ራያን አስጨፍጫፊው ሰው ጌታቸው ረዳ – ያሲን መሐመድ

“ጌታቸው ረዳ ትላንት “ሽግ ወያኔ” የሚባሉ የመንደር ወሬ ለቃሚዎችን ጫካ ውስጥ ሰብስቦ ሲፎክርና ሲያስፈራራ በዋለ ከሰአታት በኋላ ዋጃ ላይ የተገደሉት ወገኖቻችን ዛሬ ከሰአት በኋላ የቀብር ስነ-ስርአታቸው በቦታ ማሪያም ይፈጸማል” Agezew Hidaru
—-
የትናንቱ ስብሰባ Tazeze Fekadu
———
ጌታቸው ረዳ ፈርቷል፡ ተስፋ ቆርጧል፡ ህዝባችን መማፀን ጀምሯል፡ በሶስቱም የራያ ከተሞች መንቀሳቀስ አይችልም፡ በህዝባችን ንቃተ ህሊናና አልሸነፍ ባይነት ልቡ ደንግጧል፡ ዛሬ ከከተማ ራቅ ብሎ ዓዲ ባርየ(ዓዲ ሃንጥያ አለፍ ብሎ) የምትባል ትንሽየ መንደር ድረስ ተጉዞ “ሽግ ወያኔ” የተባሉ ከ200 የማይበልጡ ሰላዮች፡ ገዳዮች፡ የጌታቸው ረዳ ካልሲ አጣቢዎችና መረጃ አቀባዮቾን ስብስቦ ውሏል፡፡ ገርጀሌ ሲደርስ ፍርሃት ፍርሃት ይሰማው ነበር፡ ሰውነቱ ልቧል፡ በሶስት አጃቢዎች በመሰብሰቢያ ትንሽየ መንደር ውስጥ ተገኝቷል፡ የተሰብሳቢው ቁጥር ከሚጠብቀው በታች ሆኖ ጨልሞበታል፡ ዘግይቶ የመጣው ተሳታፊ ቁጥር አነስተኛ ነበር፡ ጌታቸው ይባስ ህልሙ ህልም ሆኖ እንዲቀር ፍንጭ ሰጠው፡፡

ተሰብሳቢው ከሶስቱም ገበሬ ማህበራት ከላይኛው ዳዩ፡ ታዖና ገርጀሌ የተውጣጡ “ሽግ ወያኔ” ተብለው የሚጠሩ ሰላዮች፡ ሰርጎ ገቦች፡ በስለላ የተሰማሩ የትህነግ ካድሬዎች፡የድርጅት አባላት፡ ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ የስልጣን ቦታ የቆዩና የባድሜ ታጋዮች በስብሰባው ተገኝተዋል፡፡

ባንዳው ጌታቸው ረዳ በስብሰባው የሚከተሉትን መልእክት ሲያስተላልፍ ውሏል
1ኛ. የፌደራል መንግስት የለም፡ ሙሉ ለሙሉ ፈርሷል
2ኛ. አብይ አህመድ የሚባል መሪ በፌደራል ደረጃ ተቀባይነት የለውም
3ኛ. ኢህዴግ የሚባል ድርጅት በፌደራል ደረጃ የለም፡ ሙሉ ለሙሉ ፈርሷል
4ኛ. ኢህዴግ እና የኢህዴግ መንፈስ ይዘን የቆየነው እኛ ብቻ ነን
5ኛ. ኢህዴግ ዘረኝነት የሚፀየፍ፡ ለፍትህና እኩልነት አበክሮ የሚሰራ፡ የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና በዲሞክራሲ የሚያምን ድርጅት ሆኖ ይሄንን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እያደረገ ያለው እንደ ድርጅት ህወሃት መሆኑ
6ኛ. ሌሎች ክልሎች ለውጡ እውነት መስሏቸው ተቀብለውት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ወደኛ እየመጡ ናቸው፡ ከኛ ጋር ተቀላቅለው እየሰሩ ናቸው
7ኛ. ወደ ነበርንበት የፖለቲካ ስልጣን እንመለሳለን፡ የአገሪቷ ስልጣንም በድጋሚ እንቆናጠጣታለን
8ኛ. በዘር፡ በሃይማኖትና በታሪክ ሊመጡባችሁ ይችላሉ እንዳትቀበሏቸው(ትግሬ ናችሁ ለማለት ነው) የሚል ተማፅኖ ሲማፀን ውሏል፡ መመከትም የሚችል አቅምም መፍጠር ይኖርብናል ሲል የቀቢፀ ተስፋ ንግግር ሲያደርግ ውሏል፡፡
9ኛ. እናንተ እዚህ ያላችሁ በየሰርግ ቤቱ፡ ለቅሶ ቤቱና በየማህበሩ ይሄንን ለህዝባችሁ ንገሩ፡ ህዝባችሁንም አሳምኑ …ወዘተ የመሳሰሉ ተስፋ ቢስ ንግግሮችን ሲሰጥ የዋለ ሲሆን በስብሰባው ወቅት ባነንዳው ፊቱ ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ይታይበት ነበር፡ በየደቂቃው ፌስቡኩን ሲከፍትና ራሱን ሲከታተል ውሏል፡ ፊቱ ፍርሃት፡ ሃዘንና ጭንቀት ይታይበት ነበር፡፡

