“ለኢትዮጵያ አዲስ የጋራ ራዕይና ፍኖተ ካርታ ያስፈልጋል።” ገረሱ ቱፋ- SBS Amharic

አቶ ገርሱ ቱፋ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የቅርብ ተመልካችና ተሳታፊ ናቸው። በቅርቡ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂ ኃይል እንደሌለውና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ፓለቲካዊ ተሣትፎውን ማካሄድ እንደሚሻ የመግለጡን ዕሳቤና የኢትዮጵያን የለውጥ ሂደት አስመልክተው አተያይቸውን ያንጸባርቃሉ።

SBS Amharic

2 COMMENTS

 1. ወንድሜ ገረሱ ችግሩ እኮ የራእይ መብዛቱ ነው። እንደ ስብሰባው ብዛት፤ እንደ ቃላችን ክምር፤ እንደዘፈናችን መሻት እንደ ጠ/ሚሩ ዲስኩር ዛሬ ሃገሪቱ ማለፊያ መንገድ ላይ በሆነች ነበር። ግን አይደለችም። ደብረማርቆስ ላይ ተማሪ ሲገደል፤ ትግራይ ውስጥ በብቀላ ሌላው የድሃ ልጅ ይገደላል። በደ/ብርሃን ዪንቨርስቲ እንደ ዋዛ የተነሳ ድንጋይ ውርዋሮ ወደ ዘር ፓለቲካ ተለውጦ የከተማ ፊልሚያ ሲደረግ ማየትና መስማት ያማል። ከዚህ በዘለለ በየትምህርት ተቋማቱ ወደ ሴቶች የምኝታ ቦታ በመግባት በር እየሰበሩ ጾታዊ ጥቃት እንደፈጸሙና እንደከጀሉ ይነገራል። ሃበሻው የተማታበት ህዝብ ነው። ዝፈን ሲሉት ያለቅሳል፤ አልቅስ ሲሉት ይዘፍናል። ሰው ገድሎ፤ አስገድሎ፤ የሰው ንብረት ዘርፎ እንቅልፍ የሚወስደው የተማታበት ትውልድ። በዘርና በጎሳው ካልተከለለ በስተቀር በራሱ እይታና እምነት መኖር የማይችል የማይመስለው።
  ዘረኞች እውሮች ናቸው። በቅርቡ “ጌታቸውን እኔ ነኝ” የሚል ቲ-ሸርት ለብሰው በመቀሌ ከተማና በዙሪያዋ የተሰለፉትን ማየት በቂ ይሆናል። ለኳስ ከትግራይ አዲስ አበባ የገቡት የክለብ አፍቃሪዎች አነ ወያኔ እዮ… እኔ ወያኔ ነኝ በማለት ሲደነፉ ማየት ውርደት ነው። ወያኔ ለትግራይም ሆነ ለኢትዮጵያ ያደረገው እዚህ ግባ የሚባል ነገር የለም። ያው በየአመቱ የኤርትራ ነጻነት እየተባለ በውጭ ሃገር ጭፈራ ቤት እንደሚከደው አይነት ቀልድ ነው። የኤርትራ ነጻነት በከበሮና በክራር የሚለካ ቢሆን ኑሮ እንዴት ጥሩ ነበር። ሰው ሁሉ ሸሽቶ ኦና በቀረች ሃገር የመዝናኛ ሰበብ ተፈልጎ እሸሼ ገዳሚ መባሉ የውስጥ መታመምን እንጂ መፈንደቅን አያሳይም። በዚያው በሃገሩ በኤርትራ ሃበሳ የሚቆጥረውን በግድ ተሰለፍ፤ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ ግባ፤ ለሃገርና ለወገን ነው ተብሎ በየቀበሮ ጉድጓድ ጭንቅ ስለሚቆጥረው የኤርትራ ወታደር የውጭ ኤርትራዊያን ቢገዳቸው ምንኛ መልካም ነበር። የሚገርመው ኢሳይያስ ቢሞቱ ወይም በሃይል ከሥልጣን ቢወርዱ የሚፈጠረውን ትርምስ መገመት ይቻል ይሆን? ለምን እንዲህ ያለ ክፉ ነገር ይታሰባል እሳቸው እኮ ዘላለማዊ ናቸው። አይሞቱም አይለወጡም። እሰየው ያቆያቸው እንዳሉ!
  በሽፍጠት የተሞላው የኢትዮጵያው ፓለቲካ እንደ እማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ እየተማማለ ያዘግማል። ከላይ ለማለት እንደተፈለገው በወሬ ብቻ የሚነዳ የንጽህ ሰዎች ደም በየቀኑ የሚፈስበት፤ የመጻፍ የመናገር የመሰብሰብ ነጻነት አለ ተብሎ እንደ እነ እስክንድር ደስታ ያሉት ጋዜጦኞችና የሰባእዊ መብት ተሟጋቾች ዛሬ እንደ ወያኔ ጊዜ አፋቸው እንዲሸበብ ተደርገዋል። የኦሮሞ ፓለቲካ ወያኔን ከተካ በህዋላ ነገር አለሙ ሁሉ ልክ እንደትናንቱ ለእኔ ብቻ ሆኖአል። ለሃገር የሚያስቡ፤ አንድነትን የሚያራምድ ሁሉ ኦነግን በመሰሉና በዘር በሰከሩ አደፍራሽ ሃይሎች በየምክንያቱ ጥቃት ሲደርስባቸው ይታያል። በመቀሌ የሞተው ልጅ ደም እና በደብረማርቆስ የተገደለው የትግራይ ተወላጅ ደም አንድ ነው። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ወያኔ፤ ሻቢያ፤ እና የኦሮሞ አክራሪዎች ከሌሎች ተለጣፊ ድርጅቶችና ለአማራ ህዝብ ቁመናል ከሚሉ የወሬ ቋቶች የሚመነጨው ይህ እኔን አትመስልም እና ውጣልኝ ተወገድ የሚለው ሸፋፋ ፓለቲካ እስካልተገታ ድረስ መገዳደላችን ይቀጥላል። የድሃ ልጅ ይሞታል። የድሃ እናት ታለቅሳለች። ማቆሚያ የሌለው የመከራ ዝናብ!

