አባቶች በደምና በአጥንት ሰርተው ባኖሯት አገር ወሮበሎች አይፈንጩባት (ሰርፀ ደስታ)

አብን በብዙዎች ዘንድ ስጋት የሆነበትንም ምክነያት ሳስተውል ለ50 ዓመት አማራ ጠል በሆነ ፖለቲካ በጥላቻና ዘረኝነት የሰከሩ ቡድኖችን እየሰበራቸው ስለሆነ ነው፡፡ አብን ባይኖር ብለን ስናስብ ነውር አይፈሬው የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ በእነ አብይ በኩል ትልቅ ጥፋት በፈጠረ ነበር፡፡ አሁን ስናስተውል በተግባር ስለዜጎች በወኔ የሚንቀሳቀስ ቡድን አብን ብቻ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ላይ ያ ሁሉ ሲሆን፣ በየቦታው የሆነው ሁሉ ሲሆን አንዳቸውም በዜጋ እናምናለን ምናምን የሚሉ ቡድኖች ቃል ትንፍሽ አላሉም፡፡ ከዛም በላይ ይሄንኑ የኦሮሞ በጥላቻና ዘረኝነት የተለከፈ ሴራን በአዲስ አበባ ላይ ታላቅ ችግር በፈጠረበት ወቅት ይሄን እንቃወማለን በለው የተነሱ የእነእስክንድርን እንቅስቀሴ ሲያወግዙ እነ የዛሬዎቹ የዜጋ አሳቢዎች እኔ ሴፉ ግርማ አላፈሩም፡፡ አብን ራሱን የአማራ ቢሊም በተለያዩ ቦታዎች በዜጎች ላይ የሚከሰቱ ግፎችን በማውገዝና የእነ የለውጥ ሀዋሪያ ነኝ የሚለውንም ቡድን ወጥሮ የያዘው በተግባር አብን ብቻ ነው፡፡ ለኢትዮጵያንና የቀደሙ አባቶችንም ታሪክ በቁጭት የሚናገር አብን ነው፡፡ ማንም እንደ እንጉዳይ ከየተም መጥቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲከኛና አዋቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ ከጥንትም ጀምሮ የመንግስታዊ መዋቅር አስተሳሰብ ያለባት አገር ነች፡፡ ይሄን የማይገባው ወሮበላ የ60ዎቹ ትውልድ ተነስቶ ዛሬ ወደ 50 ዓመት የተጠጋውን መንግስታዊ አሰራር እስኪጠፋ ድረስ፡፡ የመንግስታዊ መዋቅር አስተሳሰብ በደርግ የተሻለ ነበር፡፡ አነሰም በዛም ከቀደሙት የቀረ ትንሽ ስለነበር፡፡ በመለስ ጊዜ ዘቀጠ ግን አሁንም ይሻል ነበር፡፡ በኃይለማሪያም ጊዜ ከእነጭርሱ ጠፋ፡፡ ከዛ እነጀዋርና ምንምንቴዎች መቦረቂያ ሆነ፡፡ በአብይ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሲል እውንም ወደነበረ ክብሯ ይመልሳታል ስንል የለየለት የ50ዓመት በጸረ-ኢትዮጵያና አረመኔነት የኖረን ቡድን ዋና አራጊ ፈጣሪ ሆነ፡፡

