ለአብይ አህመድ ምክር ኢትዮጵያን እየገደለ ያለ ውሸት አስመሳይነት ነው! (ሰርፀ ደስታ)

 • አብይ ምክሬን ብትሰማ ጥሩ ነው! በቁምነገር ጊዜ እየሰጠሁ ነው የምጽፈ፡፡ ውሸትና አስመሳይነት ይወገዱ! ሴራዊ አከሄድ ይወገድ!
 • ውሸትና አስመሳይነት ሴራዊ አካሄዶች እንደኖህ ዘመን ሰዎች ኢትዮጵያን እያጠፉ ናቸው፡፡
 • ከሰሞኑ አንድ ያገኘሁት መረጃ ላቅርብና ወደ ዋናው ጉዳይ፡፡ ይሄንንም በዋናው ጽሁፌ በዝርዝር ታገኙታላችሁ፡፡ እንደምሳሌ ነው፡፡ አብይን በችግኝ ተከላ መሳተፉን ከምደግፈው ነው፡፡ ሆኖም እውነቶች ደግሞ ይታወቁ፡፡ ኢትዮጵያ በ4 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ16.1 ቢሊየን ዛፍ ችግን ተክላለች (እንደ መንግስት ወሬ) ይሄ ማለት እያንዳንዱ ችግኝ በየ 2 ሜትሩ ቢተከል ወደ 6.44 ሚሊየን ሄክታር ነው፡፡ ኢትዮጵያ አጠቃላይ ስፋቷ 110.4 ሚሊየን ሄክታር ነው፡፡ በዚህ ስሌት ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 70 ዓመታት በታች ሙሉ በሙሉ በደን ትሸፈናለች፡፡ እውነታው ግን ኢትዮጵያ በደን መራቆት ምክነያት ሐይቆቿና ግድቦቿ በደለል እየተሞሉ ይሄው ዛሬ የምትጠቀምበትን ከሌሎች አገራት አንጻር ይሄ ግባ የማይባል የመብራት አቅርቦቷ በፈረቃ ሆኖ ሕዝብ እየተሰቃየ ነው፡፡ መንግስት ሳይዋሽ ቁርጠኛ ቢሆን ይሄን ችግር ለመፍታት ግን በእጃችነ ነው፡፡
 • በዚህ ጽሁፍ አብይና መሰሎቹን ወሳኝ ነጥቦችን እንስቼ እተቻለሁ፡፡ አትዋሹ፣ አታስመስሉ፣ ዘረኛ አትሁኑ አታሲሩ ግን ጽኑ ምክሬ ነው፡፡፡ እግዚአብሔር እውነቱን ስለሚያይ ማፈር አይቀሬ መሆኑን አስቡ፡፡

ብዙ ጊዜ ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡ የምናገረው ዝም ብሎ የአክቲቪስት ትርክትን አደለም፡፡ በተጨባጭ የማገኛቸውንና አናሊቲካል መረጃዎችን በመጠቀም ነው እንጂ፡፡ ሰሞኑን አንድ አንተ (አብይ) በውሸት እየተወነጀልን ነው አይነት ነገር ስትናገር ሰማሁ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተናገርካቸው ነገሮች በራሳቸው ግን አንተም ሆንክ ሌሎች የለውጥ አመራር ነን የምትሉ በተለይ ደግሞ የኦዲፒ አመራሮችን አስመልክቶ ከሕዝብ ዘንድ የሚቀርብባችሁ ትችት ውሸት እንዳልሆኑ በግልጽ ያሳያሉ፡፡ እንግዲህ ከራስህ ንግግር የሰማሁትና እኔን ያሳዘነኝን እንዲህ ልንገርህ፡፡ ብዙ ጊዜ በንግግር ትስታለህ፡፡ እንደ አር መሪ ሳይሆን በተደጋጋሚ የኦሮሞ ብሔረተኝነትክን በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ወንበር ተቀምጠህ ትናገራለህ ብቻም ሳይሆን እንደማስፈራሪያም ትጠቀምበታለህ፡፡ ለምሳሌ ወታደሮች ቤተመንግስት በገቡ ጊዜ ዙሪያህ ያለውን የአዲስ አበባ ሕዝብ ከሕዝብ ሳትቆጥር ከሱሉልታ መንግስታችን ተነካ ብሎ ሕዝብ እየጎረፈ ነበር አልክ፡፡ የማን መንግስት? የኢትዮጵያ ወይስ የኦሮሞ? ሱሉልታዎቹ ግን አልወጣቸውም፡፡ ከአንተ በላይ እነሱ ኢትዮጵያዊ ናቸውና፡፡ የዳጬ ዘር እንደሆነ አትዘንጋ፡፡ ሌላ ጊዜ ሰው እየሞተ፣ ባንክ እየተዘረፈ ነው ስርዓት ይከበር ተብለህ ስትጠየቅ እንዲሁ አሳዛኝ መልስ ሰጠህ፡፡ አምቦ ላይ ስኳር የጫነ መኪና አስቆምክ ብለን ሰውን በመሳሪያ አንገድልም አልክ፡፡ ለመሆኑ ስለአምቦ ስኳር የጫኑ መኪኖች በሕዝብ መቆም ሕገ-ወጥ ነው ያለ ማን ነው? አምቦን ለሕዝብ ገዳይ አረመኔዎችና የባንክ ዘራፊ ወንበዴዎች ከለላ ለመስጥ ስታነሳ አላማህ ምን ምን እንደሆነ ሰው አይታዘብም ብለህ ታስባለህ? አሁንም እደግመዋለሁ አምቦ በተጠየከው ነገር አይነካካውም፡፡

