ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የመኖሪያ ቤትና የመኪና ስጦታ ተበረከተላቸው

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉልህ የሆነ ሚናን ተጫውተዋል፡፡ ታሰረዋል፣ ተንገላተዋል፡፡ እድገት እንዳያገኙና ከስራቸው እንዲባረሩ ተደርገዋል፡፡ ኦሮሞነታቸው ከኢትዮጵያዊነታቸው ጋር ተጋጭቶባቸው አያውቅም፡፡ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ በጉልሀ ተጽፈዋል፡፡ እናም ለእኝህ የተከበሩ ኢትዮጵያዊ ከዚህ ቀደም ለረዥም ጊዜ ተይዞባቸው የነበረውን የፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውን ያገኙበትን የምስጋና ዝግጅት አስመልክቶ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ የመኖሪያ ቤትና የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ተገኝተውበታል።

ክቡር ፕሮፌሰር እንኳን ደስ አሎት!!

ወንድምአገኝ ሲሳይ

 

1 COMMENT

  1. እጅግ በጣም የሚያስደስት ተግበር ነው ፡፡
    ክቡር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ለነጻነትና ለእኩልነት ለከፈሉት ዋጋ ከዚህም በላይ ሽልማት ይገባቸዋል፡፡
    ክቡር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንን ደስ አሎት!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.