ኢዜማ እያለ ራሱን የሚጠራው ቡድን ራሱን ይፈትሽ፡፡ ማንም አለም ላይ የተሳካለት አገር ታሪካዊ እውነቶችን ክዶ አዲስ እፈትራለሁ በሚል አደለም፡፡ ታሪክ የሌላቸው አገሮች ናቸው ዛሬ ዉሉ የጠፋቸው፡፡ በየአገሩ አስተውሉ ለቀደሙ የአገር ባለውለታዎች ትክክለኛውን ክብር የሰጡ አገራት ብቻ ዛሬ በክብርና በሠላም ይኖራሉ፡፡ አንድም አገር ከዚህ ታሪክ ያፈነገጠ ዛሬ ከድህነትና ኋላቀርነት አለማምለጥ ብቻም ሳይሆን ለመኖርም በማይችልበት ሁኔት እየታመሰ ነው፡፡ ሚኒሊክ በሠራት አገር የሚሊክ ጠላትና የኢትዮጵያ ጠላቶች አጎብዳጅ ሆነህ አገር መምራት ቀርቶ ለራስህም አትሆንም፡፡ መጀመሪያ የታሪክ፣ ሕዝብና አገር ቁጭት ይኑርህ፡፡  በመጀመሪያ ዜጋ ያልሆኑ ሰዎች የኢትዮጵያ ዜጎች ዋስትና ሊሆኑ ማሰብ በራሱ ምን ያህል ነውረኝነት እንደሆነ አለመስተዋል ያሳዝናል፡፡ ኢዜማን በዋናነት ዛሬ እየመሩ ያሉት የኢትዮጵያ ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች መሆኑ በራሱ አሳዛኝ ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የአገርንና ሕዝብን ክብር ቢረዱና መንግስታዊ አስተሳሰብ ቢኖራቸው ለኢትዮጵያውያን ወኪሎች እኛ መሆን አለብን ባላሉ ነበር፡፡ እኔ ከማንም ጋር የግል የሆነ ችግር የለብኝም፡፡ እውነቱ ግን መንግስት፣ ሕዝብ ልዋላዊ አገርን የማይቀበል አስተሳሰብ ያላቸው ከ60ዎቹ ጀምረው ሲያበላሹ የኖሩት ሳያንስ ዛሬም ሙጥኝ ማለታቸውን ነውር ሆን አልታያቸውም፡፡

የዜግነት ጎዳይ ዛሬ የረከሰ ነው እነ አብይ በኦሮሞነት ዜጎች ያልሆኑ ግለሰቦቹን በመንግስት አስተዳደር መዋቅርና ወሳኝ ቦታዎች ሰይመው እንዳለ ደርሰንበታል፡፡ የቱንም ያህል ኢትዮጵያን ወዳድ ቢሆን በኢትዮጵያ ጉዳይ አራጊ ፈጣሪ ልሁን ብሎ የሚነሳ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለውን እንደመንግስታዊ አሰራር ነውር ነው፡፡ ይሄን አስተሳሰብ እኮ ስሌለው ነው የ60ዎቹ ትውልድ አገር ማለት ምንም ማለት እንደሆነ የማይገባው፣ መንግስት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የማይገባው፡፡ እንደ ብዙ አገሮች ሕግ ዜግነት ብቻም በቂ አደለም፡፡ መሠረታዊ የሆነ የአገርና ሕዝብ ቁጭትና እልኸኝነትን ጭምር የሚጠይቅ ነው መሪነት፡፡ ፑቲን በራሺያ በመሪነት ለበርካታ ዘመን የቀጠለው ስለራሺያ ጽኑ ቁጭትና የራሺያን ክብር መጠበቅን ከሁሉ ቅድሚያው ስለሆነ ነው፡፡ እነ የልሲን ዜጎች ነበሩ፡፡ እንደራሺያም ቁጭቱን አላጡትም ግን ቮድካ ያታልላቸው ነበር፡፡ እንግዲህ አገር መምራት አገር ወዳድ መሆንም ብቻ አደለም፡፡ ታሪክን፣ ክብርን የሚቆጭ መሆንን ግድ ይላል፡፡ በዘፈቀደ ከየትም ሜዳ መጥቶ ሥልጣን መያዝ ከተጀመረ ወዲህ ነው አሁን እየሆነ ያለውን ያየንው፡፡  ስለዚህ ማንም ይሁን ማን የቀደሙ አባቶችን ታሪክ እያጣጣለ በኢትዮጵያ ምድር ገዥ ሆኖ ሊኖር አይችልም፡፡ ማጣጣል አደለም ታሪካቸውን የማያከብር ሁሉ፡፡ ኢትዮጵያ ነውረኛ አገር አልነበረችም፡፡ ምንንም በዛሬው ብሄሮ ሳይሆን በአደረገላት ታሪኩ ነው የምታውቀው፡፡ ዮሀንስን በትግሬነት፣ ሚኒሊክን በአማራነት ጦናን በወላይታነት ጎበናን በኦሮሞነት አደለም የምታውቃቸው፡፡ ከብር ላላቸው የአገር ባለውለታዎች ክብር ሳትሰጥ በወራዳ አስተሳሰብ በመንገደኛ ሕግ አገር ልትመራ አትችልም፡፡

