብቻ ሣይሆን ወንጀልን መተባበርና ወንጀለኛም መሆን ነው። ህወሃት ‘እኔም ጌታቸው አሰፋ ነኝ’ በተሠኘ መሪ መፈክር ስር የግለሰቡን ለፍርድ መቅረብ በመቃወም የመቀሌና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሠልፍ እንዲወጡ እየቀሰቀሰች ነው።ይገርማል። ህወሃት ይህን ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ለፍርድ መቅረብ መቃወሙ ለሕግ የበላይነት እንደማይገዛ ማመላከቻ ነው። እያንዳንዱ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ በጎሣው ብብት ውስጥ እየተደበቀ ለፍርድ የማይቀርብ ከሆነ ስርዓተ አልበኝነት ነገሰ፤ ሐገርም ተናደ ማለት ነው።ይልቅ ‘እኔም ጌታቸው አሰፋ ነኝ’ የሚለው የህወሃታውያን መሪ መፈክር ‘እኔም ወንጀለኛ ነኝ’ የሚል አንደምታ አለው። ህወሃት በዚህ አቋሙ ከገፋና ይህን ተጠርጣሪ ወንጀለኛ አሣልፎ ካልሰጠ እኛና ህወሃት ፊርማችንን ቀደን የምንፋታበት ጊዜ ቢኖር ይህ ብች ነው።

መንግስት በቦሌም ይሁን በባሌ ማንኛውንም መንገድ ተጠቅሞ ይህን ገዳይ ለሕግ ማቅረብ ካልቻለ ጥያቄ ወስጥ ይወድቃል። የጌታቸው አሰፋ መታሰርና በሕግ መጠየቅ ግለሰቡ ላይ የእስር ብይን ለመስጠት ብቻ ሣይሆን ተመሳሳይ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ዋስትና ነው።

የዴሞክራሲያዊ ሐገር ምስረታ ሕግና የሕግ የበላይነትን በማስከበር ይጀምራል። የመንግስት ጥንከሬና ለሕግ የበላይነት ያለውን ቁርጠኝነት አመልካች ነው።

NO MORE IMPUNITY!

EVERYBODY IS EQUAL BEFORE THE LAW, THE EYES OF THE LAW. USE ALL AVAILABLE MEANS & ARREST THE BRUTE GETACHEW ASSEFA. HE IS NOT SPECIAL & EXEMPTED FROM PUNISHMENT.
===========

የሚከተለውን ድንቅ የኢብነዘር አኪንሪኔድ አባባል መጠቀም እመርጣለሁ።

‘ጎሣዊ ኢ-ፍትሃዊነት (Tribal Injustice)!’

‘ይህ ሌባ የሌላ ጎሣ አባል ነው:: በክሱ ጭብጥና ቅጣት መሠረት ወንጀለኛ ነውና ይገደል::’

****
‘ይህ ሌባ የኛ ጎሣ አባል ነው:: በክሱ ጭብጥና ቅጣት መሠረት ወንጀለኛ ይመስላል:: ነገር ግን የኛ ሌባ ስለሆነ በነፃ ይሂድ::’

2 COMMENTS

  1. Aite Getachew Assefa is one of the popular heroes of Tigray. Handing overm him to the enemies of Tigray and Tigrayans is a betryal and those who would collaborate with our enemies will face severe punishment . Our enemies will never be able to arrest our hero aite Getachew Assefa. He will be protected by any means including force.

  2. ” ህወሃት ‘እኔም ጌታቸው አሰፋ ነኝ’ በተሠኘ መሪ መፈክር ስር የግለሰቡን ለፍርድ መቅረብ በመቃወም የመቀሌና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሠልፍ እንዲወጡ እየቀሰቀሰች ነው።ይገርማል። ”

    What that tells us is Askari TPLF can not learn from its past crimes, TPLF can not change, TPLF can not be reeducated, TPLF shows no remorse, and TPLF would commit the same crimes again if it had the opportunity. The “medemer” principle doesn’t work for TPLF.
    TPLF has to be arrested and punished for its crimes.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.