‹‹አብን ለአማራ ሕዝብ ብቻ የቆመ ፓርቲ አይደለም። የትኛውም ዜጋ ፍትሕ ሲጓደልበት የሚጠይቅ እና የሚሠራ ነው።›› አቶ መልካሙ ሹምዬ

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 17/2011ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየመከረ ነው።

በምክክሩ የአማራ ሕዝብ ጨቋኝ እንደሆነ ሲነገር መቆየቱና አማራ በሁሉም ዘርፍ ተወካይ እንዳይኖረው መደረጉ ተመላክቷል። ‹‹የነበረው ሥርዓት ፀረ አማራ ነው፤ ይህን ያመጣውም የብሔርተኝነት ፖለቲካ መጣመም ነው›› የሚሉ ሐሳቦችም ተነስተዋል።

የአማራ ብሔርተኝነት መመሥርት የአማራን ጥቅምና ኅልውናው አስጠብቆ ከሌሌች ብሔረሰቦች ጋር በእኩልነት የመኖር ሐሳብ እንደሆነም ነው በምክሩ የተገለጸው።

‹‹አብን ብሔርን መሠረት አድርጎ የተነሳ ቢሆንም ሌሎችን የሚጎዳ፣ የሚውጥ፣ የሚያስገብር ሳይሆን መነሻውን እኩልነት በማድርግ በእኩል ለመኖር የሚያልም ነው። ሌሎችን ብሔረሰቦች የመግፋት ዓላማ የለውም። ይህ ዓይነት መርህ አዋጭም አይደለም›› ያሉት የንቅናቄው የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መልካሙ ሹምዬ ናቸው።

አቶ መልካሙ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የንቅናቄው መሰሶ እንደሆነና መዝረፍና መቀማት አስፈላጊ ባለመሆኑ በፍትሐዊ መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚሠራም ተናግረዋል። ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሕዝቦችን በጠላትነት አንፈርጅም፤ ጠላት ሕዝብ የለንም እህት ወንድም ነው ያለን። አብን ፍትሕ፣ ዴሞክራሲ እና እኩልነት መገለጫ መንገዶቹ ናቸው›› ነው ያሉት።

የአማራ ብሔርተኝነት በጎጥ ሳይከፋፈል፣ ከኢትዮጵያዊነት ሳያፈነግጥ፣ ለፍትሕ እና ለእኩልነት የሚሠራ መሆኑንም አቶ መልካሙ ተናግረዋል። የፌዴራሊዝም ሥርዓቱ ተስተካክሎ ሁሉንም ብሔረሰቦች እኩል ተጠቃሚ እንዲያደረግ መሠራት እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት። ሁሉም ሕዝብ የሚሳተፍበት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት መጽደቅ እንደሚገባውም ነው የተናገሩት፡፡

‹‹አብን ለአማራ ሕዝብ ብቻ የቆመ ፓርቲ አይደለም። የትኛውም ዜጋ ፍትሕ ሲጓደልበት የሚጠይቅ እና የሚሠራ ነው›› ብለዋል አቶ መልካሙ በምክክር መድረኩ ባደረጉት ንግግር።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ – ከጎንደር

11 COMMENTS

 1. የስልጡን ህዝብ መለያ ከራሱ ኣልፎ ለሌላው ህዝብ የሚያስብ መሆኑ ነው።ኣብን የኣማራውን ለመወከል ግቡ ኣርጎ የተነሳ ቢሆንም የሌላውም መብት እና ነጻነት ይመለከተኛል ማለቱ ከኣባቶቹ የወረሰውን የሀገር ዋልታነትን ያሳያል ።
  ባንድ ወቅት ኣንድ ታዋቂ የጉራጌ ኣባት ” ኣማራ አገር ለማቅናት በሚዝምትበት ወቅት በሚያርፍበት ቦታ ሁሉ ኣጋሰሶቹ / ብቅሎ፣ ኣህያ የመሳሰሉት / መጀመሪያ ዉሃ እና መኖ እንደቀረበላቸው ሳያረጋግጥለራሱ እህል ዉሃ ኣይቀምስም ነበር”ሲሉ ኣጫውተውናል። ኣማራ እንኩዋን ለሰው ልጅ ለእንሰሳ ያለውን ክብር እና ኣሳቢነት ለማሳየት ነው ።
  ኣካሄዳችሁ ከስሜታዊነት ወጥቶ በእውቅት ላይ፣ በጥናት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ፖሊሲያችሁን ፣ፕሮግራማች ሁን…..ወዘተ የሚገመግም ፣ የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ የሚያቀርብ ከተለያየ ሙያ የተውጣጣ ኣንድ የኣማራ THINK TANK ብታቁዋቅሙ ለወደፊት እርምጃችሁ ይበጃል።
  God bless Ethiopia !

