በሬ ሞኙ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ ሆነ የኢትዮጵያውያን ነገር! (ሰርፀ ደስታ)

በሬ ሞኙ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ ሆነ የኢትዮጵያውያን ነገር!

ኢትዮጵያን ወደሠላማዊ መስመር ማምጣት ቀላል ነው ብይ ለመናገር ባልደፍርም ከተፈጠረው አጋጣሚ አንጻር ግን የሚቻል ነበር፡፡ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በማለቱ ብቻ ምን ያህል ሕዝብን መያዝ እንደቻለ አይተናል፡፡ እንግዲህ ሰዎችን በሚናገሩት ማመን ክፋት አደለም፡፡ በእርግጥም እንደቀደሙት አባቶች ቢሆን የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ ይባላል፡፡ ቃል እጅግ ከባድ እንደሆነ በብዙ የቀደሙ ነገስታትም ታሪክ እናነባለን፡፡ በታላቁ መጻፍ ቅዱስ እንደምናየው ብዙ ነገስታት ቃላቸውን ላለማጠፍ ሲሉ ያልፈለጉትን ስለቃላቸው ሲፈጽሙ እናያለን፡፡ ዳንኤልን ዳርዮስ ወደ አንበሳ ጉድጓድ እንዲጣል ግድ ያለው ስለቃሉ ነው እንጂ ዳንኤልን እጅግ ይወደው ነበር፡፡ በተለይ የነገስታት ቃል እንዲህ ነው፡፡ ይሄ እውነት እግዚአብሔርንም በማያውቁ ለሰዎች ጽኑ ሆኖ የኖረ ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን እንደዛ አደለም፡፡ በመሪነት ቦታ ተቀምጠው ውሸትና ሕዝብን ማጭበርበር ከጅምሩ የሥልጣን መቆያ ትልቅ ስልት አድርገው ስለሰለጠኑበት አትዋሹ ብንል እንኳን ታዲያ እንዴት ስልጣን ላይ ሊንቆይ እንችላለን ካልዋሸንና ካላጭበረበርን ቢሉን አይፈረድባቸውም፡፡

የኢትዮጵያ መንግስታዊ ሥርዓት በወንበዴዎች እጅ የገባው ዛሬ ሳይሆን ከጅምሩ የዛሬውን የውንደብድና መዋቅር እዚህ ያደረሱ መሥራቾች ከተነሱበት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ነው፡፡እንግዲህ ለእውነት ብዙ የለፉና የታገሉ ሁሉ እያለቁ ዛሬ ቦታውን ሙሉ በሙሉ በማጭበርበር እድሜ ልካቸውን በሰለጠኑ ተነጥቀዋል፡፡ አብይ አህመድ የዚህ መዋቅር ከልጅነቱ ጀምሮ ያሳደገው እንዴት አንደሚዋሽና ማጭበርበር እንደሚቻል የሰለጠነ እንጂ ሕዝብና አገርን እንዴት መምራት እንደሚቻል የሰለጠነ አደለም፡፡ ለውጥ ለውጥ የተባለለት እውነት በኢትዮጵያና ሕዝቧ ላይ ስቃይና መከራ ሲፈጽም የኖረው ቡደን ስልታዊ አካሄድ እንደነበር አሁን አሁን እውነቱ እየተገለጠ ነው፡፡ እርስ በእርሳቸው ይጠባበቃሉ፡፡ ከዚህ ስልጣን ቦታ ከለቀቁ አብዛኞቹ ከሌላ ወንጀል ነጻ ናቸው እንኳን ብንል ከዘረፋ ወንጀል ነጻ ሊሆኑ የማይችሉ ናቸው፡፡ አብዛኞቹም በመደበኛ ትምህርት አልፈው እዚህ የደረሱ ሳይሆን በተገዛና በራሳቸው የትምህርት ተቋም ብለው በከፈቱን እንደ ሲቪል ሰርቪስ ያለ ተቋም ያለፉ ናቸው፡፡ ያለ አንዳች የአካደሚክ መስፈርት ትልልቅ የትምህርት መረጃ የያዙ ናቸው፡፡ እነሱ በዚህ አልፈው የትምህርት ጥራት ለእነሱ ጉዳያቸው አደለም፡፡ በሁለት ወር ማስተርስ የሚሠጥ ተቋም በሕጋዊነት መዝግበው የሚያስተናግዱትም በምክነያት ነው፡፡ ከሁለት ወሩ ማስተርስ ተመሳሳይ የሆነ የትምህርት ችሎታቸው ነውና እነሱ ያዋቀሩት መዋቅር የተሞላው፡፡