ሰሞኑን ደግሞ ሌላ ብዙ የታዘብኩትን ነገር ተናገርክ፡፡

በአዲስ አበባ መታወቂያ ተሰጠ የተባለው ውሸት ነው ስትል ፍርጥም ብለህ ተናገርክ፡፡ ውሸት ግን አደለም፡፡ እሺ ይሄ ውሸት ይሁን፡፡ በይፋ ሕዝብ ያያቸውና እያያቸው ያሉትን ነውሮች እንዴት ትከልላቸዋለህ? አዲስ አበባ ላይ ታከለ ኡማን ለምን ሾምክ? አሁንም ነገሮችን ወደ የማይሆን መስመር አትውሰድ፡፡ ታከለ ኦሮሞ በመሆኑ ማንም አይቃወምም፡፡ የአዲስ አበባ ተወላጅ መሆን አልመሆኑም አደለም፡፡ ግን የሄድክባቸው መስመሮች ምን ያህል ሕገ-ወጥ እንደሆኑ መጀመሪያ ለራሲህ ትቀበላለህ? ከዛም በኋላ አዲሱ አረጋ ታከለ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆነበትን ቁልፍ ሚስጢር ነገረን፡፡ ለመሆኑ አዲሱ የተናገረው ውሸት ነው ብለህ ልታስተባብል ትችላለህ? ወይስ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ነው እንጂ በኦሮምኛ አዲሱ እንደዛ አልተናረም ልትለን ይሆን፡፡ እንደወረደ ነው ኦሮምኛውን ሰምተንዋል፡፡ አሳፋሪ ነው፡፡ ከዛም በኋላ ወጥቶ ይቀርታ መጠየቅ ሲገባው ከራሱ አንደበት የተነገረውን እየሰማን መካዱን መርጧል፡፡ አምቦ ላይ አዲሱ የጸጋዬ ገብረአብ መጻፍ ሆን ተብሎ በጀት ተመድቦለት በአማራና ኦሮሞ መካከል የማይታረቅ ጸብ ለመፍጠር ብሎ የተናገረውን የተስፋዬ ገብረአብን ልብ ወለድ የአምልኮ መጻፋቸው ያደረጉ ኦሮሞዎችን ስላስቆጣ ደጋግሞ ይቀርታ ሲጠይቅ ነበር፡፡ የተናገረው ግን ውሸት አልነበረም፡፡ ግን ከኦሮሞ ተቃውሞ ገጠመኝ በሚል እንጂ፡፡ ስለታከለ በአዲስ አበባ ምን እንደሚሰራ የተናገረው ግን ከይቅርታም በላይ ነበር የሚጠይቀው ጉዳዩ፡፡

ለማን ብዙ ስናምነው ተመሳሳይ ነገር ተናግሮ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ አሁንም ግን የተናረውን ለማስተባበል ሞከረ እንጂ ይቀርታ አልጠየቀም፡፡ ለማ የተናገረው ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ለምን ለማ እንደዛ ተናገረ ሁኔታዎች አስገድደውት እንጂ እሱ እንደዛ አያስብም የሚል ነው ሕዝብ ጋር በአብዛኛው የነበረው፡፡ እኔን ጨምሮ፡፡ ነገሮችን እየቆየን ስናይ ግን በጣም ችግር አለ፡፡ ይሄው አንተው ሰሞኑን የተናገርከውም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው፡፡ ለየከተሞች ኮታ ተሰጥቶ በኦሮሚያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ከሱማሌ የተፈናቀሉን አስፍረናል አልከን፡፡ እንደእውነቱ የተፋናቀሉትን እንደዜጋ ከመርዳት አኳያ ማንም ችግር ሊኖርበት አይችልም፡፡ ችግሩ ግን ከእነዚህ ዜጎች ከመፈናቀረሉ ጀምሮ ከበስተጀርባ ሴራ እንዳለበት አመላካች መሆኑ እንጂ፡፡ እኔ ሲጀምር እነዚህ ዜጎች የተፈናቀሉት በአብዲ ኢሌ ተመካኘ እንጂ በዚህ ሴራ ኦነግና ኦዲፒ በጋራ የሰሩት ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡ በፊት ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ኦነግ እንዳለበት ይሰማኝ ነበር፡፡ አሁን አሁን ሳስተውል ግን ኦዲፒም አብሮ እንደነበር ነው የምታዘበው፡፡  ስለዚህ የለማ የዲሞግራፊ ቀመር ብዙ ርቀት ታስቦበት ነው ወደሚል ሁሉ ሊወስድ ይችላል፡፡ እሱም አይሁን፡፡ ሁለተኛ በኦሮሚያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ነው ያሰፈርነው ብለህ አዲስ አበባንም እንደ አንዱ ነግረህናል፡፡ በዚህ ጉዳይ አላስፈላጊ ዋጋ እያስከፈለህ ያለህበትን ተግባር እየሰራህ መሠለኝ፡፡ ሲጀምር አዲስ አበባ የኦሮሚያ ከተማ አደለም፡፡ አዲስ አበባ ራሱን ያቻለ አስተዳደር ያለው ከተማ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ጉዳይ ደግሞ መወሰን የሚችለው የኦሮሚያ መንግስት ሳይሆን የአዲስ አበባ መስተዳደር ነው፡፡ በጠ/ሚኒስቴር ቦታ ሆነህ ይሄን ማሰብ ሳትችል እንዴት ነው አገር መምራትን የምታስበው፡፡ ሌላው ለእነዚህ ዜጎች የቱም ለእነሱ የሚጠቅ ነበር ቢደረግ የሚከፋ የለም፡፡ ሆኖም ዜጎች ሁሉ እንደዜጋ ሊታዩ ይገባል፡፡ ለኦሮሞ ተፈናቃዮች አሁን የምትለውን ሁሉ ጥረት ተደረገ ለመሆኑ ለሌሎቹስ? በየክልሉ ያለውስ ተፈናቃይ፡፡ ለአብዛኛው ሕዝብ መፈናቀል ደግሞ ምክነያቱ የኦሮሞ የዘረኛና ጥላቻ ፖለቲካ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የጌዲዮን እኮ ውሸት ነው ልትሉን ነው የሞከራችሁት፡፡ ይሄም ነውር ነው፡፡ ከዛም በኋላ በከተማ አስፍራቸውሁም አላረፋችሁም፡፡ ከተማው ያንተ ነው መጤውን አስወጥተሕ የመኖር መብት አለህ የሚል ቅስቀሳ ሳይቀር ስታካሂዱ ነበር፡፡ ውሸት አደለም፡፡ በአደማ ለነበረ ግጭት ምክነያቱ እንዲህ ያለ ሴራ ነበር፡፡ በእርግጥም በአዲስ አበባም እንዲሁ በሌሎች ላይ አደገር እንዲፈጥሩ እነዚሁኑ ተፈናቃዮች ተጠቅማችኋል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ከሱማሌ የተፈናቀሉትን በከተማ እያሰፈርክ በከተማ ቤት ሰርተው የኖሩትን አፈናቅላችኋል፡፡ እንግዲህ ልብ በል በአገሪቱ በአብዛኛው በኦሮሞ ምክነያት ብዙ ሕዝቦች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ቤት ሰርተው የሚኖሩትን ደግሞ የኦሮሞ መንግስት በመሆናችሁ (ይሄ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር ሆንህ እንኳን አንተው ያልከው የክልሉም ሕገ መንግስት ላይ በግልጽ ያስቀመጣችሁት ነው) ሌላውን ቤት አፍርሳችኋል፡፡ እንግዲህ እነዚህን በተግባር የሚታዩ እውነቶች ውሸት ናቸው ልትል ትችላለህ?

