በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል የተቋቋመው ም/ቤት ስራውን ጀመረ

 በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቋቋመው ምክር ቤት ስራውን ጀመረ፡፡

በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰብሳቢነት የሚመራው ይህ ምክር ቤት የውጪ ጉዳይ ፣ ገንዘብ፣ ገቢዎች፣ ማዕድንና ኢነርጂ ፣ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ፣ ትራንስፖርት ሚኒስትሮች ፣ ብሔራዊ ባንክ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነትን፣ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ሌሎች ተቋማትን በአባልነት ማካተቱም ነው የተገለጸው፡፡

ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን በመከላከልና በመቆጣጠር ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወነችው ተግባር አበረታች መሆኑም ከምክር ቤቱ የግምገማው ውጤት መረዳት ተችሏል፡፡

የዚህን የወንጀል ምንጮችን ለማድረቅና ከሀገር የሸሹ ንብረትና ገንዘብ ለማስመለስም ምክር ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡም ነው የተገለጸው፡፡

ከላይ የተገለጸው ወንጀል ድርጊት የወንጀሎች ሁሉ ቁንጮ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ መረባረብ እንደሚጠበቅባቸውም ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

1 COMMENT

  1. Comment:if they do beyoned acussing falsely and only about theft of one vehicle tire i hope they will better. the issue is these elected persons are immune? my point is that such challenges will eased if there is civil movement as done in brazil etc

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.