እኔ በአብን ያለኝ ስጋት ሌሎች ከሚያስቡት በተቃራኒው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ማንነቱ ላለፉት 50 ዓመት እየተገፋም ብዙ ግፍ እየደረሰበትም ኢትዮጵያዊ ማንነቱንና ወኔውን ማቆየት የቻለውን የአማራውን ሕዝብ እንደ ኦሮሞ እንዳያመክነው ነው፡፡ ዛሬ የምናየው የብዙ ኦሮሞ አስተሳሰብ ሌላው ቀርቶ በደርግ ጊዜ እንዲህ አልነበረም፡፡ ጀግኖችን ማዋረድና ኢትዮጵያዊነትን እንዲጠላ ያደረጉትን ጆሮ ሰጥቶ ስለሰማ ዛሬ ሌላ ቀርቶ የኖረበትን የክርስትናም በሉት እስልምና እምነቱን ትቶ የተስፋዬ ገብረአብ መጽሀፍ አምላኪ እሰከሚሆን ደርሷል፡፡ ስርዓትና ሕግ የሌለው በነውር የለሽ ስግብግብነት በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመንጠቅና ለመግደል በሚያሰፈሰፉ ቡድኖች እየተመራ እውነትን ማየት ተስኖታል፡፡ ከዚህ በታች የምታዩት በኦሮሞ ሕዝብ ሥም የሚቁምሩ ቡድኖችን ነው፡፡ ዛሬ ስለእነዚህ ሁሉ ማንም ትንፍሽ አይልም፡፡ ይልቁንም በይፋ ባንክ እየዘረፈና ሕዝብ እየገደለ ያለውን አረመኔ ቡደን ጸጥ ነው ያለው ሁሉም፡፡ ስለ አብን ግን ብዙ ይወራል፡፡ አብንን ኢትዮጵያዊ ክብርን እንዲጠብቅ እንጂ ከዚህ ከአላፈነገጠ ብዙዎች እንደሚከተሉት ስጋት የሆነባቸው ይመስላሉ ዛሬ ስለ አብን የሚጮ ሁት፡፡ የኦሮሞ በድኖች

 1. የኦሮሞ ዲሞክራሳዊ ፓርቲ (የኦነግ የውስጥ አርበኞች የሞሉት)
 2. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሸኔ
 3. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቶኩሜ
 4. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃማ ጪዎምሳ
 5. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አቦ
 6. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃማ ጂጂረማ
 7. የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ
 8. ቢዮሌሳ ኦሮሞ ፓርቲ
 9. ፓርቲ ቢሊሱማ ቢዮሌሳ ኦሮሞ
 10. አዳ ቶኩማ ኦሮሞ
 11. አዳ ዲሞክራታዋ ኦሮሞ
 12. ኮንግረሲ ወራቅሳ ኦሮሞ
 13. ፓርቲ ሲርና ገዳ
 14. ፓርቲ ዲሞክራታዋ ቶኩማ ኡመታ ኦሮሞ
 15. ፓርቲ ወለቡማ ኦሮሞ
 16. አዳ ቶኩማ ቢሊሱማ ኦሮሞ
 17. አዳ ቶኩማ ወለቡማ ኦሮሞ
 18. ወዘተ……….