በዚህ ብቻ አላበቃችሁም አሁንም ከኋላ በፖሊስ ጭምር አጅባችሁ በአዲስ አበባ የኮንደሚኒየም እጣ የደረሳቸውን ቤታቸውን እንዳይወስዱ ያደረጋችሁበትን ሂደት አስተውል፡፡ ይሄን ሕገ-ወጥ ብለህ ለመናገር እንኳን አልፈቀድክም፡፡ ግን እንዲህ ያለው መረን የለሽ ቡድን አዲስ አበባን እወራለሁ እያለ በሚደነፋበት ወቅት ሁኔታውን የሚከላከልላቸው የመንግስት መዋቅር ሳይቀር በዚሁ ቡድን እንደተወረረ የተረዱት አዲስ አበቤዎች በእነእስክንድር በኩል ተደራጅተው ራሳቸውን መከላከል ግድ ሆነባቸው፡፡ ይሄን ግን ሕገ-ወጥ ለማለት ጊዜ አለወሰደብህም ብቻም ሳይሆን በመግደል አላንም እያልክ ስትሰብክ የነበረው ሰውዬ ጦርነት አወጅህ፡፡ ትንሽ እንኳን ሊያሳፍርህ አልወደድክም፡፡ በየትኛውም አለም ግን እንደ እነ እስክንድር ያለው አደረጃጀት ሕገ-ወጥ አደለም! ይሄን በድጋሜ በሰሞኑ ነግግር ደግመህ ሕገ-ወጥ ስትል ሰምቼሀለሁ፡፡ በአደማ መሰልክው እንጂ፡፡ ሲጀምር የመንግስትን መዋቅር በኦሮሞነት ስለወረራችሁት ሌሎች በሚታዩ አደገኛ ድርጊቶች አደለም በሰላማዊ መልኩ ተደራጅተው መብታቸውን ለማስጠበቅ መንቀሳቀስ ቀርቶ በጦር መሣሪያ ቢፋለሟችሁ ከነበረው አካሄዳችሁ አንጻር በሕግ ቢሆን ቀድሞ ወንጀለኛ የሆነው የመንግስት መዋቅሩን የያዘው ቡድን ነው፡፡ ለማንኛውም እነ እስክንድር የሄዱበትን አካሄድ ሕገ-ወጥ ነው ማለትህ ምን ያህል ከዲሞክራሲ እንደራቅህና ይልቁንም የኦሮሞ ዘረኝነትክን በድጋሜ ለሕዝብ ይፋ እያደረክ እንጂ በማንም አእምሮ በሰላማዊ መልክ ተደራጅቶም ይሁን ሳይደራጅ እንኳንስ ያን ሁሉ አደጋ የመጣበት ሕዝብ ቀርቶ ምልክት ከአየ ራሱን መከላከሉ ዲሞክራሳዊ መብት ብቻም ሳይሆን ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ይሄ ለአንዳችሁም አልተዋጠላችሁም፡፡ ሌሎች አናፋሽ የፖለቲካ ቡድኖችን ጨምሮ፡፡ በሕዝቡ ተጋርጦ የነበረውን በይፋ ይታይ የነበረውን ግን ማንም አላወገዘም፡፡ ስለ እነ እስክንድር ዲሞክራሳዊ አካሄድ ግን እስኪ ትንሽ ዲሞክራሲን የሞከሩ አገራትን እውነት እዩ፡፡ እድሜ ልክ የኖራችሁበት አስተሳሰብ ነው ለእናንተ ዲሞክራሲ የሚለካው፡፡ በሕግ-እጣ ወጥቶላቸው ቤታቸውን እንዳይረከቡ ያደረጉትን ግን ሕገ-ወጥ ማለት ቀርቶ ጭራሽ እነሱን በመደገፍ መግለጫ አወጣችሁ፡፡

