የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ለሁሉም ዜጎች መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ቃል ገቡ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ ሀገራቸውን ከሙሰኞች ለመከላከልም ቃል ገብተዋል፡፡

ሙሰኞችን ከመዋጋት ባለፈ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አዲስ ተስፋ እና ለውጥ እንደሚያመጡም ነው ራማፎሳ በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ ትናንት በቃለ መሃላቸው ያረጋገጡት፡፡በደቡብ አፍሪካ ምድር ሁሉም ዜጋ መሠረታዊ ፍላጎቱ እንዲሟላለት ለማድረግ እንደሚሰሩም ነው በዓለ ሲመታቸውን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር ያረጋገጡት፡፡

በበዓለ ሲመቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ አልታደሙም፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ወደ ፍርድ ቤት በመሄዳቸው ነው፡፡ በዝግጅቱ ለመገኘት ጊዜ እንደሌላቸው፣ ይልቁንም ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ነጻ መሆናቸውን በማረጋገጥ ወህኒ ቤት ላለመውረድ እየታገሉ ስለመሆናቸው አስቀድመው አስታውቀው እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ከአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ኤ ኤን ሲ) ፓርቲ የተወከሉት ሲርል ራማፎሳ በ57 ነጥብ 5 የምርጫ ውጤት ነበር የፕሬዝዳንትነት ፉክክሩን ያሸነፉት፡፡ ይህም ፓርቲው ወደ ሥልጣን ከመጣበት 25 ዓመታት እስካሁን ከነበሩት የፉክክር ውጤቶች ትንሹ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ራማፎሳ እ.አ.አ በ2018 ነበር ጃኮብ ዙማ በሙስና ተከሰው ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ የፕሬዝዳንትነት መንበሩን የያዙት፡፡ በሀገሪቱ የአፓርታይድ አገዛዝ ካከተመበት እ.አ.አ 1994 በኋላም በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ አምስተኛው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡

በአስማማው በቀለ/አብመድ

1 COMMENT

 1. ” የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ለሁሉም ዜጎች መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ቃል ገቡ ”

  You know what ? If right extremists (also called conservatives) in the West hear that, they would shout communism, communism, communism !

  Well, that goal, namely meeting basic demands of the population like food, shelter, free health and free education, was the goal of socialism that the West fought and claims to have defeated it in the year 1989 G.C. or so. Western politicians at the time claimed that “Marx is dead, Jesus is alive”.

  Well, Cuba has such a system, where basic demands of the population are met, for decades. Ethiopia also tried that system over 40 years ago and faced resistance from the West in the form of destabilization, seccession movements and civil war, that consumed much of the country’s resources and prevented it from achieving that goal. The USA and its allies fought Ethiopia to prevent it from achieving that goal.

  But how does South Africa intends to finance that ?

  High taxes means less investment, meeting basic demands means less drive of the population to work hard and achieve something, …
  Also, the Western dominated international organizations like IMF and World Bank would oppose such plan of South Africa. If South Africa is to achieve its goals it must work on regional and global levels. For example it has to be independent from the Western global financial system and the USA global reserve currency.
  By the way, Tanzania tried that also, but unlike Ethiopia the West didn’t destabilize and fight it.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.