የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አዲስ መፅሀፍ

የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አዲስ መፅሀፍ በሀገር ውስጥ አዲስ አበባ ክብሩ መጸሀፍት መደብር ያገኙታል። ትናንት ለነጻነት ትግሉ ህይወቱን አደጋ ላይ የጣለው አንዳርጋቸው ጽጌ- የዚህን መጽሀፍ 70% ገቢ ለኢዜማ በስጦታ አበርክቷል። ሌሎች በህዝብ ገንዘብ ይከብራሉ:: እነ አንዳርጋቸው እሁንም ያቅማቸውን ለህዝብ ትግል ያውላሉ።
Meskerem Abera:

አቶ አንዳርጋቸው ትሁት በመሆኑ የመፅሃፉ ድራፍት ወደ ማተሚያ ቤት ከመሄዱ በፊት ኮመንት እንዳደርግ እንደሚፈልግ ነገረኝ፨

መደናገሬ አልቀረም! “እኔ አንተን ኮመንት ማድረግ አይከብደኝም ብለህ ነው?” አልኩኝ። አቶ አንዳርጋቸው በተለይ በግል ሲያናግሩት ብዙ መናገር አያበዛም ፣አጠር አድርጎ “አንች ደሞ! Humility ሲበዛ arrogance እንደሚሆን አታውቂም? እልክልሻለሁ በአጭር ጊዜ አይተሽ ትልኪልኛለሽ” ሲል መለሰልኝ። ቀጠለ “በፈለግሽው መንገድ እይው፣የሚገባ ይግባ ፤የሚወጣ ይውጣ ለማለት እንዳትሳቀቂ፣ግን በአጭር ጊዜ ጨርሰሽ ላኪልኝ” አለኝ። “እሽ” ብዬ ልሄድ ተነሳሁ።

በሳምንቱ ኢሜሌን ስከፍት የመፅሃፉን ድራፍት አገኘሁት። ፕሪንት አድርጌ ገባሁበት! የሁልጊዜ አንደኛዬ ከሆነው “ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጭ”መፅሃፍ በመንፈስም በአቀራረብም ለየት ያለ ሆኖ አገኘሁት። ያኛው የሃገራችን ፖለቲካ፣ባህል፣ፍልስፍና፣ታሪክ፣የትምህርት ስርዓት፣ስነ-ልቦና እና ሃይማኖት ተጣምረው የፈጠሩት ክፋት ልማት የተፈተሸበት ኮስተር ያለ መፅሃፍ ሲሆን ይህኛው ደግሞ ዘና ያለ ግን ደግሞ ከፀሃፊው ቁም-ነገረኛነት የተነሳ ቶሎ ወደ ቁምነገሩ የሚገባ ፣በፀሃፊው ግላዊ ታሪክ አድርጎ፣ በአዲስ አበባ ዘ-ፍጥረት አልፎ፣የኢህአፖን ውስጠ-ፓርቲ ስንክሳር ፣የመሪዎቹን ሰውኛ ዘይቤ ፣የመኢሶን ኢህአፓን ቁርቁስ ሌላኛ ስርመሰረት(እስከ ዛሬ ያልተነገረንን) ያስቃኘናል።

ይህን ሁሉ ሲያደርግ ፀሃፊው ኢህአፖነቱን ቀርቶ የወላጆቹ ልጅነቱን ሁሉ ረስቶ እንደ ባዕድ ታዛቢ ሆኖ ነው። እናቱን ይታዘባል፣አባቱንም አይምርም ፣ኢህአፖንም ይታዘባል! ይህን መፅሃፍ የሚያነብ ሰው የግርጌ ማስታወሻውን ካላነበበ ከመፅሃፉ የሚያገኘው ጥቅም እጅጉን ይጎዳል ፨

መልካም ንባብ!