እንግዲህ አብይ ሆይ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪ መሆን ለቻለ ሕወቱን ሳይቀር እንደሚሰጥ በተግባር አይተህዋል፡፡ ግን የሚታመን መሪ አለማግኘቱ ያሳዝናል፡፡ የተሰጣችሁ እድል ታላቅ ነበር፡፡ አበላሻችሁት ብቻም ሳይሆን እስከወዲያኛው እንዳትታመኑ ማረጋገጫ ሰጣችሁት፡፡ የኖራችሁበት የውሸትና አስመሳይነት ባሕሪ አውሮአችኋል፡፡ አዝናለሁ በብዙ ቦታ ለማስመሰል ሞክራችኋል፡፡ እውነት ግን ቢኖራችሁ ከአገኛችሁት ድጋፍ እንጻር ያሰባችሁትን ሁሉ በሰራችሁ፡፡ ሸፍጡንም ጨምሮ፡፡ ግን አንድም በጎ እንዳታደርጎ እግዚአብሔር ማንነታችሁን ስላስተዋለ በቶሎ ስገግብግብ አድርጎ አጋለጣችሁ፡፡ አሁንም እላለሁ፡፡ አገር መሪ ለመሆን በመጀመሪያ ራስህን ከገባህበት የአስተሳሰብ ችግር ነጻ አውጣ፡፡ በኦሮሞነት የሄዳችሁበት አካሄድ ገና ብዙ ዋጋ ያስከፍላችኋል፡፡ ሕዝብ ያመናችሁን ያህል በድርጊታችሁ እጅግ እንዳዘነ እውነቱን እነግርሀለሁ፡፡ አዳማ የኦሮሞ ነው በሚል አስተሳሰብ የት እንደምትደርሱ ግልጽ ነው፡፡ የማንንም ተራ አስተሳሰብ የመንግስታችሁ እቅድ አድርጋችሁ አመት ሳይሆን የሆነውን ሁሉ አስተውሉት፡፡ ቤተመንግስት አድሳለሁ ትላለህ ለመሆኑ እነዛ ቤተመንግሰቱን የሰሩት ሕዝብ እንዴት እንደመሩ የሆነ ቦታ ላይ ተጸፎ አላገኘህም? የኢትዮጵያ መሪዎች ምትሀት ነበሩ? የተበታተንን አገር አንድ እንዴት አደገረጉት? ዓላማና ግብ የሚባል ቁርጥ መዳረሻ ነበራቸው፡፡ ይሄውም አገርና ሕዝብ የሚሉት፡፡

ሌላው አብይ ሆይ አሁንም መዋቅሮችን ከኦሮሞነት እንድታጠራቸው እመክርሀለሁ፡፡ ለራስህ ነው፡፡ ይሄ ማለት ከኦሮሞ የተወለደ ማለት አደለም፡፡ በኦሮሞነት ያስያስካቸውን መዋቅር እንጂ፡፡ በተለይ የገቢዎች ሚኒስቴርና ንግድ ባንክ ጉዳይ ገርሞኛል፡፡ ሌላውም ጋር እንደዛው ነው፡፡ እውነት እንጂ ማስመሰል ቆይቶ ያዋርዳል፡፡ አመት በአልሆነ ጊዜ የሆነውን ታያለህ፡፡

ሌላው አገራዊ ፕሮጄክቶችን ትተህ አዲስ አበባና ቤተመንግስት ላይ ትልቅ ትኩረት እንዲኖር ያደረክበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው፡፡ አዲስ አበባ አሁንም ሌላ ችግር እየተሰማ ነው፡፡ ዜጎችን በልማት ስም ማፈናቀል፡፡ አንድ ነገር መንግስት ዜጎችን የሚኖሩበትን ቦታ ለልማት ከፈለገ በመጀመሪያ በዛ ቦታ ለሚኖሩ ዜጎች በቂ መጠለያ ማዘጋጀትና ከበቂ ትራንስፖርትና የመሳሰሉ ተዛማች አገልግሎት ጋር ማስፈር ግዴታው ነው፡፡ እንደግዲህ በለመዳችሁት አካሄድ ዜጎች በማን አለብኝነት እያፈናቀሉ ሜዳ ላይ እየጣሉ ልማት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሳይገባችሁ ይሄው አሁንም መሪ ነን ትላላችሁ፡፡ እንግዲህ መንግስት ዜጎችን በቂ መጠለያ ማዘጋጅት ከአልቻለ ከቦታቸው የማፈናቀል መብት ሊኖረው አይችልም፡፡ የትኛውም ልማት ቅድሚያ ለዜጎች ደህንነት ሊያስብ ይገባል፡፡ ይሄ እንኳን ተደርጎ ዜጎች አንነሳም የማለት መብት አላቸው፡፡ በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው እስካልተገደዱ ድረስ፡፡ ምን አልባትም ተጨማሪ ካሳ ያስፈልጋቸዋልና፡፡ የመኖሪያ ቤትና አገልግሎት ግን ከእነዚህ ሁሉ በፊት የሚቀርብ ነው፡፡ መንግስት ማለት ከገባህ እንዲህ ነው፡፡