 2. ” “ለኢትዮጵያ አዲስ የጋራ ራዕይና ፍኖተ ካርታ ያስፈልጋል።” ገረሱ ቱፋ- SBS Amharic ”

  Who is this guy ?

  First of all, Ethiopia is an ancient country, with thousands of years of history (well, some could be recent arrivals).

  If he means by አዲስ, something different from TPLF’s and Abiy’s tribalism, then that is at least something. By the way i have yet to listen to what he said.

  But when we say አዲስ, we should know that the TPLF and Abiy imposed old system of tribalism is A NON-ETHIOPIAN SYSTEM, designed by Benito Mussolini and brought to Ethiopia by the CIA. The tribalist system IS NOT an Ethiopian system, it was imposed by agents of foreigners like TPLF and retarded Abiy.

  We need to view tribalists as foreign agents and traitors who should be accused of treason.

  Ethiopia doesn’t need አዲስ system, it has already a well-functioning and wise system that managed to create the only independent black country on the planet, thanks to the victory in Adwa. What we need to do is to remove the TPLF and Abiy imposed NON-ETHIOPIAN SYSTEM of tribalism.
  Well, we can make improvements here and there, but the ancient country has already a well-functioning system.

  By the way, tribalist Abiy and his ilk need to be accused of treason, genocide and crimes against humanity for lying to Ethiopians and for their crimes of the past 14 months.

  Down with tribalists, who are foreign agents and traitors !

  Power to Ethiopian nationalists, the group of Ethiopians foreigners are so scared of !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.