ጉዳዩ የአካደሚክ ትምህርት ከመማር ጋር በቀጥታ ስለሚገናኝ ሳይሆን በወንጀልና በማጭበርበር የሚኖር መሪ ሥርዓትን ማስጠበቅ ራስን ለሕግ አጋልጦ እንደመስጠት ስለሚሆንበት እንጂ፡፡ የቀደሙ ያልተማቱት መሪዎችማ የሰሩትን ታሪክ አይተናል፡፡ የተማሩት ለማሰባሰብና አገርን ወደተሻለ ለማድረስ ትምህርትንም ከታች ጀምረው ብዙ ለፍተው ነበር፡፡  እነዛ መሪዎች ከልብና ከቁጭት ይሰሩ ስለነበር እግዚአብሔርም ረድቷቸው ዛሬ ድረስ በታላላቅ አገራት ሳይቀር ስማቸው በከፍተኛ ክብር ይነሳል፡፡ታላቁ መሪ አጼ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ማድረግ፣ አድዋን የሚያክል ድል ለዓለም ሳይቀር ማስመዝገብ መቻል ብቻም ሳይሆን በዛን ወቅት አለም ላይ አለ የተባለን ቴክኖሎጂ ወደ አገር አምጥተው አገርን እንዴት እንደለወጡት ዛሬ ላለው ትውልድ ማስተዋሉ ለጠፋበት ሊገባው አይችልም፡፡ ሚኒሊክ ዛሬም ድረስ ብርቅ የሆነውን የምድር ባቡር በስኬታማነት ዘርግተው አሳይተዋል፡፡ አንደነ ስልክ የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎች አን ገርሀም ቤል ከፈጠሩት በጥቂት ዓመታት ነበር ኢትዮጵያ የደረሰው፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ በቴልፎን የት ነች? አልም ላይ አለ የተባልን ሁሉ ለአገር አምጥተዋል፡፡ ዝርዝሩን ከታች አስቀምጣለሁ፡፡ ሚኒሊክ ትምህርትን ጀምረው ኃይለስለሴ በስፋት አስፋፉት፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችንም ጨምሮ ታላላቅ የትምህርት ተቋማትን መሠረቱ፡፡

እኔ ከልጅነት ጀምሮ ያለፍኩት ኃይለስላሴ በአሰሩት ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሊያውም እጅግ ዘመናዊ ቁሳቁሶች የተሟሉበት፡፡ ይሄን የምለው እኔ የከተማ ልጅ አደለሁም፡፡ እልም ካለው ገጠር በተሰራ ትምህርት ቤት ነው ትምህርት የጀመረኩት፡፡ የሚገርመው ብላክ ቦርድ የሚባለውን በትክክል ያወኩት ስድስተኛ ክፍል ጨርሼ መለስተኛ ስገባ ነው፡፡ እኔ በተማርኩበት ኤለመንተሪ የነበረው ዛሬ በምዕራባውያን የማየው አረንጓዴ የሚመስል ቀለም ያለው ቦርድ ነበር፡፡ ክፍሎቹ፣ መቀመጫና ዴስኮቹ ዳስተሮቹ ሳይቀሩ እጅግ የሚያምሩ ነበሩ፡፡ እንግዲህ ይሄ ትምህርት ቤት የተሰራው ለሀብታም አደለም፡፡ ትምህርት ለሚፈልግ ሁሉ እንጂ፡፡ በኃይለስላሴ የተሰራው ት/ቤት ከነውበቱ ጠብቆጭ ስለተማርኩበት አሁን ሳስተውል ምን ያህል እነዛ ሰዎች አገርንና ሕዝብን ለማሳደግ እንደለፉ አያለሁ፡፡ ዛሬ ወሮበሎች በሚፈነጩባት አዲስ አበባ ኃይለስላሴ ታዓምር የሚመስሉ ውብና ኩራት የሚሆኑ ግንባታዎች ሰርተዋል፡፡ ለማስተዋል፣ መዘጋጃ ቤቱን፣ ፖስታ ቤቱን፣ ባንኩን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ጀምሩ በቀጥታ ዛሬ ታላላቅ የምንላቸውን አገራት እያየ የተሰራ ነበር፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ሆስፒታሎች ከጥሩነሽ ዲባባ ሆስፒታል በቀር በሙሉ የተሰሩት አሁንም በኃይለሥላሴ እንደሆነ ስናስብ ከ50 ዓመት እየተጠጋው ባለ ጊዜ ውስጥ ምን ያህል ጊዜና የሰው ሕይወት እንደባከነና እንደጠፋን እጅግ ያስቆጫል፡፡ ይሄን ሁሉ የሚያደርጉት መሪዎች ቤተመንግስታቸው የዛን ያህል የተጋነነ አደለም፡፡ ያም ቢሆን ለመንግሰት መዋቅር ታስቦ ደረጃውን ጠብቆ ነበር፡፡ ዛሬ ስድስት ኪሎ እየተባለ የሚጠራው ካምፓስ ኃይለስላሴ ለትምህርት ከፍተኛ ክብር በመስጠትና ተማሪዎችንም ለማበረታት ለዩኒቨርሲቲነት ያዋሉት ቤተመንገስታቸው ነበር፡፡  ዛሬ በ50 ዓመት ውስት ስንቶች ከምንም ተነስተው ታላላቅ በሆኑበት ወቅት ግን ኢትዮጵያ እዛው ብትቆም አንኳን መልካም በሆነ፡፡ ሕግም ሥርዓትም ጠፍቶ የመንግስት መዋቅር በወንደበዴዎች እጅ ወድቆ እናየዋለን፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ እስከዛሬም ሙጥኝ ብሎ ያልለቀቀን ያ የ60ዎቹ ትውልድ ዛሬ በአሳደጋቸው ልጆቹ ወሮናል፡፡ አዝናለሁ፡፡ እነ አብይ የዚህ ከሀዲና አገር አጥፊ ትውልድ ከልጅነት ጀምሮ እያሰለጠነ ያሳደጋቸው መሆነቸው ይሄው አረጁ ልንገላገላቸን ነው ባልንበት ወቅት ተተክተው የቁልቁሊቱን ጉዞ ቀጥሏል፡፡