ሌላው አንዳንድ ሕዝብን ለማነሳሳት በሚል የምታደርጋቸውን ተሳትፎ እደግፈዋለሁ፡፡ ለምሳሌ ቆሻሻ ማጽዳት፣ ችግኝ መትከል፣ ሌላም፡፡ ሆኖም ግን ለማስመሰል አይሁን፡፡ መጀመሪያ ከውሸት የፀዳ በእርግጥም ቁጭትና እልህ ያለበት ምሳሌነት ይሁን፡፡ ይሄን ግን በብዙ ነገር የታደላችሁ አልመሰለኝም፡፡ ሚኒሊክ ሕዝባቸው ረሀብ ባጠቃባቸው ወቅትና ከብቶች በበሽታ አልቅ በነበረበት ወቅት በሬ ለማረስ ስለጠፋ ዶማ ይዘው ቅድሚያ እንደወጡ ተጽፏል፡፡ ሚኒሊክ በብዙ ነገር ለሕዝብ ምሳሌ ነበሩ፡፡ ቴክኖሎቺዎችን ወደ አገር ለማስገባት ሁሉንም ራሳቸው ሞክረው ነው፡፡ መኪናውን፣ ሳይክሉን፣ ሆቴሉን ሌላውንም፡፡ እንግዲህ የሚሊክ ለማስመሰል ሳይሆን አላማን ከግብ ለማድረስና ለሕዝብ ምሳሌ ለመሆን ነው፡፡ የኦሮሞ ዘረኝነትና ጥላቻ የለከፋቸው የሚኒሊክ ሥም ሲነሳ እንደሚያሳብዳቸው አውቃለሁ፡፡ እውነቱን ዋጥ ማረግ ግድ ይላል፡፡ ሚኒሊክ የኢትዮጵያ ታላቅ መሪ ናቸው!! መሪ እንዲህ ነው፡፡ ለፎቶና ለወሬ አደለም፡፡  ሰሞኑን ችግኝ በመትከል ተሳትፎ እያደረክ መሆኑን አሁንም አደግፋለሁ፡፡ የችግኝ ጉዳይ ግን በየዓመቱ ብዙ ቢሊየን ይተከላል፡፡ በአገራችን ግን በመረት መጋቆት ምክነያት ይሄው ግድቦቻችን ደለል እየሞላ መብራት እንኳን ጠፍቷል፡፡ ብዙ ውሐማ ቦታዎች በደለል እየተሞሉ ነው፡፡ የአለማያ ሐይቅ ምሳሌ ነው፡፡ አሁን አቢያታ፣ ጣናም፣ ዝዋይ አደጋ ላይ ናቸው፡፡ አዋሳ ሐይቅም እንዲሁ፡፡ ይሄን ለማስቀረት አንድ ሐሰብ አዘጋጅቼ ነበር፡፡ ዛሬ አንተ የአዲስ አበባ ወንዞችን ማጽዳት ብለህ ከምትናገርለት ፕሮጄክት ጋር አስቤው የነበረው፡፡ የአዲስ አበባውን ወንዞችን ማጽዳትና ማስዋብ ሐሳብ እኔ ከ7ዓመት በፊት ለአዲስ አበባ መስተዳደር አቅርቤ እንደነበር ከዚህ በፊት ገልጫለሁ፡፡ ሒደቱ ግን አሁን አንተ በያዝከው አይነት እንዲሆን አልለኩም ነበር፡፡ አሁንም ልክ አደለም፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ወንዞችንና ውሃማ አካሎችን ለመታደግ ሀሳብ ነበረኝ፡፡ ሒደቱም መንግስት ሙሉ በሙሉ በባለሙያዎች በተዋቀሩ ልዩ ድርጅቶች እንጂ በመንግስት በቀጥታ እንዲሰራ አደለም፡፡ መንግስት ፖሊሲ ያወጣል፣ ፕሮጄክት ካለው ገንዘብ ይመድባል ሆኖም በቀጥታ በልማት መሳተፍ የለበትም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡ ይሄን ሐሳብ በይፋ እንዳቀርብ እድል ባገኝ ያሰብኩትን ግዙፍ ፕሮጄክት ለማሳወቅ፣ መነሻ ሐሳቡን ሰነድም ለማቅረብ ፍቃደኛ ነኝ፡፡ እንደነዚህ ያሉ ፕሮጄክቶችን ለማከናውን ከመንግስት ውጭ ከየት ገንዘብ ሊገኝ እንደሚችል ሁሉ ጭምር፡፡

ስለችግኞች ተከላ ግን አንድ ወዳጃችን ያቀረበውን መረጃ እንሆነ

ሐምሌ 6:2010 (ኢዜአ)፡  4.3 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታስቦ እስካሁን በሁሉም ክልሎች 3.3 ቢሊዮን ችግኝ ለተከላ ዝግጁ ሁኗል።

ሰኔ 23፣ 2009 (ዋልታ)፡ በያዝነው ክረምት 3.5 ቢሊዮን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

ሰኔ 4:ቀን 2008 አም (ኢዜአ)፡ በአገሪቱ በክረምት ወራት 4 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚተከል ተገለጸ፡፡

ሰኔ 20፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.)፡ የአካባቢና የደን ሚኒስቴር በዘንድሮው የክረምት ወቅት 5. 3 ቢሊዮን ችግኞችን ለተከላ አዘጋጀ፡፡

ከላይ በተጠቀሱ 4 ዓመታት ብቻ የመጀመሪያውን 4.3 የታሰበውን ትተን ለተከላ ተዘጋጀ የተባለውን 3.3 በመውሰድ በድምሩ በአራት ዓመቱ 16.1ቢሊየን ችግኝ እንደተተከለ ይታሰባል፡፡ እንደው እያንዳንዱ ችግኝ 2 ሜትር በ2ሜትር ተተከለ ብንል 6,440,000 (ስድስ ሚሊየን አራት መቶ አርባ ሺ) ሄክታር መሬት ተሸፍኗል፡፡ ኢትዮጵያ አጠቃላይ ስፋቷ 110.4 ሚሊየን ሄክታር ይገመታል፡፡ በዚህ ስሌት በአራቱ አመት የአገሪቱን 6 በመቶ የሚያህለውን ቦታ በደን መሸፈን ተችሏል፡፡ በሚቀጥሉት 70 ዓመታት ጊዜ ውስጥ አገሪቱን ሙሉ በሙሉ በደን ትሸፈናለች በዚህ ቀመር፡፡ እንግዲህ ተመልከቱ ማንን እየዋሸን እንደሆነ፡፡ ድሮ እኔ በዜና በመንግስት የሚነገር ነገር እውነት ይመስለኝ ነበር፡፡ ልጅ ሆኜ መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ግን መንግስት ከማመን አንደ የሰፈር ሰው መጠየቅ ይሻላል፡፡ ቢያንስ የሚያውቃትን በተሻለ ጥራት ይነግርሀል፡፡ ይሄ እልቆ መቋረጫ ያጣው ውሸትና አስመሳይነት አገርርን እያጠፋ ነው፡፡ እንግዲህ ወንዞችም፣ ሐይቆችም በደለል እየተሞሉ ሰው በመብራት እጦት እየማቀቀ እያየን እንኳን መዋሸትን አላቋረጥንም፡፡ ምን ሁሉም ቦታ እንጂ በአጠቃላይ እንደኖህ ዘመን ሰዎች አስመሳይነታችንና ውሸት ሌሎችም ነውሮቻችን እስከሚያሰጥሙን ላይገባን ምለናል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ መንግስት ነን የሚሉት እንዲህ ነው እንግዲህ የሚቀልዱብን፡፡ ከላይ ለቀረበው ሪፖርት አብይን ተጠያቂ እያደረኩ አደለም፡፡ በዚህ ከእሱ ይልቅ በሙያው ላይ ያሉት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ማስተዋል ጠፍቷል፡፡

