ኢትዮጵያን ከነውርና ርኩሰት የሚያድ መሪ ይስጠን! (ሰርፀ ደስታ)

ሰሞኑን ብዙ ነገር የሚደብር አለ፡፡ የሚከተሉትን ላንሳ

የሶዶማውያን ፉከራ፡- በቅድስናው ቦታ የርኩሰት ሥራ ሲሰራ አንባቢው ያስተውል የሚል ቃል በመጻፈ ቅዱስ ያነበብኩ መሰለኝ፡፡ ሌላው ከመጻፍ ሁሌ ትዝ የሚለኝ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው የፈላስባው የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ነው፡፡ ሐይማኖትም ባሕላዊ እሴቶችም ሁሉም የእኛ የነበሩ ነገሮች በፍጥነት እየተሸረሸሩ ናቸው፡፡ ሰሞኑን የሰዶማውያን ወደ ኢትዮጵያና ሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ነውራቸውን ለማዛመት ጉዞ እናደርጋለን በሚል በይፋ ሲደነፉ እያየን ነው፡፡ እንግዲህ ነውረኞች ነውራቸውን ለማስፋፋት መብታችን ነው እያሉ ሲደነፉ እምነቱን፣ ባሕሉን ማንነቱን፣ በአጠቃላይ ስብዕናውን ሊያረክሱበት የሚመጡበትን የመከላከልና አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ የመውሰድ መብት እንዳለው እነ በዲሞክራሲ ሽፋን የነውር አዛማቾች አይቀበሉም፡፡ የውጭ ወራሪ አገርን ሲወር ከሚደረገው ጦርነት በላይ ይሄ መሠረታዊ የሆነን የስብዕናን ማንነት የሚያጎድፍን ነውር ሊያዛምቱ ወደ አገራችን ዘልቀው ለመግባት ያሰቡትን ሕዝብ ራሱን የመከላከልና ጠላቶቹን የመበቀል መብት አለው፡፡ ዛሬ በዲሞክራሲ ሰበብ የፈቀዱትም ችግር ውስጥ ገብተዋል፡፡

