ቋ ን ቋ ን መ ሰ ረ ት ያ ደ ረ ገ የ ማ ን ነ ት ፣ የ ክ ል ል ፓ ለ ቲ ካ ና ፣ ህ ገ መ ን ግ ስ ቱ ፣ ለ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ት አ ን ድ ነ ት ተ ፃ ራ ሪ ነ ዉ ።

የኢትዮጵያ፤የውዪዪትና፤መፍትሔ፤መድረክ  (EDF)
Ethiopian Dialogue Forum
9900 Greenbelt RD. E#343 – Lanham, MD 20706

May 30, 2019

በቋንቋ፣  በጎሳና  በክልል  የተደራጀው  የፌዴራሉም  ሆነ  የክልል  መንግስታት  የአገራችንን  የፖለቲካ  ስልጣን መዋቅሮች  ከተቆጣጠሩበት  1983  ዓ.ም.  ጀምሮ  የኢትዮጵያ  ጥንታዊ  ታሪክና  ቀጣይነት፣  የህዝባችንንም አንድነትና   አብሮነት   ተክዶ   በምትኩ   አገርና   ህዝብን   ማፈራረስና   መበተን   ዓላማው   የሆነ   ኢህአደጋዊ መንግስት መቋቋሙ ይታወቃል።

ህገመንግስቱም   ሆነ   ዋንኞቹ   የመንግስት   አካሎችም   በዘር   ላይ   ለተመሰረተው   ፌደራላዊ   ስርዓት   ህጋዊ ዋስትና    ለመስጠት   የተደነገጉና        የተዋቀሩ፣      የህዝባችንንም      መብት   የደፈጠጡ   መሆናቸው  በተግባር ተረጋግጧል።

በየጊዜው   የምንመለከተውም   ሆነ   የምንሰማው፣   ህዝባችን   ከተወለደበት፣   ሃብት   ካፈራበትና፣   ኑሮውን ከመሰረተበት  ስፍራ  የዚህ  ወይም  የዚያ  ቋንቋና  ጎሳ  አባል  አይደለህም  እየተባለ  መሰረታዊ  መብቱ  ተጥሶ፣ ሲንገላታ፣   ሲፈናቀልና፣   ሲሰደድ   መኖሩን   ነው።        ከሶስት   ሚሊዮን   በላይ   የሚሆን   ህዝብ   ከተለያዩ

አካባቢዎች  ተፈናቅሎ  እጅግ  አሳዛኝ  የሆነ  ጭንቀት  ውስጥም  ወድቋል።

ረሃብና  የኑሮ  ውድነት  እጅግ  በሚዘገንን  ደረጃ  ላይ  ይገኛል።  በፍጥነት  ኢኮኖሚዋ  እያደገ  ነው  እየተባለ ህዝባችን  ለረሃብና  ለበሽታ  ተጋልጥዋል።  ከስምንት  ሚሊዮን  በላይ  ህዝብ  ለሰብአዊ  እርዳታም  ተጋልጧል። ስራ   አጥነት   በገጠሪቱም   ሆነ   በከተማዎች   ተበራክቷል።   በአንዳንድ   ከተሞችም   ከ50%   ያላነሰ   ወጣት ትውልድ  በስራ  አጥነት  ይንከራተታል።

ህዝባችን  የሰላምና  የደህንነት  ህይወት  አጥቶ  በፍርሃትና  በስጋት  ይኖራል።  በጠራራ  ፀሃይ  የህዝብ  ንብረት የሆኑ  ባንኮች  ይዘረፋሉ።  ጠያቂና  ተጠያቂ  የለም።  መንግስት  አልባ  የሆነች  አገር  ትመስላለች  ።

 

ስለሆነም፦

1፦  ለዚህ  ሁሉ  ማህበራዊ  ፖሊቲካዊና  ኢኮኖሚያዊ  ችግሮችና  የአንድነታችንና  የአብሮነታችን  መናጋት  ፣ የአገራችን   ታሪክ   መደብዘዝና   ቀጣይነቱ   አደጋ   ላይ   መውደቅ   ዋንኛውና   ብቸኛው   ምክንያት   ገዢው ፓርቲና(ኢህአደግ)   መንግስት   የሚከተሉት   በቋንቋና   በጎሳ   ላይ   የተመሰረተ   ርእዮት   ዓለምና   የክልል መንግስታት  አስተዳደር  ነው።  ስለዚህ  ኢትዮጵያንና  ህዝባችንን  ልንታደግ  የምንችለው  ጸረ  ኢትዮጵያና  ጸረ ህዝብ   ከሆነው   በዘር   በቋንቋና   ጎሳ   ላይ   ከተመሰረተው   የፖሊቲካ   አደረጃጀትና   አመራር   ሙሉ   በሙሉ ስንላቀቅ   በመሆኑ፣   መንግስት   እውነት   ከስህተቴ   ተምሬአለሁ፣   ለኢትዮጵያዊነትና   ለለውጥ   ቆሚያለሁ የሚል   ከሆነ   አርአያነቱን በመውሰድ   ይህንን   የሰውን   ዘር   የሚጻረር   የፖሊቲካ   አካሄድ   እንዲያወግዝ

