አገውን ከገዛ እርስቱ ከመተከል ማፈናቀል የማይታሰብ ነው (አዲሱ መኮንን)


የሞት ሁሉ ክፉ ሞት አገውን ከገዛ ባድማዉ ማፈናቀል ነው። የቤንሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የመተከል ዞን አስተዳደር፣ በመተከል ዞን የምትገኙ የየወረዳ እና የየቀበሌ ሀላፊዎች አገውን ከገዛ እርስቱ ማስወጣት ለወደፊቱ አደጋው የከፋ ይሆናል። መተከል “ሚቲኪሊ” የሚል ታሪካዊ የአገው ህዝብን ስያሜ የያዘች እና የአገው ህዝብ በየትኛውም ዋጋ የማይተመን ክብር ህይወቱን ትናንት የገበረባት ግዛታችን ናት።

የአገው ህዝብ መተከልን ለውጪ ወራሪ ሀይል አላስደፍርም ብሎ ለዘመናት ከሱዳኖች ፣ ከእንግሊዞች እና ከጣሊያኖች ጋር እልህ አስጨራሽ ጦርነትን በማድረግ ሺህ የአገው አርበኞችን ገብሮ ግዛታችንን ሳያስደፍር ለአሁኑ አገው ትውልድ ማለትም ለእኔና ለሌሎች ውድና ለጀግኖች የአገው ልጆች አስረክበዋል። የእኔ ትውልድ አባቶቻችን የሰጡንን ታሪካዊ የግዛት ባለቤትነት መብት መነጠቅ ማለት የሽንፈታችን ሁሉ ተራ ሽንፈት መሆኑን ልንረዳ ይገባል።

የአገው ንጉስ ዣንችዃይ ያስረከቧትን ሚቲኪሊ ማጣት ማለት ለሁሉም አገው ህዝብ የቁም ሞት እና ታሪካዊ ስህተት እንዲሁም ማንነታዊ ጥቃት ነው። ንጉሳችን ዣንችዃይ “ሰለሞናዊ ሪዮዕት ዓለምን (ስዩመ- እግዚአብሔር )” በአገው ህዝብ ላይ ለማስረፅ ከውስጥ በተደጋጋሚ ከሸዋ እና ከጎንደር ገዥዎች ይደረግ የነበረውን ጦርነት ይፋለሙ የነበሩባት መተከል የአገው ህዝብ “የደም መሬት” መሆኗ የሚታወቅ ነው። ታድያ በሺህ አገው ደም ከቆየችልን ግዛት አገውን ማፈናቀል ማለት ቅዠት ነው።

የአዊ ዞን አስተዳደር ለተፈናቃዮቹ እያደረግክ ያለኸው መልካም ወገናዊ ደራሽነት እጅግ የሚያመሰግን ነው። የአገው ብሔርተኝነትም የትግል ማዕከልነቱ ይህ እንዲሆን ስለሆነ የአዊ ዞን አስተዳደር ለተፈናቀሉ አገዎች ያሳየችሁት ልባዊ ፍቅር አኩርቶናል። መሪነት ህዝባዊነት መሆኑንም አረጋግጣችሁልናል። ሁሌም ከአገው ህዝብ ጎን ስትቆሙልን የአገው ብሔርተኝነት ታጋይ ወንድሞቻችሁም ልባዊ ደስታቸው የላቀ ይሆናል ፤ ለመልካም ስራችሁም ዕውቅና ይሰጣል።

አሁንም ቢሆን ለተፈናቃይ ቤተሰቦቻችን ወገናዊ ድጋፍ በተለይ በጤና፣ በውሃ፣ በምግብ፣ በምኝታ እና በሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶች ከአዊ ዞን የሸንጎ አመራሮች ጋር በመሆን የአዊ ዞን አስተዳደር አስፈላጊውን ግዴታ እንዲወጣ ከልቤ ጥሪዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። ለህዝባችን ደራሾቻችን እኛው ራሳችን መሆኑን አውቀን ጊዜ የማያሻቸውን መሠረታዊ ነገሮች ለተፈናቀሉ ቤተሰቦቻችን ህዝባችንን በማስተባበር ማቅረብ ቤተሰባዊ ግዴታችን ነው። ለቤተሰብ ደራሽ ቤተሰብ ነው።

ማህበራዊ ፍትህ ለተፈናቃሉ አገው ቤተሰቦቻችን

አዲሱ መኮንን

 

4 COMMENTS

  1. Is it only Agewus that have been and are being the victim of the very evil- guided politics of ethnicity of EPRDF and its so- called allies or satellite groupings from Metekel or anywhere else? Why we totally lost in a very dirty political game of ethnic and parochial politics ? What is wrong with standing against all political crimes being committed by the ruling party or by any crazy grouping? What we do not say that all innocent Ethiopians should not be victims of all politically motivated eviction and its consequences ? Will these kinds of very narrow and terribly parochial political attitude and behavior take us where we want to be ? Why not at least mention other innocent Ethiopians whenever we talk about our own ehtinic group? Very sad!

  2. Guys,

    stop worshipping the anti-Amara TPLF constitution that was designed by Benito Mussolini !

    Restore the Gojam province !

  3. Gojam is an appropriate title for various groups who have been living there for years.I remember my class mate girl at College told me she didn’t want to be called called Amhara that I respect .There are many ethnic groups some diminshing like Agoba and others exiting like Agew,Kemant and who want to keep up their identity.Same is true in South and West who are identified by others like Dawro ,Gabra etc as Oromo but they have different identity they want to be recognized. Raya in the Noreth has also such identity not to be tossed with Amhara,Oromo or Tigere.It is high time to respect the identity of all not to assign any different ethnic group to the major ethnic groups.However the bottomline is the create a untied Ethiopian federal republic by regions accepting member ethnic groups with democratic federalism instead of tribal or ethnic federalism.

  4. ይቅርታ በትግርኛ መተከል ማለት “መተከልቲ” ነው፡፡ ይህ ደግሞ የተጋሩ ታሪካዊ ዕርስት ሰለሆነ ማንም እየተነሳ የባለቤትነት ጥያቄ ሊያቀርብ አይገባም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.