መንግስት እንደ ሕዝብ አያስብ ብንል እንኳን በአገሪቱ ሕግ መሠረት ሶዶማዊነት ወንጀል እንደሆነ ማስጠንቀቅ በተገባው ነበር፡፡ ጉዳዩን ብዙ ማጮኸ ሳይሆን በተግባር የተገለጠን እርምጃ መውሰድ ግድ ይላል፡፡ ብዙዎች የእነዚህን ነውረኞች ጋር የተያያዘን ዜና ሁሉ ከነውረኞቹ ምልክት ጋር ሲለጥፉ ታዝቤያለሁ፡፡ ይሄ አንዱ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ እነዚህ ነውረኞች ከሚፈልጉት ነገር አንዱ ምልክታቸውን በብዛት ማስተዋወቅ ነው፡፡ ወሬያቸውንም እንደዛው፡፡ አሁን ራሱ ዋና ዓላማቸው እንዲህ ትልቅ ወሬ በመፍጠር ራሳቸውን ከሌላው ጋር ማለማመድ ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያሉ ነውረኞችን በተቻለ መጠን በውስጥ በልዩ ሁኔታ እርምጃ መውሰድን ይጠይቃል፡፡ ዛሬ ይሄን ያህል ተወራ ለሚቀጥለው 10 ዓመት ግን መብታቸው ነው የሚለው እንዳይበዛ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ ሰው በተፈጥሮ ከእንስሳ የሚለየው አስባለሁ በሚል በሚሰራቸው ከተፈጥሮ የወጡ ድርጊቶች አንዱ ሰዶማዊነት ነው፡፡ እንስሳት በተፈጥሮ ከተሰጣቸው የማንነት ሥርዓታቸው አይወጡም፡፡ እንግዲህ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደደው መጠን እንዲህ ላሉ የረከሱ ነውሮች አእምሮው ይገዛል፡፡ ሰዶማዊነት ጄኔቲክ ወይም በተፈጥሮ ያለ ሳይሆን ሰዎች በራሳቸው የአስተሳሰብ ነውረኝነት የሚያመጡት ችግር ነው፡፡ ለዛም ነው የሰው ልጅ እምነት፣ ሥርዓትና ባሕል የሚያስፈልጉት፡፡ ሰው ያለ እነዚህ እሴቶች እንደእንሰሳ ተፈጥሮአዊ መሆን አይችልም፡፡ በቀጥታ የሰይጣን ማደሪያ የመሆን እድል አለውና፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያ ኦረቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውግዘት አስተላልፋለች፡፡ በሌሎች እምነትም ቢሆን የሚወገዝ ከስብዕና የወጣ ነውር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስለቅዱሳን መካናቶቿ ብቻ ሳይሆን ስለምድሪቱ ኢትዮጵያ ጭምር ነው ውግዘቷ፡፡ እርምጃው ሊሆን የሚገባው ላሊበላና ሌሎች ቅዱሳን ቦታዎች ሳይሆን በአጠቃላይ በሰዶማውያንነት ተደራጅተው የሚመጡትን ከየትኛውም የአገሪቱ መዳረሻዎች ማገድ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የመንግስት ዋነው ሥራው ነው፡፡ በሕጉ ወንጀል የሆነን ድርጊን የሚያስፋፉ ወንጀለኞችን በየትኛውም ቦታ ቢሆን በቱሪስትነትና በዲሞክራሲ ሽፋን መቀበል የወንጀለኞቹ ተባባሪ መሆንና በኢትዮጵያ ምድር እንደመንግስት መቀጥል የሌለበት ነው፡፡   በቃ ጫጫታ አያስፈልግም መንግስት ኃላፊነቱን ከአልተወጣ  ሕዝብ የትኛውንም እርምጃ የመውሰድ መብት አለው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የእምነት መሪዎች ሕዝብን ለነውር እያጋለጣችሁና ከእምነት እያወጣችሁ ነው፡፡ ሰው ከእምነት፣ ባሕልና ሥርዓት ከወጣ ከላይ እንዳልኩት እንሰሳ እነኳን ሆኖ መቀጠል አይችልም፡፡ አሁን አሁን የምናየው የእምነት መሪዎች ከእምነቶቹ መሠረታዊ ሥርዓት በወጣ ሕዝብን ከእምነት የሚያሸሽ ነው፡፡ እምነት ታላቅ ፍልስፍና ነው፡፡ እባካችሁ አስተውሉ፡፡

የእስክንድርና ኦነጋውያን ግብግብ፡- እንግዲህ እስክንድር ራሱን ነጻ አውጥቷል፡፡ አንድም ፓርቲ ነኝ ባይ በእስክነድር ላይ የተደረገውን የእነአብይን ሴራ አልነቀፈም፡፡ አዲስ አበባን ከአደገኛ ወሮበሎች ለመከላከል ሕዝብን ማደራጀት መብት ብቻም ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ ነው፡፡ የአብይ ቡድን ወሮበሎችን በፖሊስ እገዛ ኮንደሚኒየም በማስከልከል ብቻ አልተወሰነም፡፡ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ 30 ሺ ቤት አፈርሳለሁ እያለ ሲደነፋ እስክንድር ይሄ ሊሆን አይችልም በማለቱ የብዙዎችን ማንነት እስከምንታዘብ ድረስ በእስክንድር ላይ ዘመቻ ተከፍቶ አይተናል፡፡ ኋላም የሳተላይት ቲቪ ለመመስረት መግለጫ ሊሰጥ የነበረውን ከልክሎታል ነውርን የማያውቀው የኦሮሞ መንግስት (የኢትዮጵያ ሊሆን አልቻለም)፡፡ ታከለ ኡማ ለእናቶች አዛኝ ለመምሰል ዲስኩር ሲያሰማ ነበር፡፡ መቼም አስመሳይነትና ውሸትን የተጠመቁበት ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ እናቶችን ከለገጣፎ ከኖረ ቤታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ የጣለ አረመኔና ዘረኛ  ቡድን ዛሬም አዛኝ ነኝ ሲል እባብ ሞኝን ሁለት ጊዜ ነደፈው አይነት ነው፡፡ እነ አብይ ግልጽ ሊሆንላቸው የሚገባ ጉዳይ ከዚህ በኋላ ምንም እድል እንደሌላቸው ነው፡፡ ሰሞኑን ዶ/ር ተድላ የአብይ ችግር የፓስተርነት ነው ይለናል፡፡ ተድላ የተሳሳተ መሠለኝ፡፡ የኦነጋውያንን አስተሳሰብ በደንብ ስለማይረዳ የአብየን ችግር ከፓስተርነት ጋር አገናኘው፡፡ ችግሩ ያለው ለዘመናት የተሞሉት የዘረኝነትና ጥላቻ አስተሳሰብ መልካም እናስብ ቢሉ እንኳን አይቻላቸውም፡፡ በይፋ መዋቅሩን ሁሉ በስግብግብነት በኦሮሞ ሞልቶ ይሄው አለሌ ኦነጋውያን እየጨፈሩበት ነው፡፡ አሁን የባክ ዘረፋው አዲስ አበባ ደርሷል፡፡ የሚዘረፉት ባንኮች ደግሞ የማን እንደሆኑ አስተውሉ፡፡ እስክንድር የእነአብይን ማንነት ግልጽ እያወጣ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች አስመሳዮችን ጭምር ማንነታቸው እንዲጋለኝ ምክነያት ሆኗል፡፡