 2. ገመዳ የተባልክ ገመድ:: እንዴት አድርገህ ነው እብን የምታጠፋው? አቅሙስ አለህ? አማራው የምደራጀት መብት የለውም? ስለናዚ ታሪክና አመጣጥ ምን እውቀት አለህ ? ጭቃ ከመቀባት ውጪ! I understand NAMA is getting into your skin ..thank God , Amahras have finally a voice in Ethiopian affairs
  የአማራ ነገር እያብከነከነህ ኑር:: የምትለውጠው ነገር ግን አይኖርም አማርኛው አይገባህም if I just say few words in English ( the language you worship) you may understand me. You are a bonehead who doesn’t qualify to criticize NAMA

 3. ‹‹አብን የትኛውም ዜጋ ፍትሕ ሲጓደልበት የሚጠይቅ እና የሚሠራ ነው።›› Oh yes! It has shown us that in real practice in Wallo Kamisie, in Gumuz districts bordering Amhara Region and many other places!

  A nationalist organization struggles for the respect of the democratic rights of its constituency (nation or people). An ultra-nationalist (or nazi) organization like NAMA fights to suppress the rights of others! That is the difference! What ABN is doing, Fighting to reimpose the old Amhara-centered authoritarian system that tried to obliterate the identities and cultures of other nations and nationalities in Ethiopia, is not a democratic right!

 4. Abawirtu has shown clearly what his real views are on his comment to the writing by dr. Girma dadhi aka serse desta. You have disqualified yourself my brother. You are enemy to oromo struggle.

 5. አይተ ገመዳ/ አይተ ጫላ
  ሁለታችሁም 95 በመቶ ወያኔ እንደሆናችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ወያኔ አማራ ሲደራጅ ብቻ ሳይሆን ሰሙ ሲጠራ እንደ ቢጫ ወባ ያንቀጠቅጣታል፡፡ ያ የሶፋ ውሻ የሚያክል አጎታችሁ ለገሠ ጨናዊ በህዝብ ፊታ ሲቀባጥር አንድ አማራ ቢጮህበት ናላው ፍንድቶ ሞተ፡፡ ስለዚህ አማራ ተደራጅቶ አይደለም እንዲሁ ስሙን ስትሰሙ ያንቀጠቅጣችኋል፡፡ የሚገረመው ደግሞ ልክ ብሎኬት ማምረቻ ውስጥ እንደወጣ የምትሰጡት አስተያየት አሰልችና ተመሳሳይ ምንም አመክንዮ የሌለበት ነው፡፡ የአልዚመር ብሽተኛ እንኳ ከእናንተ በተሻለ ነገሮችን ያስተውሰል፡፡ ለማንኛውም ምደረ ቁልቋላም ቁለቋልህን እየበላህ እዛው ሰፈርህ ትኖራታልህ፡፡ ዱቄታም፡፡

 6. Mastewal፣ መልክ ጥፉን በስም ይደግፉ እንድሚባለው መሆኑ ነው? አስተዉለህ ሞተሃል! ስለ እኔ ማንነት ምን አስጨነቀህ፣ ስለጻፍኩት ጉዳይ መልስ መስጠት ስለማትችል ስድብ መረጥክ። Why should it matter who I am or what I eat or how I look like? What is you counter-argument to the issues at hand: ABN (NAMA) is a fascist organization, whose aim is to reimpose the old Amhara-centered authoritarian system that tried to obliterate the identities and cultures of other nations and nationalities in Ethiopia.

