የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግፍ ጉዳይ፦ (አያሌው መንበር)

ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከሳምንት በፊት ግቢ ረብሻ ነበር፥ አራት ቀን ሲሰቃዩ ቆይተው ዩንቨርስቲው ይቅርታ ጠይቆ፣ ችግሮችን አስተካክላለሁ ብሎ ግቢ ይገባሉ።

በማግስቱ (ትላንት) ድጋሜ ብጥብት ተነስቶ 6 ተማሪዎች ቆስለው ሆሲታል ሲገቡ፤ 11 የሚሆኑ በሁሉም ዘርፍ ንቁ የሆኑ ልጆችን ታሥረዋል።

ከታች የሚታየው ፎቶ የትላንት ማታ ተማሪዎቹን አዳር የሚያሳይ ነው። የሚቀሩ ቢኖሩም ከግቢ የወጡት ግማሾቹ ወደ ዘመድ ቤት ሲያድሩ፥ ዘመድ የሌላቸው ደግሞ በፎቶ እንደሚታየው ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አድረዋል።

አንዱ ወንድማችን ወደ አዲስ አበባ ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር ተብሏል። ይህ ልጅ ትናንት ሌሊት ነው የተጎዳው ኮማ ውስጥ የነበረ ተማሪ ነው። አሁን ወደ አአ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈር ተብሏል። ሌሎች 5ቱ ሆስፒታል ናቸው።

ቀሪዎቹ ግማሾቾ ቤተ ክርስቲያን ያደሩትም ጭምር ሌሎቹ አሁንም ያለ ምንም ዋስትና ግቢ ውስጥ ይገኛሉ።

አሁንም አጥፊዎችን ከመያዝ ይልቅ ዝም ብለው ግር ግር አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎችን ማፈስ ጀምረዋል።

እስካሁን 10 የአማራ ተማሪዎች እስር ቤት ይገኛሉ።

ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ አመራር ጭምር የሚደርስባቸውን ችግር በደብዳቤ ገልፀዋል።

2 COMMENTS

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.