አብይን ዛሬ ላለበት ስልጣን ያበቃው እስክንድር እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እስክነድር ወያኔን በመጋፈጥ ለአለም የወያኔን ሴራ ያጋለጠ ብቻውን ብዙዎች የፈሩት ሰው ነው፡፡ አሁንም እውነትን አትተላለፉም በማለቱ ጥርስ ነክሰውበታል፡፡ ከእስር የፈታው አብይ ነው ይላሉ እውነትን ለማወቅ የማይወዱት፡፡ ዓለም በወያኔ ፖለቲካ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ የነበረው ከማንም በላይ በእስክንድር ምክነያት ነው፡፡ ኢንግሊዛዊው አንዳርጋቸው እንኳን የእስክንድርን ያህል ትኩረት አልነበረውም፡፡ አሁንም የእስክንድርን ከእውነት አለማፈግፈግ እና አስመሳይ አለመሆን እጅግ ያስፈራው የአብይ ኦነጋዊው ቡድን ቀይመስመር አስከማለፍ እየደረሰ ነው፡፡ የኢዲስ አበባን መስታዳድርና ፖሊስን በኦሮሞነት የተቆጣጠረው ቡድን ወሮባውን ጀዋርን እያጀበ እስክነድርን ሰላማዊ መግለጫ አትሰጥም በሚል የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ የእነእስክንድር ባልደራስ ባይኖር ለመሆኑ ስለሕዝቡ የሚናገር ማን ነበር?

