ጥሩ መሪ መናገር ብቻ ሳይሆን ማዳመጥ አለበት!

ዛሬ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተሳታፊ ነበርኩኝ። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ጠ/ሚኒስትር አብይን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ኃላፊዎች እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተው ነበር። ከመድረኩ መሪ ጀምሮ አራቱን ፅሁፍ አቅራቢዎች በጣም ምርጥ የሚባል ሥራ ሰርተዋል። እውነት ለመናገር በውስጤ የሆነ ደስታ ተሰምቶኛል።

እንዲህ ያሉ ምጡቅ የሆነ አዕምሮ እና ሰፊ ልምድ ያላቸው ምሁራን ቀድሞ ከተገፉበት እና ከተሰደዱበት መጥተው ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል ያሉትን ዕውቀት እና ሃሳብ በነፃነት ሲያቀርቡ ማየት በጣም ደስ ይላል። ሌላው ደስ ያለኝ ነገር የዶ/ር አብይ ምግባር ነው። እንደ ማንኛውም ሰው በስብሰባው ታድሞ የምሁራኑን ሃሳብ በጥሞና አዳምጦ ሄዷል። ይሄ ለአንዳንዶች ምንም ላይመስል ይችላል። ነገር ግን የፖለቲካ መሪዎች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የመናገር እድል አላቸው። መሪዎች የሌላቸው የሚያዳምጡበት ግዜ ነው። በተለይ ደግሞ ልክ እንደ ዛሬ ምሁራን ለሀገር ይጠቅማል ያሉትን ሃሳብ ሲያቀርቡ መሪዎች ማዳመጥ ነው ያለባቸው።

ዛሬ ዶ/ር አብይ ያደረገው ይሄንን ነው። ሁሉም ፅሁፍ አቅራቢዎች በጣም ምርጥ ናቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ የዶ/ር ሰሚር ፅሁፍ እና አቀራረቡ ቀልቤን ገዝቶታል። #በነፃ_ውይይት ፕሮግራም ላይ እንግዳዬ አድርጌ እስክጋብዘው ድረስ ቸኩያለሁ።

ስዩም ተሾመ

4 COMMENTS

  1. እቶ ስዩም እንዳቅሚቲ ዳሜጅ ኮንትሮል ማከናወንህ ነው። አቢይ ተራ መሆኑንና የዝቅተኝነት ልክፍት የተጠናወተው መደዴ መሆኑን ከህክምና ባለሙያዎች ጋር በተካሄደው ስብሰባ ላይ ያሳየው ብልግና በቂ ምሳሌ ነው። ስዩም ተረኛው የወያኔ ከበሮ ከሆንክ ውሎ አደረ። የምመክርህ ለራስህ ክብር ይኑርህ የሚል ይሆናል። በተረፈ ትንሽም ቢሆን ለማንበብ ክሪቲካሊ ለማሰብም ሞክር ሻሎው መሆንህ በያንዳንዱ ጽሁፍህ ይታያል። ሰላም ሁን።

  2. ይስረ ውያኔ ኢሀዲግአሁንም ኢሀዲግና ኦነግ ያለውየለየለት ይአብይ ተበቃ ሆነህየሚቃወመውን ስትሟገትጋዜጠኝ አይደለም መድረክ እንዴት እንድተሰጠህም እይታወቅም የተታሰራችሁት ህዋትን ስለምትጠሉነበር ይሄነውአላማችሁከትግሬ ወደ ኦሮሞአባገነን ዲሞክራሲ የሚለውብአፍ ትጠሩታላችሁ እንጂፈጭሞ አታውቁትም የትጠይቀውንየማታቅ የምትጠላውን አብን ሰው እንዲጠላልህ የንትወ እሳትንም እንደዛው የጮኸንልንህዝብበጠላት የፈርክታማኝነትህን አይቶበቅርቡ የአፈ ቅቤው ቃላ አቀባይ ይሾማኸልየምስራውና የምትጠይቀው ንፃ ሆነህ ሳይሆንበፍን የሱ ቲፎዞሆነነው የሰውሃሳብ የማታስጨርስ አንተ ክላስደሰተህያንተን መሪ የሚቃወም ነገር ለመስማትየማትሻ የሰውሙያ እያራከሳችሁ ስለሆነወደ ቀድሞ ስራሁተመለሱያቺስጎን ኤልቲቭ ጭምርነውግዜ የሰጠውቅል ዱባይሰብራል ነውየሚባለው

  3. Roman and Dave Dost

    ምንም ብትታጠቡ ስዩም ተሾመ ስብእና እትደርሱም:: ያለአቅማችሁ አትንጠራሩ:: ይህ የኢትዮጵያውያን ውይይት መድረክ ነው:: ስዩም በህውሀት ወናፎች አይረበሽም::
    ስዩም በርታልን ገንቢ አሳቦችህን ጀባ በለን

  4. please don’t censor. commenters have options other than satenaw. never forget that. abugida tried censoring and playing games and ended up losing all its viewers. did you know that? now you know!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.