የምንስማማው አሕዱን ፈትታችሁ ጃዋርን ስታስሩ ነው!  (መስከረም አበራ)

የአሃዱ ሬዴዬ ጋዜጠኛን እና ባልንጀራውን ያሰረው የወቅቱ ግልገል ዘረኛ አምባገነን መንግስት ስላደረገው ብልሹ ስራ ልፅፍ ያሰብኩትን ስዩሜ እንዲህ አሳምሮ ስላስቀመጠው ብዕሬን ወደ ሰገባው መልሻለሁ። ብፅፍም ከዚህ በላይ ልል አልችልም! አንብቡት

የምንስማማው #አሕዱን ፈትታችሁ #ጃዋርን ስታስሩ ነው!

አንድ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣን ጋዜጠኛ ሊያስር የሚችለው መቼ ነው? ጋዜጠኛው በክልሉ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀስ ከተገኘ ሊታሰር ይችላል፡፡ ነገር ግን ባለፈው አንድ አመት ኦሮሚያ ውስጥ ወጣቶች ዱላና ገጀራ ይዘው እንዲወጡ በመቀስቀስ ረገድ ሁሉም ጋዜጠኞች አንድ ላይ ቢደመሩ #ጃዋርን አይስተካከሉም፡፡ እንደ #አለሙ_ስሜ ባሉ የክልሉ ባለስልጣናት ላይ የሃይል እርምጃ እንዲወሰድ በመቀስቀስ የሞት ፍርድ ሲፈርድ የነበረው #አያቶላህ_ጃዋር ነው፡፡ የኦዴፓ ሆነ የክልሉ መስተዳደር ሃላፊዎች ያሳለፏቸውን ውሳኔዎች በመፃረር ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ በመቀስቀስ ከሆነ እንደ ጃዋርና OMN የተሳካለት የለም፡፡ በህዝቦች መካከል ቂምና መቃቃርን በመስበክ ረገድ ከደቡብ ሲዳማ እስከ ሰሜን ጎንደር የአመቱ ተሸላሚ ሚዲያ የጃዋር OMN ነው!!! በፈለገው ሰዓትና ቦታ የሚያቀረሸው ጃዋር ነው!!! የአሕዱ ራዲዮና ጋዜጠኞች ጥፋት ምንድን ነው? የጃዋርና ጃዋር አለመሆናቸው አይደለምን?? ለእነ ጃዋር ሲሆን እንደ ህዋ ሰፍቶ የተለጠጠው ትዕግስት እና ልበ-ሰፊነት ለአሕዱ ሲሆን እንደ መርፌ ቀዳዳ የጠበበበት ምክንያት ምንድነው?
#ዓይን_ያወጣ ጎጠኝነት? ዘረኝነት? አድሏዊነት?
#እባጭ አምባገነንነት? ጨቋኝነት? አፋኝነት? ወይስ
#አጉል እብሪት? ትዕቢት? ማን-አለብኝነት? ቅብጠት?

በአጠቃላይ እንደ ጃዋር ያለ ሰው እንደፈለገው በሚያዛርጥበት ሀገር የአሕዱ ራዲዮ ጋዜጠኞች መታሰር ለብዙዎቻችን ከልክ ያለፈ፤ ጎጠኝነት፥ ዘረኝነት እና አድሏዊነት ነው!!! #በአሕዱዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ከልክ ያለፈ እባጭ አምባገነንነት፥ ጨቋኝነት እና አፈና ነው!!! ሌላው ሀገር እያተራመሰ “አለሁ ባይ” ባለግዜ የሌላቸውን ጋዜጠኞችን ማሰር፥ ማንገላታትና ማስፈራራት ለብዙዎቻችን በአጉል እብሪት የተሞላ ትዕቢት፥ ማን-አለብኝነትና ቅብጠት ነው!! አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በተናገረ ቁጥር ሀገር የሚበጠብጠው፣ እንደ ሰሞኑ ዝም ሲል ደግሞ ሰላም የሚወርደው፤ በሀገርና ህዝብ ላይ ቁማር እየተጫወተ ገንዘብ የሚያተርፈው ጃዋር የሀገር ሰላምና ደህንነት አደጋ ነው፡፡