 

ለአንዳንድ ሰዎች አስተያየት ልስጥ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን የአዲስ ስታንዳርዷ አስካለ ለማን እንዴት ዲሞግራፊ እቀይራለሁ ብሎ አወራ ብለው ያወሩበታል በሚል አምርራ ስትናገር ሰምቼ ገርሞኛል፡፡ አስካለ ሆይ ለማ ራሱ የተናገረው እውነት እንጂ ሰዎች ያስወሩበት አደለም፡፡ ለዛ ራሱም ማብራሪያ ሊሰጥ ሞክሯል፡፡ ሰዎች የተናገረውን እንደወረደ አቀረቡት፡፡ ለምን አቀረቡት ካላልሽ በቀር፡፡ ይሄ ደግሞ ለምንም አላማ ይሆን ከእሱ እስከወጣ ድረስ መብታቸው ነው፡፡ አስካለን ተንተርሼ ለሁሉም እላለሁ እውነት ላይ ቁሙ፡፡ በደጋፊነትና በተቃዋሚነት አደለም፡፡ እውነትን በመጋፈጥ እንጂ፡፡ ለአገርና ሕዝብ ስንል የምንሸሽጋቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለእንትና ደጋፍ ብለን ግን ሊሆን አይችልም፡፡ አብይንና አሁን ለውጥ ላይ ነኝ የሚለውን ቡደን እኔን ጭምሮ ብዙዎች ደጋፊ ነበርን፡፡ የምርም ኢትዮጵያዊ የሆኑ ይህን አድርገዋል፡፡ በዛው ልክ ግን ሲካዱ መምረራቸውን አስተውሉ፤፡ እውነት የሚነግረን ጋዜጠኛና ገለልተኛ የሆነ ሚዲያ አናይም፡፡ ባለስልጣኖችን ስትጠይቁ እኔ ከላይ እንዳነሳኋቸው ያሉትን ነጥቦች ግልጽ መጠየቅ የሚችል ቢኖር እነሱንም ከጥፋት ባዳነ ነበር፡፡

ለብዙ ጊዜ እኔ በምጽፋቸው ላይ አስተያየት የምትሰጥ አባ ጫላ የምትባል ሰው፡፡ ዛሬ ልመልስልህ የምፈልገው አላስፈላጊ የሆነ መረጃ ለሕዝብ የሰጠህ መስሎኝ ነው፡፡ ብዙዎች ስለ ጀርመን የሚያስቡት የተሳሳተ ነው፡፡ እኔ ጀርመንን አውቀዋለሁ፡፡ ጀርመኖችም በብዙዎች እንደሚታሰቡት ዘረኞች ሳይሆን ክብር የሚወዱና በጣም ስርዓትን የሚጠብቁ ሕዝቦች ናቸው፡፡ በጀርመን የናዚ አፍቃሪያን እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ የጀርመን ሰሪዎች ናዚዎች አደሉም፡፡ ናዚ አመሳስል ካልከኝ ናዚ ማለት የኢትዮጵያውን ኦነግ አስተሳሰብ ይዞ የተነሳ ነው፡፡ ኦነግ በትክክለም ናዚን ይመስለዋል፡፡ በጣም ዘረኛና የጥላቻ ፖለቲካ ማራመድ ብቻም ሳይሆን የሚጠላውን ዘር ለማጥፋት በተግባር ሞክሯል፡፡ አለመሳካቱ አደለም የሚታየው፡፡ በተረፈ ግን ጀርመን የተመሰረተችው በኦቶ ቢስማርክ እንጂ በሒትለር አደለም፡፡ ሒትለር ጀርመኖች በተሳሳተ አስተሳሰብ በመበከሉ ብዙ ችግር ደርሶባቸዋል፡፡ ዛሬ ኦነግ ኦሮሞን እንዳደረገው ማለት ነው፡፡ ቢስማርክ ጀርመንን አንድ ሲያደርግ እጅግ በከፍተኛ ጦርነት ነበር፡፡ ዛሬ ቢስማርክ የሚታወቀው በጀርመን አባትነት ነው፡፡ በጀርመን ታሪክም ቢስማርክ በክብር ላቅ ያለ ነው፡፡ ሌላው ጀርመኖር በእርግጥም እስከዛሬም በታሪክ ሰሪዎቻቸውና በነገስታቶቻቸው ይመካሉ፡፡ ከአንዳንደ ጀርመኖች ሥም በፊት ቮን (በእነሱ ፎን -von) የሚል ቅጽል ዛሬም ድረስ ይታያል፡፡ እነዚህ ማለት የጀርመን የነገስታት ዘሮች ናቸው፡፡ ሕዝቡም ያከብራቸዋል፡፡ በኒዘርላንድ ተመሳሳይ ስም አለ ቫን ለምሳለ ቫን ኒስትሮይ (ኳስ ተጫዋቹ)፡፡ በአጠቃላይ ጀርመንን ጨምሮ አውሮፓውያን ለነገስታት ቤተሰብ ትልቅ ክብር አላቸው፡፡ ምክነያታቸው ደግሞ የአገራችን ባለውለታዎች ናቸው በሚል ጭምር ነው፡፡ እስከዛሬም እንደ አገር ምልክት አድርገው በንግስና ያቆዩ አገሮች ብዙ ናቸው፡፡ ሥርዓትን በማስተማርና ሕዝቡ ለእነዙ ሥርዓት በመገዛቱ ምክነያት አገሮቹ ሊያድጉ እንደቻሉ ይረዳሉ፡፡ መንግስት በሕዝብ ላይ ችግር ሲፈጥርም ይገስጻሉ፡፡ የነገስታቶቹ ሚና ሕዝቡን የእኔ ብለው ስለሚያሰቡ በሕዝብ በደል ሲደርስ ይገስጻሉ፡፡ ይሄ ማለት በሆነው ባልሆነው እየተነሱ አደለም፡፡ስለ ጀርመኖች ግን እኔ ምስክር ነኝ፡፡ ቢሆንልኝስ ኢትዮጵያውያንን እንደጀርመኖች ቢሆን እመኛለሁ፡፡ ዘረኞች አደሉም፡፡ ልክስክስ አደሉም፡፡ ይሄ አውነት በጃፓኖችም የምናየው ነው፡፡ ክብራቸውን ይወዳሉ!  ማጭበርበር ምናምን አይመቻቸውም! ይሄው ነው ጀርመን ማለት፡፡ ይልቁንም ናዚዎቹ የጀርመንን ክብር የሚያቆሽሹ ናቸው፡፡  አባ ጫላ ከኦሮሞነት ወጣ ብትል ታየዋለህ፡፡ ለእኔ ደግሞ የጸጋዬ አራርሳን አባባል ጠቅሰህልኛል፡፡ ጥሩ አደለም፡፡ ብዙ አልልህም እንድትታረም ብዬ ነው፡፡ እንደ ግለሰብነትህ፡፡ ቢያንስ ግን የራሰህ አስተሳሰብ ይኑርህ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ከአንድ ሰው በውስጥ መስመር ሄኖክ የሺጥላ እንዳለው የሚል መልዕክት ደርሶኝ ነበር፡፡ እንግዲህ የምቅሷቸው ግለሰቦች በራሱ ለመጠቀስ ቀርቶ ለአመክንዮዋዊ ሁኔታ ለማስረዳት አስቸጋሪ የሆኑና በራሳቸው ጊዜ የጠፉ መሆኑ ሳያንስ የእነሱ አስተሳሰብ ተገዥ በማድረግ ብዙውን እንዳጠፉ እናያለን፡፡ የምጽፈው ለመታወቅ አደለም፡፡ ለአባ ጫላ ይሄ የመጀመሪያዬም የመጨረሻዬም አስተያየት ነው፡፡ ራስህን ከሌሎች አስተሳሰብ ነጻ አድርግ፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