እንዲህ ነው የምትሆነው ማንነትህ ሲጠፋ የማንም ሰፈረተኛ ተነስቶ ፖለቲከኛ ይሆንልሃል፡፡ ማንነትና ሥርዓት የሌለው ያደርጉሀል፡፡ ሰሞኑን የኦሮሚያ ሲኖዶስ መቋቋም አለበት የሚሉ ሰምተናቸዋል፡፡ እነጀዋር የሲኖዶስ አስመራጭ ናቸው፡፡ እንግዲህ እንዲህ ነው የምትሆነው ማንነትህን ለሌሎች ለወሮበሎች አሳልፈህ ሰጥተህ የአባቶችህን ታሪክ ከወሮበሎች ጋር አጥላልተህ ለወደድከው ወራዳነት መገዛት ግድ ነው፡፡ ሐይማኖትን ሳይቀር እነሱ ይጽፉልሀል፡፡ ለዛም ነው ተስፋዬ ገብርዓብን ማምለክ ግድ የሆነብህ፡፡ አሁን ሲኖዶስ መስርትና እንግዲህ ሞክረው፡፡ በፕሮቴስታነት ስም ገብተው ባዶ መዋቅር የሌለው ማንነትን ያወረሱት ናቸው ዛሬ የሚነግዱበት፡፡ ተቋማዊ ስርዓት ያላቸው እምነቶች ላይ ብዙ ግፍ የሆነው በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡ በኦርቶዶክሱም በእስልምናውም የሆነው ይሄው ነው፡፡ ተቋማዊ ስርዓት ስላላቸው ለወሮበሎች በጣም አደገኛ በመሆናቸው ከውስጥ ገብተው ሲያተራምሱ ኖረዋል፡፡ የአብይ የአሁን ጠጋጠጋ ማለትን በጥንቃቄ ልንስበው ይገባል፡፡ አላስፈላጊ የሆነ ፈንጠዝያ በእምነት አያስፈልግም፡፡ ዘበናዊነትም አያስፈልግም፡፡ እምነት የሰዎች ልጆችን በስርዓት እንዲሄዱ ትልቁን ድርሻ የሚያበረክት ነው፡፡ ክርስትና፣ እስልምና፣ ቡዳ፣ ጂው፣ ሂንዱ እነዚህ የአለምን ሕዝብ ስርዓት እንዲኖረው ትልቅ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ ነውርን መጠየፍንም ሁሉም ያስተምራሉ፡፡ በሞራልና በብልጭልጭነት አይሁን፡፡ የሚሊኒየሙ የሙስሊሞች አፍጢር ከነበረው ችግር አንጻር እንደ ነገሮች ፈር በመያዛቸው እንደዝግጅት ከመልካምነቱ አስባለሁ፡፡ የዚያንው ያህል ግን የአላስፈላጊ ዘበናዊነትና የመተያያ ፌሽታ አይነት ገጽታ ከእምነቱ ስርዓት ውጭ እንዳይለመድ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡ ሰሞኑን በቢቸና መስኪድ ተቃጠለ የሚል ወሬን ሰማሁ፡፡ ይች ቁማር በዝታለች፡፡ ድሮ ቤተክርስቲያን ነበር የሚቃጠለው፡፡ አላዋጣ አለ መሰለኝ አሁን አሁን መስኪድ ማቃጠል የተለመደ ሆኗል፡፡ በተለይ ደግሞ አማራ ክልል ላይ ነው ዋና ኢላማ የተደረገው፡፡ ቁማሩ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬ ላይ የአማራ ክልል ሙስሊሙና ክርስቲያኑ በአማራነት አንድ ሆኖ አስቸግሯል፡፡  አሁን አሁን በኢትዮጵያዊነት ከክርስቲያኑ ሙስሊም አማራውና ጉራጌው ዋና መሪ ሆኗል፡፡ ይሄ የእግር እሳት የሆነባቸው ብዙ ናቸው፡፡ ከላይ የዘረዘርኳቸው ቢያንስ በአብዛኞቹ ይሄን እንዴት እንደሚጠሉት እናውቃለን፡፡ ዛሬ በዘረፋና በመዋቅር ገንዘብ እየተላለፈላቸው በተለያዩ ቦታዎች ችግር በመፍጠር ላይ ዘምተዋል፡፡ በተለይ አማራ ክልልን ለ50 ዓመት የገነቡት የጥላቻና የዘረኝነት አስተሳሰብ ሊያወድምባቸው የሚነሳ ቡድን ይኖራል ብለው ስለሰጉ ክልሉን እርስ በእርስ ለማጋጨት ሁሉንም ሞክረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የገቢዎች ሚኒስቴር ጉዳዩ ከገንዘብ በላይ  ትልቅ የደህንነት ስጋት ነው፡፡