ባንዳው ጌታቸው ረዳ ያለ የሌለ አቅሙ ለመጠቀም ሞክሯል፡ “የማንነት ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ አስቁመነዋል፡ የማንነት ጥያቄ የሚያነሱት ጫት ቃሚዎች፡ ዱርየዎችና ሱሰኞች ናቸው” ሲል ባንዳነቱን አረጋግጧል፡፡ “የማንነት ጥያቄው የሚያነሱትም ቢሆኑ ለህዝብ የማያስቡና የመንደር ዱርየዎች ለቃቅመን አስረናቸዋል” ሲል ከ2000 በላይ ካለ ጥፋታቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን በሱ ፊት አውራሪነት መታሰራቸውን መድረክ ላይ አረጋግጦልናል፡፡

መድረኩ ላይ የተገኙት ሰላዮች ሲያንጨበጭቡለት ውለዋል ቢሆንም በጌታቸው ረዳ ፊት ሲነበብ የነበረው ፍርሃት፡ ጭንቀትና መርበድበድ ታዝበውታል፡፡ በቦታው መገኘት ከነበረበት ቁጥር በማነስ የጌታቸው ረዳ ቅስም ተሰብሯል፡ በቦታው የተገኘውም ቢሆን የጌታቸው ረዳን እያንዳንዷ መረጃና ንግግር በማደራጀት ልከውልናል፡ በስብሰባው እንዳይሳተፍ ተደርጎ ዳር ሆኖ ሲመለከት የነበረው የአከባቢው ነዋሪ የጌታቸው ረዳን የአስተሳሰብ ድህነትን ሲያረጋግጥ ውሏል፡ ምነው በስብሰባው በነበርኩና ልኩን በነገርኩት ሲል ቁጭቱን ገልፇል፡፡

ጌታቸው ረዳ ከ2000 በላይ ለታሰሩት፡ ከ80 በላይ አካለ ጎደሎ ለሆኑት፡ ከ200 በላይ ለቆሰሉት፡ 16 ወንድሞቻችን ለተገደሉት፡ ለተፈናቀሉትና ቀያቸውን ጥለው ለተሰደዱት ተጠያቂ ነው፡፡ ጌታቸው ረዳ ባንዳ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት በስብሰባው የተገኙት ስም ዝርዝራቸው ይደርሰናል፡ ለህዝባችነም የምናሳውቅና ጠላቱን እንዲለይ የምናደርግም ይሆናል፡፡ ስም ዝርዝራቸውን በማደራጀት የአካባቢው ነዋሪ ትልቅ ተሳትፎ ያደርጋል፡

ራያ ትግሬ ሆኖ አያውቅም!! በባንዳው ጌታቸው ረዳ ተራ ስብሰባ የማንነት ተጋድሏችን ፈፅሞ አይቀለበስም!!

ራያነት ወደፊት!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.