“ችግር የለውም አትጨነቁ በአማርኛ ጠይቁኝ … አማርኛ እችላለሁ!!” አዲሱ የሩሲያ አምባሳደር ኢቪጅኒ ተርከሂን

“ችግር የለውም አትጨነቁ በአማርኛ ጠይቁኝ … አማርኛ እችላለሁ!!”

አዲሱ የሩሲያ አምባሳደር ኢቪጅኒ ተርከሂን በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች በእንግሊዝኛ ለመጠየቅ ሲደክሙ የመለሱላቸው።

2 COMMENTS

  1. ” “ችግር የለውም አትጨነቁ በአማርኛ ጠይቁኝ … አማርኛ እችላለሁ!!” አዲሱ የሩሲያ አምባሳደር ኢቪጅኒ ተርከሂን ”

    That is an important gesture. If journalists can not use Russian in this case, why use English for a non-UK or non-USA citizen ?
    I think the Chinese behave also the same way, they prefer to be asked in Mandarin or they use translator, they don’t like to use English.

  2. ይገርማል። በምድሪቱ የተወለድት የፓለቲካ ልክፍቶች ቋንቋው የጨቋኝ ነው እያሉ የሚያላዝኑትን ሩሲያዊው ሲናገሩት መስማት ምንኛ ደስ ይላል። ቋንቋ መግባቢያ ነው። በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች ሁሉ እንደ እንግሊዘኛ ቋንቋ የመጨቆኛ መሳሪያ የሆነ ቋንቋ በምድር ላይ የለም። ዛሬ ግን የታላቋ ብርታኒያ የቅኝ ግዛት የነቡሩና ያልነበሩ ሁሉ ቋንቋውን ለትምህርት፤ ለምርምር እና ለመግባቢያ ይጠቀሙበታል፡ የራሱ ፊደል ያለው አማርኛ ግን የአማራ ቋንቋ ነው እያሉ ሻቢያና ወያኔ አሁን ደግሞ የነሱ ሰይጣን የወረራቸው የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ሰው እንዳይማረው እንዳያውቀው ለማድረግ ለ 50 አመታት ጥረዋል። ቋንቋው ግን በውጭና በውስጥ ሃገራት እየተስፋፋ ይገኛል። ለዚህም ነው የሃገሬ ፊደላት ተቀምጦ በላቲን ኦሮምኛን ተማሩ ለሚሉኝ ጀሮ የለሌኝ። የሃገራችን ቋንቋዎች ሁሉ የራሳችንን ፊደላት ተጠቅመው አንድ ያንድን ቋንቋ ማወቁ ለአያሌ ነገር ይጠቅማል። ይሁን እንጂ አፍራሽን አፍራሽ እየተካው ስንፋለም ጊዜው መሸ። የሩሲያው ሰው በአማርኛ ቋንቋ መናገራቸው ድርሻየን፤ ድንበሬን ባንዲራየን የሚሉ ጭፍን የፓለቲካ እውራንን የእውነትን ጭላንጭል ብርሃን ለማየት እንዲችሉ አመላካች ይሆናል እላለሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.