ለእሱ ከጥፍር እስከ ፀጉሩ እንክብካቤ እየተደረገለት የአሕዱ ጋዜጠኞችን ማሰር በሁላችንም ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው፡፡ የአሕዱ ጋዜጠኞች ያጠፉት ብቸኛ ነገር ቢኖር እውነትና ትክክል ብለው ያመኑበትን ነገር በግልፅ መናገራቸው ነው!!! በግልፅ ሆነ በድብቅ ውሸት እየተናገረ ጥላቻና ቂም ሲሰብክ የሚውለው ጃዋር፣ ሁከትና ብጥብጥ የገቢ እና ዝናው ምንጭ የሆነ ሰውዬ ቆሞ እየሄደ ሌሎች ጋዜጠኞችን ማሰር የመጨረሻው #ቀይ_መስመር ነው፡፡ እንዲህ ከተጀመረ ደግሞ ከእኔ ጋር የምንስማማው አሕዱዎችን ፈትታችሁ ጃዋርን ስታስሩ ነው!!!

7 COMMENTS

 1. “የምንስማማው አሕዱን ፈትታችሁ ጃዋርን ስታስሩ ነው” አለች መስከረም! ከማን ጋር ነው የምትስማሚው፣ ከህወሃት ጋር?? ድሮስ መች ተጣላሽ?
  #ዓይን_ያወጣ ጎጠኝነት? ዘረኝነት? አድሏዊነት?
  #እባጭ አምባገነንነት? ጨቋኝነት? አፋኝነት?
  #አጉል እብሪት? ትዕቢት? ማን-አለብኝነት? ቅብጠት? በሙሉ የአንቺ እና የሃበሾች ተፈጥሮአዊ ባህርይ ሆኖ እያለ ሌላውን በነዚህ ለመክሰስ ያብከነከነሽ trade mark ተቀማን ለማለት ነው?? ለጀዋር ሲሆኑ ነው የሚያስከስሡት? ቢያስከስሱ ኖሮማ እስር ቤት በዬት ሊበቃችሁ ነበር!?? የአሕዱ ጋዜጠኞች አማራ ስለሆኑ እንዴት ተነኩ፣ ያንቺን አስተሳሰብ የማይጋሩት ደግሞ ለምን አልታሰሩም የሚል ነው ጩሄትሽ! እንጂ ትንሽ አመዛዛኝ ህሊና ኖሮሽ አይደለም። ለነገሩ ሜዲያዉን በሞኖፖል ይዛችሁታል፣ ግን የምትነዙት ዉሸት ሲበዛ ግዜ እዉነት የሆነላችሁ እየመሰላችሁ ጫጫታ አበዛችሁ እንጂ ሃቁ በቦታው ነው ያለው!! It is just an illusion! Just ilusion!

 2. የለየልሽ ዘረኛ ማለት አንቺ ነሽ ፡፡

  አንድ አማራ ጋዜጠኛ ተሠረ ብላችሁ የ ኦሮሞ አክቲቪስት ጃዋር ይታሠር እያሉ መቀባጠር የዘረኝነትሽን ልክ ከሚገናገር በለይ የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡

  ጃዋርን መሆን ሲያቅት አሱን ለማኮሰስ የምትሔዱበት ረቀት ይበልጥ ከሚያጀግነው ና ከሚያስከብረው በቀር የሚያመጣው ለውጥ የለውም፡፡

  ህዝብ ያከበረውን የመንደር ምናምንቴ ሊያኮስሰው አይችልም፡፡

 3. መስከረምን ከመስደብ ስዩም ተሾመን ለምን አትጠይቁትም? እርሷ ካለችው ምን ሀሰት አለው?
  ወደዳችሁም ጠላችሁም ያ የጋኔል ጋን ጃዋር አንድ ቀን የእጁን ማግኘቱ አይቀርም። እናንተ እርሱን ከብባችሁ የምታድኑት መስሏችኋል?
  ያ ህዝብን ከህዝብ ያፋጀበት ምላስ ይቆረጣል
  ያ ህዝብን ከህዝብ ያጣላበትን ጽሁፍ የፈበረከበት እጁ ይቆረጣል።
  የጊዜ ጉዳይ ነው። መንግሥት እርሱን ሊቀጣ ፈሪ ከሆነ ፈጣሪ ራሱ አረም እንደሚታረም ነቅሎ ይጥለዋል።