አንዳርጋቸው ጽጌ- የዚህን መጽሀፍ 70% ገቢ ለኢዜማ በስጦታ አበርክቷል

 

3 COMMENTS

 1. ፖለቲክ በአፍሪካ ህምም ነው የሚባለው በርግጥም እውነት ነው፡፡ ይኸውና አፋችሁን መክፈት ከጀመራችሁ ከ40 አመታት በላይ ሆነ፡፡ ውጤቱንም አየነው፡፡ አሁን ደግሞ ምንቀረህና ነው ይህን እንቶ ፈንቶ ዕርዕሰ የመረጥከው፡፡ ምን አለበት ይህን ህዘብ ለቀቅ ብታደረጉት፡፡ ምን ታደረጉ በሁለት ካርድ ትጫወታላችሁ፡፡ እንደ እናንተ ያለ የዞረበትና የተደናገረ ወንጋራ የ60ዎች ትውልድ ሀገር ማፍረስና በዕውቀት ድርቅ የተማታ ትውልድ እንዲፈጠረ አደረጋችሁ፡፡ እኔ የሚገረመኝ ወያኔን እንወቅሳለን እንጂ ፈጣጣና ይሉይኝታ ቢሶች እንደእናንተ ያለ ትውልድ አይቼ አላውቅም፡፡ ፓርቲ እና ተቋም ስታፈርሱ እንደገና ስተመሰረቱ እንዲሁ እኛንም ሰላም ነስታችሁ ሀገሪቷንም እንደ ቤተ ሙከራ አይጥ ስትመራመሩባት እዚህ ደርሰናል፡፡ የተረገመችና እና ህዝብ አልባ የሆነች ሀገር ይመስል በየስብሰባው እና በየፓርቲው ውይይት እናንተን ብቻ በማየት ከ30 አመታት በላይ ሆነ፡፡ አሁን ደግሞ ኢዜማ ኢዜና ኢዜጋ እያላችሁ ከፈረንጅ በምታገኙት እርጥባንና ድጎማ ታደንቁሩናለችሁ፡፡ ለማንኛውም ይህ መፃህፍ መደናገር እንጂ ሌላ ነገረ ስለማይኖረው ባይታተም ምርጫዬ ነበር፡፡ እናንተ ኮተታሞች ሰላማችሁ ይጥፋ፡፡

 2. ውድ ማስተዋል፣
  አጻጻፍህ ማስተዋል የጎደለው ይመስላል።
  ገና ያላነበብከውን መጽሐፍ፣ “ይህ መፃህፍ መደናገር እንጂ ሌላ ነገረ ስለማይኖረው ባይታተም ምርጫዬ ነበር” አልክ!
  እንዴት ነው ነገሩ? አቶ አንዳርጋቸው አንተን ማስፈቀድ ነበረበት?
  “ኮተታሞች” ማለት አሁን ምን ያስፈልጋል? እራስህን እያዋረድክ እኮ ነው?
  አስሬ ፓርቲ እያሉ ግራ አጋቡን ያልከውን እቀበላለሁ።
  የነመለስ፣ የነአንዳርጋቸው፣ የነሌንጮ ትውልድ መንቀፍና ማውደም፣ ሥልጣን ለመያዝ መከፋፈል እንጂ
  እስካሁን አልቀናውም። ኢትዮጵያዊ እንደ መሆናቸው ተሳትፎአቸውን መከልከል አንችልም።
  ብትችል የአቶ አንዳርጋቸውን መጽሐፍ ገዝተህ አንብብና ያልተስማማህን ነጥቦች ዘርዝረህ ስታበቃ
  ያንተን አማራጭ የምትላቸውን በዚሁ በሳተናው ላይ አስነብበን! አደራ!

 3. ” አሁን ደግሞ ኢዜማ ኢዜና ኢዜጋ እያላችሁ ከፈረንጅ በምታገኙት እርጥባንና ድጎማ ታደንቁሩናለችሁ፡፡ ”

  Have courage to mention the CIA.

  My understanding is G7 was an MI6 or CIA creation, for the purpose of neutralizing Ethiopian nationalists. Neither Berhanu Nega nor Andargachew Tsige could be trusted. Why was Berhanu made “president” of this ኢዜማ given his records ? He shouldn’t hold key positions, perhaps only advisory positions.
  Abiy, whom the West seems to like, is also not trustworthy.

  Ethiopian politics has to be cleansed from agents of the West ASAP. Till that happens trouble will not stop in the country.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.