 7. @Abawirtu; enyumaa kee saaxilte! Nafxanyota walin Oromo arrabsita; yeroo isaan tuqaman ammoo burra karayyuu! jetta! Kan Obbo Gammadaan tarreesse isuma isaan jechaa bahani dha. Itti siif dabaluu?
  ABN is not only ultra-nationalist, it is blasphemous too!
  እየሱስ ክርስቶስም የአማራ ስነ ልቦና አለው!
  ሰማይ ቤትም መላዕክት መለኮታዊ ቋንቋችን አማርኛ ይጠቀማሉ!
  etc

 8. Mastewal
  ማስተዋል እውነትም ማስተዋል:: አፌ ቁርጥ ይበል! እኔ ትውልዴ አማራ ብሆንም የስጋ ዘመዶቼ በሙሉ ኦሮሞዎች ናቸው:: ኦሮሞ ኩሩና አፍቅሪ ህዝብ ነው:: በኦሮሚያ ከ10 ሚሊዮን የበለጠ አማራ ተጋብቶ ተቀላቅሎ ይኖራል:: የመለስና በረከት ሰይጣንዊ ከፋፋይ አጀንዳ አፈር ድሜ በልቷል:: ህውሀት አማራ 24 ሰአታት በሙሉ ኢትዮጵያዊነት እስክስታ እንዲያዜሙ ይፈልጋሉ:: ለማጥቃት ይመቻልና ነው:: ዛሬ ለአማራ እሰዋለሁ የሚል አብን ተወልዷል:: ይህ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል:: ልክ እንደ ብአዴን የሚጭኑት አህያ አይደለም:: ጫላ ወይንም ገመዳ በደመ ነፍስ የሚዳክሩት አማራንና ኦሮሞን እንደገና ለመለያየት ነው:: ብቻቸውን አደሉም ሌሎችም የፖለቲካ ደላላ ኢትዮጵያውያን ተብዬዎች አማራ እንዳይደራጅና አንገቱን ደፍቶ እንዲገዛ ይዳክራሉ:: እውነተኛ አንድነት በኢትዮጵያ የሚገነባው አማራ መብቱን ሲያስከብር ነው::

 9. The so called Ganada, maybe u came from another planet, devil sprit. Are u belong to TPLF, fanatic ormyians like Juwar group or what? Maybe ur destiny go to not heaven. No one can get it let alone ur stupid view.
  መዘባረቅ የትም አያደርስም፡፡ ሁሉም የሚጠቅመውን ያቃል፡፡ የኦሮሞ ህዘብ ከመላ አገሪቷ ጋር አብሮ የሚኖር ነው፡፡ Don’t waste ur time.

 10. @ተሰማ i strongly share your idea
  ————————
  i shall present it as it is;

  Mastewal
  ማስተዋል እውነትም ማስተዋል:: አፌ ቁርጥ ይበል! እኔ ትውልዴ አማራ ብሆንም የስጋ ዘመዶቼ በሙሉ ኦሮሞዎች ናቸው:: ኦሮሞ ኩሩና አፍቅሪ ህዝብ ነው:: በኦሮሚያ ከ10 ሚሊዮን የበለጠ አማራ ተጋብቶ ተቀላቅሎ ይኖራል:: የመለስና በረከት ሰይጣንዊ ከፋፋይ አጀንዳ አፈር ድሜ በልቷል:: ህውሀት አማራ 24 ሰአታት በሙሉ ኢትዮጵያዊነት እስክስታ እንዲያዜሙ ይፈልጋሉ:: ለማጥቃት ይመቻልና ነው:: ዛሬ ለአማራ እሰዋለሁ የሚል አብን ተወልዷል:: ይህ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሯል:: ልክ እንደ ብአዴን የሚጭኑት አህያ አይደለም:: ጫላ ወይንም ገመዳ በደመ ነፍስ የሚዳክሩት አማራንና ኦሮሞን እንደገና ለመለያየት ነው:: ብቻቸውን አደሉም ሌሎችም የፖለቲካ ደላላ ኢትዮጵያውያን ተብዬዎች አማራ እንዳይደራጅና አንገቱን ደፍቶ እንዲገዛ ይዳክራሉ:: እውነተኛ አንድነት በኢትዮጵያ የሚገነባው አማራ መብቱን ሲያስከብር ነው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.