 4. What Meskerem said about Jawar Mohammed is true and it has nothing to do with your ethnicity. Jawar is a sharpened business man, who doesn’t care if Oromo,Amhara, Sidamas, Ethiopian Somalies goes to hell, the kerros and others are just a simple tools that takes him wherever he plans to be. Accusing Meskerem for being a racist is an fair and un just, we need to late it go our inferior complex for belonging to a certain ethnic group, it only prevents us to hear the truth and Jawar knows it and he uses that every time he gets the chance, how we that belongs to Oromo ethnic groups were oppressed,enslaved and underprivileged than others but the fact was all Ethiopians were oppressed.
  Good Work, Messe.

 5. @ምን አገባህ፣
  እኔ የጃዋር ጠበቃ አይደለሁም። ግን እዉነት እንነጋገርና “ያ ህዝብን ከህዝብ ያፋጀበት ምላስ” ምን ተናግሮ፣ “ያ ህዝብን ከህዝብ ያጣላበት ጽሁፍ” የትኛው እንደሆነ በግልጽ ማስረጃ ብታቀርብ አብረን እንከሰው ነበር! ክስ ያለማስረጃና ምስክር (በራስህ ፍርድ ቤት እንደሆን እንጃ እንጂ) ከስም ማጥፋት የተለየ ስላልሆነ በራሱ ያስከስሣልና ወይ አቅርብ፣ አሊያም አፍህን ሰብስብ! ያንተ የግል ጥላቻ (እውነት መጥላትን ጨምሮ) ምስክርና ማስረጃ ሊሆን አይችልም።

 6. እውነት እየተነገረ ያለው በአሀዱና ሸገር ሬዲዬ ሲሆን ጋዜጠኞቹም አንጋፋ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡እውነተኛ የኢትዮጵያ ድምፅ፡፡ የተሳሰተ መረጃ ቢዘገብ እንኳን ማስተካከያ ነው የሚጠየቀው፡፡ Intimidiation & harrasment መፍጠር ተገቢ አይደለም፡፡

  እራሰቸውን አግዝፈው ያለም በህግ የሚጠይቃቸው ባይኖርም እንደ ሮማን ኢምፓየር አንድ ቀን መጥፋታቸው አይቀሬ ነው፡፡ አትዮጵያ ግን ትቀጥላለች፡፡
  ኢትዬጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!

 7. @አባ ጫላ; ምነው ቀረርቶ አበዛህሳ? ነገ የሃገሩዋ አምባገነን መሪ እንደምትሆን እርግጠኛ የሆንክ ትመስላለህ! ግን አንድን የኤሶፕን ተረት አስታወስከኝ > አንበሳ እና አህያ አብረው አደን ሄዱ። አንድ የዱር አጋዘኖች የተደበቁበትን ዋሻ አገኙና አህያው ዋሻው ዉስጥ ገብቶ ወደ ዉጪ እንዲያባርራቸውና አንበሳም እየሸሹ ሲወጡ እንድይዛቸው ተስማሙ። እናም አህዮ ዋሻ ገብቶ እያናፋና እየረገጠ አስደነበራቸዉና ሲወጡ አንበሳ የቻለውን ያህል ያዘ። ከዚያም አህያው ወጥቶ “እንዴት እንዴት እንዳረኳቸው አየህ አይደል” ሲለው፣ አንበሳም “አህያ መሆንህን ባላዉቅ ኖሮ ስራህማ እኔንም ባስበረገገኝ ነበር!” አለው ይባላል! < መሆንና በአፍ ማስመሰል የተለያዩ ናቸው ለማለት ነው። አጥፊ ካለ በህግ ይጠየቃል። ዛቻህ ግን (በመንግስቱ ሃ. ማ. ዘመን) የደነቆረ ሰው ያስመስልሃል!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.