ክብር ለቀደሙ አባቶች! ኢትዮጵያውያን የአባቶቻቸውን ታሪክና ክብር መመለስ ግድ ይላቸዋል!

ልዑል አባት እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

8 COMMENTS

 1. ሰርፀ ሰላም! ትገርመኛለህ:: ከወራት ወደሗላ ሄደህ ብትመለከት አ ብ ን ስታብጠለጥል በእጅጉ ታቃውሜህ ነበር:: ከአማራ አብራክ የተፈጠረ አማራ ሁሉ አብንን ሲቃወም ያቅለሸልሸኛል:: አማራ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር የ50 አመታት ትርክት: ድራማና መገፋት ነው አብንን የወለደው:: እንኳንም ተወለደ:: አማራ የሚያሳፍር ታሪክ የለውም:: ስለዚህም ማንነቱን የሚያስከብረውና የተካሄደበትን ዘመቻ የሚያመክነው በአማራነት በመደራጀት ብቻ ነው:: ለአማራ ኢትዮጵያዊነትን ማንንም የፖለቲካ መሪ አያስተዋውቀውም:: አንዳድ የፖለቲካ ነጋዴውች አብንና ኦነግን ሲያመሳስሉ ትንሽ እንኳ ሀፍረት የሌላቸው ደካሞች ናቸው::በተለይ የአማራ ምሁር ተብዬዎች ለመወደድሲይጎበድዱ አማራውንም አዋርደው ለእነሱም ሌሎች ክብር አይሰጧቸውም:: የዜግነት ፖለቲካ አራማጆች አማራ አይደራጅ የሚል አቅዋም ከሌላችው ብዙ ችግር አይታየኝም:: ካወቁበት ኢዜማና አብን ቢደጋገፉ
  ወጤታማ ይሆናሉ::

 2. “በየአገሩ አስተውሉ ለቀደሙ የአገር ባለውለታዎች ትክክለኛውን ክብር የሰጡ አገራት ብቻ ዛሬ በክብርና በሠላም ይኖራሉ፡፡ ” ሰርፀ ደስታ።
  በሰርፀ ደስታ ሎጂክ ዛሬ ጀርመን ታላቅ፣ ሃብታም እና የተከበረች ሃገር የሆነችው ለቀደሙ ናዚዎችዋ ክብር ስለሰጠች ነው ማለት ነው! You can worship your neo-fascists in the name of አብን (NaMA) in Amhara Kilil, if neo-fascism is what the Amharas think would serve their interests. Lest they try to extend their fascist activities beyond the Amhara borders, it would call for a civil war, and the destruction of your imiyie Ityopiya. And the likes of you, the Vuvuzelas of ABN, should restrict their dirty mouths and fingers to Amhara issues. Matters concerning other ethnics is not your business! In case you are not still aware of, Ethiopia does not solely belong to the Amhara!

  ABN should first see how it would raise the people in Amhara region out of the excruciating poverty and backwardness, before talking about people in other regions! If Amharas want to live as equal citizens with other ethnics in the country, they have to first respect the rights of others (including those in the Amhara Kilil). Shouting ‘akaki zeraf!’ and demanding for the further granting of old previleges, while demeaning and belittling other peoples, calls only for further hatred and violence against Amharas!