3 COMMENTS

 1. Comment:
  There is a debt-for-nature swaps concept : financial transactions in which a portion of a developing nation ‘s foreign debt is forgiven in exchange for local investments in environmental conservation measures.
  May be that is the real reason behind the tree planting!

  Another concept is about the sugar corporations being sold; debt-for-equity swaps which I am going to explain next time!

 2. @አባ ጫላ
  “ተማርን ያሉ ለራሳቸው የኢኮኖሚ ብልጵግና እንጅ ደሀው 80ፐርሰንት የሚሆነው አርሶ አደር ትላንትም በበሬ ጫንቃ በደሳሳ ጎጆ በባዶ እግሩና በጠፍር አልጋ …” እያልክ የምታላዝንለት ህዝብ ከዚህ የመከራ ኑሮ እንዳይላቀቅ ያደረገው የድሮ ስርዐታችሁ መሆኑን በመደበቅ እና ይህንን የባርነት ዘመን ታግለው የጣሉትንና ተመልሶ እንዳያንሰራራ የሚታገሉትን ለችግሩ እነርሱን ብቻ ተጠያቂ ለማድረግ ዐይንህን በጨው አጥበህ ላሞኛችሁ ትለናለህ! “ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ ” እያልክ ሌላውን ለማጥላላት ስትጥር እናንተው የድሮ ስርዐት ናፋቂዎች፣ ለህዝቡ ሳይሆን የጥቂት ሆዳሞችን የበላይነት ለመመለስ እንደምትኳትኑ፣ ከስራችሁ እና ከሚትለፍፉት ሁሉ ግልጽ መሆኑ ለናንተ ብቻ አይታያችሁም! ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ሃገር መሆኑዋን ለአፍ እንኳ ሳትቀበሉ፣ የሃገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፋንታ የእነዚህ ማህበረሰቦች የጋራ ስምምነት ብቻ መሆኑን ክዳችሁ የሻገተውን “የአንድ ቋንቋ አንድ ባህል አንድ ህዝብ” ቀረርቶ ታሰሙናላችሁ! Camouflaging Amhara nationalism as unity, “Ethiopian” nationalim or “የዜግነት ፖሊቲካ”, bla bla is over, outdated and discarded! No alternative other than “Ethnic” federalism or disintegration! You have the choice!

 3. @ሰርፀ ደስታ;
  Every body knows that you are a disgruntled demagogue, and an avowed anti-Oromo. You express your virulent Oromo-phobia, though veiled as a campaign against its vanguard organisation – the OLF. Demagogues scribble and shout just for attention, so do not deserve a response. Just one point though:

  አዎ፣ የዛሬዋ ጀርመን የተመሰረተችው/አንድ የተደረግችው በኦቶ ቢስማርክ ነው። ጀርመኖች አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ግን የተበታተኑና በጥቃቅን ነገስታት የሚተዳደሩ ነበሩ። አንድ ሃገር ቢመሰርቱም ዛሬም በእዉነተኛ ፈደራሊዝም ነው የሚተዳደሩት። አንተ በተዘዋዋሪ ለማለት የፈግከው ሚኒሊክን የኢትዮጵያ ቢስማርክ ለማድረግ ነው! Weit gefehlt! sagen die Deutschen፣ ፍጹም ከእዉነት የራቀ መሆኑን ለማስረገጥ። ሚኒሊክ ቢመሳሰል ከሂትለር ጋር እንጂ ከቢስማርክ ጋር አይደለም! ሂትለር፣ የጀርመን/አሪያን ዘር ከሰው ዘር ሁሉ የላቀ/የበላይ ስለሆነ ሌሎች ኋላ ቀር ዝሪያዎች ጠፍተው መሬትን ለአሪያኖች ማስፋት አለብን ብሎ እንደተነሳው ሁሉ፣ በሚኒሊክ የተመራው የአምሃራ ኤሊትም በነጮቹ እገዛ ሃበሻ ያልሆኑ/ የሃበሻ ግዛት ውጪ የነበሩትን የጎረቤት ህዝቦችን በመዉረር ቅኝ አድርጎ፣ ከመጨፍጨፍ እና በባርነት ከመሸጥ የተረፉትን በአማሮች ኋላ ቀርና አረመኔአዊ አገዛዝ ስር ከባርነት በከፋ ሁኔታ እንዲማቅቁ ያደረገ ስርዐት ገንብቶአል። ልክ እንደአሪያኖች አማራ፣ የአማራ ቋንቋ፣ ሃይማኖትና ባህል ከሁሉ የላቁ እንደሆኑና የሌሎች በቅኝ የተያዙ ህዝቦች ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ እና ሃይማኖት እንዲጠፉ ፖሊሲ ተቀርጾ ሲሰራበት ነበር። ይህ የጭቆናና የባርነት ቀንበር እስከአጼ ሃይለ ስላሴ ዘዉዳዊ አገዛዝ መጨረሻ ድረስ የቀጠለ መሆኑን ያን ዘመን በአካል ያየን ስላለን፣ ሃቁን ለማድበስበስ መሞከር እንደመሳደብ ይቆጠራልና አትሞክር! አንተ የሚታጥላላቸው እንደ OLF, ONLF, SLF, EPLF, TPLF የመሳሰሉት የህዝቦች ነጻ አዉጪ ድርጅቶች የፈለቁት የመደራጀት ዲሞክራሲ ስለተስፋፋ አልነበረም። ህዝባቸውን ከፍጹማዊ ባርነትና ብሎም እንደህዝብ ከመጥፋት ለማዳን፣ ሺህ ሰማዕታትን ገብረው በከፊልም ቢሆን የዛሬውን የነጻነት ጭላንጭል አስገኝተዋል፣ ኤርትራም ነጻ ወጥታለች። ከኢትዮጵያ ኋላ የተመሰረቱ ሃገሮች እንኳ ሳይቀሩ አልፈዋት ሄደው፣ እሷ ብቻ ሁሌም በዕድገት ወደኋላ የዞረችው የዚህ የሃበሻ (አምሃራ/ትግሪኝ) የዘረኝነት ፖሊሲ ዉጤት መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ፣ ዛሬም በአስተሳሰብ ከመካከለኛው ክፍለ ዘመን ፈቀቅ ያላላችሁ የአማራ ኤሊቶች ሃገሪቷን ከጨለማ ለማዉጣት የሚታገሉት ላይ ያላሰለሰ የሚዲያ እና የነፍጥ ዘመቻ በመክፈት ወደ ሚኒልክ ዘመን ልትመልሱን ትጥራላችሁ! Fascism? no way!

  በሌሎች ሃገሮች ማን በምን አይዲኦሎጂ ሃገሩን ወደላቀ ደረጃ አሸጋገራት የሚለዉን ያነበነቡ ምሁራን ብዙ ናቸው። ችግሩ፣ እነዚህ ምሁራን ግን ባብዛኛው ስለሃገሪቱ ህዝቦች ባህላዊ አስተዳደር፣ ምጣኔ ሃብት እና ስነ ልቦና የሚያዉቁት ስለሌለ የሌሎች ሃገሮችን ተሞክሮ ከሃገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድና በማዳበር ዘመናዊ ሃገር መገንባት አልቻሉም፣ አይችሉም። ከፈረንጆች የቀዱት ሶሺያሊዝም፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ኒኦ ሊበራልዝም ወዘተ አልሰራ ሲሉ፣ የተጨቆኑ ህዝቦችን የነጻነት ትግልን፣ አሊያም አረቦችን፣ ኢምፐሪያሊዝምን ወዘተ በመርገም ጊዜ ያሳልፋሉ። ሌላው እነ ሰርጸ አይነቶቹ የሃበሻ ኤሊቶች የሚሟገቱት፣ በዬት ስልጣን እጃችን እናስገባለን እንጂ ህዝቡን የስልጣን ባለቤት ማድረግ (empowerment of the people) አይደለም ጭንቀታቸው። ያ ህልማቸውም ዉስጥ የለም፣ ቢኖርም ህልማቸውን የሚጻረር ስለሆነ ይዋጉታል! እንደ ኦነግ ያሉ፣ ህዝባቸውን የሃገሩ ባለቤት ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን የመጨረሻ ጠላታቸው ያደረጉበት ምክንያትም ይሄው ብቻ ነው!

  በመጨረሻም፣ የህዝቡን ኑሮ ከገጠር እስከከተማ ስለማዉቀው ችግሩን ለመረዳት “ከኦሮሞነት ወጣ” ማለት አስፈላጊዬ አይደለም። ከራሱ ማንነት ወጥቶ ሰው ሆኖ የቆመ የለምና! ያንተም ደማጎጊ የበዛው ከአማራነት ስለወጣህ ሳይሆን በጭፍን አማራነት ሌሎችን በጥላቻ እያየህ ስለሆነ ነው! እኔ የኦሮሞ ህዝብ መብት ይከበር እያልኩ ነው እንጂ የአማራ ወይም የሌሎች መብት ይገፈፍ አላልኩም። አንተ ግን የአማራ ኤሊቶችን ቅንጦት? (previlege) ለማስጠበቅ ኦሮሞ መሰረታዊ መብቱ ለምን ተከበረ ነው የምትለው! ልዩነቱ ሊገባህ አይችልም፣ ቅንጦት የለመደ፣ ያ ሲቀርበት እንደተጨቆነ ስለሚቆጥር!
  ደህና ሰንብት!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.