በጥብቅ   እንጠይቃለን።   በተመሳሳይ   ሌሎች   ህዝብን   እናደራጃለን፣   እንመራለን   የሚሉ   ድርጅቶች   ሁሉ ራሳቸውን  ከጎሳና  ከዘር  ፖለቲካ፣ ከክልል  አስተዳደር  ማላቀቅና  በኢትዮጵያዊነት መጽናት እንደሚጠበቅባቸው     እያሳሰብን  ህዝባችንም  ተጽዕኖ   ሊያደርግባቸውና “የዘር    የጎሳ  ፖሊቲካንእንቃወማለን”  እንዲላቸው  ህዝባችንን  እንማጸናለን።

2፦  በብሄር  ብሄረሰብ  ልኡላዊነት  ላይ  ብቻ  የቆመው  ፣  የኢትዮጵያን  ልኡላዊነት  የሚጻረረው  ፣  በህዝብ ተደጋፊነት      የሌለው    ህገመንግስት       የዜግነትን      የሰብዐዊና     ዲሞክራሲ  መብቶችን   የሚያፍን               በመሆኑ

በአስቸኳይ   ሊገደብ   ይገባል።   ስለሆነም           ለህዝብ   ከህዝብ   የተውጣጣ   ሁሉ   ባለድርሻዎች   የተስማሙበት የህገመንግስት  አርቃቂ  ኮሚሽን  ተቋቁሞ  ስራውን  በአስቸኳይ  እንዲጀምር  እናሳስባለን።

3፦   ከመንግስት   ቀዳሚና   ዋነኛ   ተልዕኮዎች   አንዱ   የአገራችንን   ህልውና   የህዝባችንን   ሰላምና   ደህንነት ማስጠበቅ  ነው።ባለፉት  ዓመታትም  ሆነ  ዛሬም  ጭምር  የምንመለከተው  ኢትዮጵያውያኖች  አብሮ  በሰላም የመኖር  ልምዳቸው  ተናግቶ፣       ሽብርና  ግድያ  መፈናቀል  በየቦታው  ተበራክቶ፣  ሰላም  ጠፍቶ፣  ትውልዱ

በፍርሃትና  በስጋት  እየኖረ  ነው።  መንግስት  ከጊዜ  ወደ  ጊዜ  አገርን  የማስተዳደር  ችሎታውና  ተቀባይነቱ እየመነመነ      በመምጣቱ  የዜጋዎችን     መብት  የሚያስከብር    የህግ     የበላይነት               የሚተገበርበት   ሁኔታዎች መዳከማቸዉ  በግልፅ  ይታያል  ።

ስለሆነም፣   ህዝባችንና   አገራችን   ወደ   ከፋ   አዘቅት   ከመግባታቸው   በፊት   የሚመለከታቸው   ፣ከመንግስት (ገዢ    ፖርቲ)፣ከደጋፊም      ሆነ    ተቃዋሚ፣ተፎካካሪ     የፓለቲካ     ድርጅቶች፣ከህዝባዊ       ድርጅቶች፣ከሙያ

መሀበራት፣ከሀይማኖት  ድርጅቶች፣ከከፍተኛ  የትምህርትና  የምርምር  ተቋማት፣ከቲንክ  ታንክ  ድርጅቶች፣ ከታዋቂና  አገር  ወዳድ  ዜጋዎች፣እንዲሁም  ባለድርሻ  የሆኑ  ተመሳሳይ  ድርጅቶች  ሁሉ  የሚሳተፉበት  የጋራ ጉባኤ   ሊጠራ   ይገባል   እንላለን።ይህም   የጋራ   ጉባኤ   የአገሪቱን   የወደፊት   ዕጣ   ፈንታ ላይ   በመነጋገር ዲሞክራሲያዊት  ኢትዮጵያን  ለመገንባት  የሚያስችለውን  ጉዞ  የሚቀይስና  የምንመራበትን  የፖለቲካ  ስርዓት አማራጭ  ሀሳብ  አመንጪ  መሆን  እንዳለበት  አጥብቀን  እናስታውቃለን።

 

ዘረኝነትንና  የጎሳ  ፖሊቲካን  አጥብቀን  እንቃወማለን።

ኢትዮጵያን  ታሪኳንና  ህዝቧን  እናክብር።

ሁላችንም  የአንድ  አገር  ልጆችና  አንድ  ህዝበ  ኢትዮጵያዊ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.