አብይ አህመድ በመቶ አመት እንደኔ የሰራ የለም ይላል፡፡ እንዲህ ነዋ የሠለጠነው፡፡ የቤተመንግስት አዳራሽ አደስኩ ብሎ በትልልቅ ሚዲያ ያወራል፡፡ አገር ግን እየሞተች ነው፡፡ ሁሉ ነገር ቆሞ የቤተመንግስት አዳራሽና የከተማ ፕሮጄክት በሚል እየቆመረ ነው፡፡ እንደተናገረውና እንደመሪ ቃሉን ቢጠብቅና ኢትዮጵያውያንን ለማሳተፍ ቢሞክር አዲስ አበባን ሳይሆን በጥቂት ጊዜ ኢትዮጵያን ሙሉ ውብ ማድረግ በተቻለ ነበር፡፡ ችግሩ በማታለል ይሳካል የሚል አሳዳጊዎቹ ያስተማሩትን እሱኑ በሥራ አዋለው ይሄው ዛሬ ለአብይ አህመድ መዋቅር ኦሮሞነት ካልሆነ ሌላው አለመታመን ብቻ ሳይሆን በጠላትነትም ተፈርጇል፡፡ በይፋ ሕዝብና ሕዝብን በማጋጨትና ብዙ የውንብድና ሥራን የሚሰራውን ጀዋርን በፖሊስ እያሳጀበ በሕዝብ ላይ እየዘመተ እስክንድር ነጋ በአብይ የኦነግ/ኦፒዲኦ ከኋላ በሚደገፈው ወንበዴ ቡደን ሕዝብ ራሱን እንዲከላለክል በማደራጀቱ በይፋ ጦርነት የተከፈተበት ጠላት ሆነ፡፡ አብይ እስክንድር ነጋን ከአሳዳጊዎች አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ እስክንድር እድሉን ከአገኘ ነውራችንን ሁሉ አደባባይ ያወጣብናል የሚል እጅግ የሚፈሩት ሰው ነው፡፡ በአለፈው እስክንድር የአዲስ አበባን ጉዳይ አስመልክቶ የተናገረው ስህተት አልነበረም፡፡ ኋላ እስክንድር ዋሽቷል ለማለት እንደልባቸው በያዙት ሚዲያ ወጥተው እናቶችን አናፈናቅልም፡፡ ታሪክ አናጠፋም ሊሉን ሞከሩ፡፡ ደርሶ ለእናት አዛኝ መምሰል፡፡ እናቶች መስለውኝ ወልዳ ቤት ተኝታ በነበረቸው ሳይቀር ቤቷን በላይዋ ያፈረሱት፡፡ ሕጻናት ከትምህርት ቤት ሲመጡ ቤታቸው ፈርሶ በሕወታቸው ሁሉ ሊረሱት የማይችሉትን ሰቆቃ የተጋፈጡት፡፡ አስመሳዩ አብይ ሲጀምር በትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ቦረሳ ማድል ጅመሮ ነበር፡፡ ቦርሳ ማደል መልካም ነው፡፡ ግን ዞረው የሚገቡበትን ቤት ማፍረስና ሜዳ ላይ መጣል ከእነጭርሱም ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ማደረግ አረመኔነት ነው፡፡ ያ ሁላችንም ያየነው አረመኔያዊ ድርጊት እንዳይደገም ነው እስክነድር የተናገረው፡፡ ለእናት አዛኞች አይናችን እያየ ያለውን አረመኔነታቸውን አዛኝ ነን ይሉናል፡፡ እግዚአብሔር ያያል፡፡ ይፈርዳልም! አይሳካላችሁም!