ኢሳት፡- ኢሳትን ድሮም ቢሆን እኔ አልወደውም፡፡ ከመጀመሪያውም ችግሩ ይታየኝ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜም ተናግሬያለሁ፡፡ ይባስ አሁን በይፋ የአብይ ጠበቃ ሆኖ የራስን ማጥፋት እርምጃ መውሰዱ የራሱ የኖረ ችግር ነው፡፡ ብዙዎች በኢሳት ጉዳይ ቴድሮስ ጸጋዬን ሊከሱም ሲሞክሩ አይቻለሁ፡፡ ለሕሊናችሁ እደሩ፡፡ ቴድሮስ የፈለገውን የራሱ አጀንዳ ቢኖረው ኢሳት ላይ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡ ለሪዮት የሰጠው ቃለምልልስን ያላስተላለፈው ኢሳት ራሱ እንጂ ቴድሮስ ምን አጠፋ፡፡ በተቃራኒው ከማንም በላይ በአሁኑ ወቅት አመክንዮዋዊና በመረጃ የተደገፉ እውነቶችን ለሕዝብ በማድረስ ቴድሮስ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡ የእነ አብይን የጓዳ ሴራ ሳይቀር ለሕዝብ ያደረሰው ቴድሮስ ነው፡፡ በማይታበል መረጃ በማቅረብ፡፡ ኦሮሞ ስለሆነህ ቴድሮስን መጥላት ያው የተሞላህውን ዘረኝነትና ጥላቻ ካልሆነ የለማንና አዲሱን ነውር የሆነ ንግግር እንደሰው ማውገዝ በቻልህ ነበር፡፡ ለማንኛውም ከነውርና እርኩሰት እንጽዳ፡፡ ለእነ አብይ ከጎዳና ቆሻሻ በፊት ራሳችሁን አጽዱ እላለሁ፡፡ እጅግ ማስመሰልና መዋሸት ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፡፡ አገር እንደ አገር እየሄደች አደለም፡፡ ብዙ ተስፋ የተደረገው ነገር ሁሉ  ተበላሽቷል፡፡  ዛሬ አገራት ለኢትዮጵያ ያላቸው እይታ ብዙዎች እንደሚያስቡት አደለም፡፡ በተለይ ምዕራባውያን የመንግስትና መሪነት ፕሮቶኮልን ትልቅ ቦታ ይሰጡታል፡፡ አንድ ሰሞን አብይን ሕዝቡ ሲቀበለው አይተው የተደመሙት ምዕራባውያን ድሮውንም ሊሆን የሚችለውን ቢረዱም ትንሽ ለማበረታታት ሞክረው ነበር፡፡ አሜሪካ ከጅምሩ የኦሮሞነት አስተሳሰብ አደጋ እንደሚሆን ለአብይ ለራሱ ጥቆማ አድርጋለት ነበር፡፡ አገር መምራት አትችሉም እንደ አገር አታስቡም እንድ ኦሮሞ ነው ብለዋቸው ነበር፡፡ የተናገሩት ነው ዛሬ በይፋ የሚታየው፡፡ ከወያኔ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ዛሬ ወራዶች እንደሚያስወሩት ሳይሆን በዛ ዘመን አገርን እንዴት እንደመሩና ዛሬ አብይ በኦሮሞነት የገባብን ቤተመንግስት እነደሰሩ በወያኔና ኦነግ ላደጉ ለእነ አብይ ከቶም አይታያቸውም፡፡ ዶር ተድላ እንዳለው የአብይ ችግር የፓስቶራል ሳይሆን ዋናው ችግሩ በኦሮሞነት መጥበብ ነው፡፡ አብይም ሌላውም፡፡ በጥላቻና ዘረኝነት ታውረው ሲስገበገቡ የደረሳቸውን ትልቅ እድል ለራሳቸውም አበላሹት፡፡ አዝናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር አገራችንን ከርኩሰት፣ ከአስመሳዮችና ከሴረኞች ይታደግ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

1 COMMENT

  1. ትንሽ ያነበብክ ትመስለኝ ነበር:: ያው አንተም ዶማ ጭንቅላትህን አጋለጥክ ከኦባማ በእውቀት ትበልጣለህ? እሱ ተቀብሎ አክብራቸዋል:: ለጥቁር ህዝብ እኩልነት የሚታገሉ አጋሮች ናቸው::ሳይንስ ስለእነሱ ያረጋገጠውን አትቀበልም?
    እነዚህን ሰዎች እግዚአብሄር ሲፈጥራቸው ልክ አጭርና ረጅም አድርጎ እንደሚፈጥር ፈጥሯቸዋል:: ይህ የእነሱ ምርጫ አይደለም:: የቱሪስት ህግ ጠብቀው ለጉብኝት ቢመጡ ሀገሪትዋ ቱሪስምን ከፈለገች የግድ ማስተናገድ ይጠበቅባታል:: ይህን አይነት ጭፍን አመለካከት የሚራመድ ከሆነ ከሰለጠነው ሀገር የሚመጡ ሌሎች ቱሪስቶች ኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ ያደርጋሉ? አቅም አላቸው::ማን ይጠቀማል ከህውሀት በስተቀር? ጳጳሱም የህውሀት ሹመኛ ስለሆኑ ይህን ያራግባሉ::በየቦታው የሚገደለው ወገን ቢጮሁለት እንዴት ባማረ! እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ባይመጡ ሌሎች ሀገሮች ምርጫ አላቸው::ለምን ከቢያንሴ ጋር ሲያሽቃብጡ ሀጢአቱ አልታያቸውም?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.