ድንቅ ነው-በትግራይ ክልል ባለፉት 9 ወራት 38 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመን ፈቃድ ተሰጠ

 በትግራይ ክልል ባለፉት 9 ወራት 38 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 1 ሺህ 258 ባለሃብቶች የኢንቨስትመን ፈቃድ ተሰጠ።

የክልሉ የከተማ ልማት፣ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሃፍቶም ፋንታሁን እንደገለጹት ፥በተጠቀሱት ወራቶች ለ1ሺህ 185 ፕሮጀክቶች ፍቃድ ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር አንስተዋል።

ይሁንና በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ተከትሎ የስራ አፈፃፀሙ ወደ 1 ሺህ 258 ማደጉን ተናግረዋል።

የተሰጡት አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶችም ለማኑፋክቸሪንግ 755፣ ኮንስትራክሽን 219፣ ለግብርና 218፣ ለማህበራዊ አገልግሎት 24፣ ለሆቴልና ቱሪዝም 22 እንዲሁም ለማዕድን 20 መሆናቸውን አብራርተዋል።

በካፒታል ደረጃ ሲታይም በማኑፋክቸሪንግ 32 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር፣ በግብርና 1 ነጥብ 76 ቢሊየን ብር፣ በሆቴልና ቱሪዝም 1 ነጥብ 17 ቢሊየን፣ በኮንስትራክሽን 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር፣ በማህበራዊ አገልግሎት 209 ነጥብ 6 ሚሊየን እንዲሁም በማዕድን 240 ሚሊየን ብር መሆኑ ነው የተገለፀው።

ፕሮጀክቶቹ በቋሚነት ለ143 ሺህ 530 ዜጎች እንዲሁም 47 ሺህ 561 ለሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በጊዜያዊነት የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የስራ አፈፃፀም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም በእጥፍ መጨመሩን አቶ ሃፍቶም ገልፀዋል።

በደስታ ተካ/ኤፍ.ቢ.ሲ

3 COMMENTS

  1. That is the stolen money from Ethiopia !

    All money and wealth in Tigray was stolen from Ethiopia and can be confiscated.

  2. This is just a tiny fraction of the loot tigre liberation front has amassed over the last 27 years . Tplf looters have packed their loots in sacks and carried them on lorries into tigraiy. There has been massive amounts of looted capitsl inflow into tigraiy.
    It is good that some of the money is remaining in the country and will benefit the tigreay people. On the other hand tigre liberation front has been using some of their loot to cause bloodshed and mayhem in places like benishingul and ogaden and addis abeb2.
    Billions of dollars still remain in foreign banks held by tplf politbureau membrs and their kits and kin. Unfortunately this money is gone for ever.

  3. ግልጽ ያልሆነልኝ፣ ኢንቬስትስ ያርጉ፣ የት ነው የሚሸጡት? ከትግራይ ቀጥታ ውጭ አገር ይልካሉ? ቀረጥ ይከፍላሉ? የስብሃት ወንድም ልጅ ፈትለወርቅ የኢንዱስትሪ ሚንስትር መሆኗ ሁሌ ያሳስበኛል። በየሚንስቴር መ/ቤት ያሉ ሁሉ ነቅተው መከታተል አለባቸው። የከዚህ ቀደሙ ዝርፊያ መደገም የለበትም። በህግ እስከ ሆነ ማንም ይሁን ማን ይሥራ። ችግር የለብኝም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.