አዋኪ ናቸው የተባሉ 231 የንግድ ተቋማት ታሸጉ

የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 231 አዋኪ ናቸው የተባሉ የንግድ ተቋማትን ማሸጉን አስታውቋል።

አዋኪ የንግድ ተቋማትቱ ውስጥ 38 የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ወስዷል።

በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ 9 የንግድ ተቋማት ታሽገዋል። ጫት ለመቃምና ሺሻ ለማስጨስ ይውሉ የነበሩ 3 ሺህ 500 እቃዎች እንዲወገዱ መደረጉም ተገልጿል።
66 የንግድ ድርጅቶች ያልተፈቀደ የውጭ ምንዛሪ ሲሰሩ ተይዘው በክስ ሂደት ላይ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በኮንድሮባንድ ቁጥጥርም ከ15ሺህ ሊትር በላይ የፓልም ዘይት፣ ከ24ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚል እና 269 ኬሻ ለውጭ ገበያ የሚውል ቡና መያዙን ገልጿል። 253 ኩንታል ስኳር በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የ9ወራት አፈፃፀሙን በማቅረብና የ3 ወራት የኮንትሮባንድ እና ህገ ወጥ ንግድ ለመከላከልና የመቆጣጠር እቅዱን አቅርቦ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

ሪፖርተር፡- አስማረ ብርሃ

2 COMMENTS

 1. እርምጃው ቢዘገይ እንጂ አይደንቅም፡፡ ሰዉ እኩ ከተበከለ ቆይቷል፡፡ ገና ብዙ ስራም ይቀራል፡፡ እናት ወይም አባት ወይም ሌላ ዝም ብሎ ገንዘብ መሰብሰቢያ መንገድ መፈለግ እንጂ ህሊና ከጠፋ ቆየ፡፡ ልጅ ሳታውቅ እናቷ ሺሻና አሽሽ በምታስጨበት ቦታ ላይ የተገኘችበት ጊዜ ነው ያለነው፡፡

  ይቆጣጠራሉ ተብለው የተቋቋሙ መ/ቤቶች መች ስራቸውን በአግባቡ ያከናውናሉ፡፡ የሚገርመው እኮ ደሞዝ የሚከፈላቸው እኮ ከምስኪኑ ህዝብ ከሚሰበሰብ ግብር መሆኑን ይዘነጋሉ፡፡ ለህሊና ሰርቶ መሞት ጥሩ ነው፡፡ ነገ ምን አይነት ትውልድ ሊኖር እንደሚችል አሳሳቢ ነው፡፡ ከጫት ጀምሮ ብዙ ብዙ ህገወጥ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡ ይህ ለአገር ውድቀት ነው፡፡ በወቅቱ ያለ አስተዳደርም ለዚህ ሁሉ ተጤቂ ነው፡፡

  እንዴት ነው ነገሩ????? ቻይና አገር እኮ አደንዛዥ ዕፅ ይዞ መገኘት ሞት ፍርድ ነው የሚያስከትለው፡፡ በድሮ ዘመን አገራችን ቆፍጣና አመራር ነበራት፡፡ አሁን ግን ትውልድ ለማጥፋት ይመስላል፡፡ ስንት ተማረ የሚባል የአስተዳደር እርከን እያለ ጨዋታ፡፡ አሁን ነው ሊታሰብበት የሚገባው፡፡

 2. ====> this thing is new and is not an Ethiopian/African tradition: ሺሻ

  Why was it allowed to spread in Ethiopia ?

  We need to start to cleanse Ethiopia from harmful non-Ethiopian cultures, traditions, habits, etc

  That ሺሻ could spread in Ethiopia has sure something to do with the plan of Askari TPLF to destroy Ethiopian culture. Askari TPLF was promoting every harmful habit from foreign lands.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.