 3. “While seeking a more just, a more peaceful, and a more truthful society, it is important that the work of liberation, reconstruction, and reharmonization is (self)consciously and reflexively done. This work requires a radical rethinking of the terms of reconstituting the polity (that may become a harmonized common homeland for all). Assimilation to, or integration with, an Ethiopia NAMED, MADE, and IMAGINED only by Abyssinian conquerors and their descendants will not be enough as it condones (even celebrates)the foundational violence and the intractable injustice thereof.”
  Tsegaye Ararssa

 4. Thanks Dr . Sertse.
  I always try not to miss reading your
  Posts . I don’t live in Ethiopia ; but ,thanks
  To the modern technology I am able to
  See and read what is going on in our Country through the social media.
  That is why I have great respect to you and some other honest Ethiopians.
  Last time , when you comment on NAMA
  ( ABN ) , I was not comfortable with some
  Of your points and I have tried to convince
  Myself that you might misunderstood
  NAMA’s core idea when they talk about
  Amhara nationalism.
  Brother Sertse….. I am a believer of
  Ethiopian unity with realistic democracy.
  To achieve democracy and maintain
  Respect among the different language
  Speaking people in Ethiopia, we need to
  See and have a balanced power at least
  Among the most populous and historically
  Influential ethnic groups ; and that is
  Where all peace and true democracy
  Loving Ethiopians desperately need a kind
  Of organization like NAMA ( ABN ).
  At the present Ethiopia, where the nation
  Is infested with racism and hatred and
  The so called unity parties are weak and
  Unpopular, a party like NAMA is a blessing
  For Ethiopia and its people . Because, this
  Party is truly the only equalizing force
  In the Ethiopian political field.
  Whoever cry and spread negative things
  About NAMA has either a hidden agenda
  Or doesn’t understand how complex the
  Current Ethiopian political situation is.
  Honest Ethiopians must protect ,support
  And watch and correct whenever we
  Believe the NAMA leadership make mistakes. That is our obligation.
  Thanks Dr. Sertse one more time.

 5. አባ ጫላ የአማራ ጨቋኝነት የፈጠራ ድርሰት ጊዜው ያለፈበት ነው:: አማራ እንደእንሰሳ ክልል የለውም:: የአማራ ክልል ኢትዮጵያ ናት:: ማንንም ኢትዮጵያዊ በዬትኛውም የኢትዮጵያ ክልል የመኖርና ሀብት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ ነው:: ካልተጠበቀ ተደራጅቶ ያስጠብቃል:: ኦሮሚያ የኦሮሞ የግል ርስተ ጉልት አይደለችም:: ይህን ካላወቅህ ትምህርት ቤት ገብተህ ተማር:: በዚህ ዘመን በጉልበት አሸንፋለሁ የሚል ቅዠት ውስጥ ብትወጡ ይሻላችሗል:: ማንም የሚገዛልህ የለም:: ማንም አማራ አማራ እንድትሆን የሚፈልግ ጅል የለም:: የአማራ ህዝብ እጅግ ብዙ ነው:: እንደብዛቱ መብትና ፍትሀዊ የሀበት ተጠቃሚነቱ መረጋገጥ ይኖርበታል:: አማራ ትእግስተኛ ስለሆነ ዝም ስላለ ብዙ ጨፈራችሁ:: ዛሬ ለአማራ ህዝብ ክብር አብን ተወልዷል get used to it. NAMA is here to stay. ያለፈው ትርክትና ድራማ ወቅቱ እልፏል::

 6. ክብር ለእግዚአብሔር ይግባው !ክፉን ከበጎ እንድንለይ ማስተዋይ እእምሮን መምልከቻ አይን ያበጀልን ለዘለአለምይመስገን!እስራኤል መከራና ግፍ የተመለከተ አምላክ ሙሴንነበር ያነሳው!አዎ ፈሪያእግዚአብሔር ያደረበት የአማራ ህዝብ ወያኔና ኦነግ እዲሁም እንደ አባ ጫላ እንደነ ጁሀር የመሰሉ ርኩሶች ሰይጣኖች ክቡሩን ሰው መከራ ላይ ሲጥሉ ብድራቱን የሚከፍል አምላክ እንዳለ እንደሚመለከትም ጨርሶ የዘነጉ አውሬዎች ነበሩ አሁንም ናቸው!ያ የግፍ ዘመን ከቶ ላይመለስ አልፎ በፈጣሪው የተጎበኘ ደጉ አማራ ህዝብ በእርሱ ሃይል ተነስቶል!እመኑኝ ድልም ያደርጋል ሁሉም ነገር በእርሱ ዘንድ አለና!አብንም ሆነ አማራውን ያነቃ ያነሳ የፈጠረ ማስተዋልም የሰጠ አምላክ በደልን በቃ ብሎ በመላው ኢትዮጵያ በአለምም ተበትነው ያሉ ዘሮቹ ተነስተዋል!!እነ አባጫላ ትግል ሜድው እንደ ዳዊትና ፈርኦን እንግጠም ምርጫው ከሆናችሁ ምርጫችሁን አክብረን ውንጭፍአችንን ይዘን ለነፃነት ዳግም በኦነግ ላንታረድ ላንሰደድ በወያኔም መከራ ዳግም ላንበደል አብን እንድ ሙሴም እንደ ዳዊትም ሃይል በቃ ተነስተናል!እንኪያ ሰላምታው ትዝብትን ጥላቻን ከማትረፍ በስተቀር!!

 7. @ተሱማ፣
  “የአማራ ጨቋኝነት የፈጠራ ድርሰት ነው” እና “የአማራ ክልል ኢትዮጵያ ናት” የሚሉት ዐረፍት ነገሮችህ አይጋጩም? ሌላው ህብረተሰብ ሳይጨቆን ሙሉ ኢትዮጵያ የአምሃራ ክልል የሆነችው እንዴት ነው? እንደአህያይቱ ስታናፉ ከኋላ የሚወጣውን ማስተዋል እንኳ አትችሉ! “ኦሮሚያ የኦሮሞ የግል ርስተ ጉልት አይደለችም” አማራ ክልል ግን የአማራ ብቻ ርስት ነው አይደል? እስቲ አንድ ኦሮሞ ወይም ሲዳማ ወይም አኟክ ባህር ዳር ሄዶ መሬት ይሰጠኝ ቢል እሰዬው ብላችሁ በደቦ ቤት የምትሰሩለት ታስመስላላችሁ! የመኖር መብት ሌላ፣ እንደ ሰሜነኞች (ኦርቶዶክስ ቤ. ክ. ጨምሮ እንደሚያደርጉት) ነባሩን ነዋሪ አፈናቅሎ መሬት መውረር ሌላ ነው። አዎ የኦሮሚያ መሬት የኦሮሞዎች የወል ርስተ ጉልት ነው! መሬት የሌለው ህዝብ ሃገር ሲኖረው አይተህ ታዉቃለህ?? ዐዎ፣ ኦሮሞን፣ ጋምቤላን፣ ሲዳማ፣ በኒሻንጉሉን ሃገር አልባ ለማድረግ ከወያኔ ጋራ በተቀናጀ መልክ ስትሰሩ እንደነበር እናዉቃለን። የደቡቡ ጭቁን ህዝቦች ትግል ሃገሩን ለማስመለስ እኮ ነው፣ እንደናንተ የፖለቲካ ስልጣን ለመሻማት ወይም ሌላው ላይ ጌታ ለመሆን አይደለም! ገባህ?

  Nama is working not for the respect of Amhara rights, but as it has demonstrated in its short existence, it is striving to suppress the right of others, a Nazi ideology! That is what we are against.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.