አብይ አህመድ ከየአገሩ እስረኞችን ማስፈታት መልካም ነው፡፡ ከቁጭትና እውንም ከወገናዊነት ቢሆን ትልቅ ክብር ነበር፡፡ ችግሩ አሁንም እያንዳንዷን ድርጊትህን ለራስህ ማስታወቂያ የምትሰራው እንጂ ዛሬ በመላ አገሪቱ እየሆነ ያለው ላስተዋለ ሥራህ የጎደፈ ነው፡፡ ቅን ልብ ከሌለበት አይሳካም፡፡ ይሄው ሕዝብ ከሕዝብ ስታጋጩ ብዙ ወራት አለፈ አሁን በዩኒቨርሲቲ አዲስ የሆነ ስልት የተጀመረ ይመስላል፡፡ አዝናለሁ፡፡ የብሔር ፖለቲካ ጉዳይ የማንደራደርበት ነው የሚሉት ወደው አደለም፡፡ ዛሬ አገርና ሕዝብን በይፋ ጦርነት ከፍቶ እያመሰ ያለን ቡድን በሆቴል እያንደላቀቀ አገርና ሕዝብ መከራ ያያል፡፡ የአብይ መዋቅር አደገኛነቱ ለዚሁ የአገር አጥፊ ቡድን ቁልፍ የገንዘብ ምንጭ የሚሆኑ ተቋማትን በዚሁ ቡድን የውስጥ አርበኞች ማስያዙ ነው፡፡ ዛሬም እላለሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉዳይ አሳሳቢ ነው፡፡ ምዕራባውያኑ እውነቱን አውቀውታል፡፡ ችግሩ ከጅምሩም ሲናገሩት የነበረው ነው የሆነው፡፡ በተለይ ወደመጨረሻ አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ኢትዮጵያ ሊረከብ የሚችል ቡድን ጉዳይ አሳስቧቸው ነበር፡፡ አሁን የለውጥ ሐዋርያ ነኝ የሚለው ቡድን ችግር እንዳለበት አውቀዋል፡፡ የተጃጃልነው እኛ ነን፡፡

አሁን የፕሬስ ሕግ እየረቀቀ ነው፡፡ ዓላማው ያው ለውንብድናቸው አላፈናፍን ያሏቸውን እንደ እስክንድር ያሉትን ለማፈን ነው፡፡ እንጂማ ዋና የሐሰትና የጥላቻ ወሬ ነዥውን እኮ አሁን በአለው ሕግ ራሱ መጠየቅ በቻለ፡፡ የጥላቻ ንግግር በሕዝብ ላይ አደለም በግለሰብም ወንጀል ነው፡፡ ውሸት ከተባለ ደግሞ ዋና ችግሩ ከራሱ ከአብይ ነው፡፡ አብይ ቤተመንግስት ወታደሮች ሲገቡ የሱሉልታ ሕዝብ መንግስታችን ተነካ ብሎ ነቅሎ እየመጣ ነበር ሲል ምን ማለት ነው? ይሄ ጉዳይ በሌላ አገር ቢሆን አብይ እንደኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነት ሊቀጥል ባላስቻለው ነበር፡፡ በቀጥታ ዘረኝነቱንና ሌሎችን አግላይነቱን የገለፀበት ነው፡፡ ቴድሮስ ጸጋዬ ያወጣውን እውነትስ? የትኛውም ሕግ ቢኖር ቴድሮስ ጸጋዬ ቃል በቃል ሰዎቹ የተናገሩትን ነው ያቀረበው፡፡ እንግዲህ ይሄን የሀሰት ዜና በሚል ሊከሰስ ነው? ጥላቻውንስ እየሰበከ ያለው ማን ነው፡፡ በኦሮምኛ ለኦሮሞ ጥላቻን እየሰበክህ በአማርኛ ኢትዮጵያ ኢትየጵያ ከማለት የከፋ ዘረኝነት አለ? መጀመሪያ ወደ ነገሮች ከቅም በላይ ከለማወቅ ብለን ብዙ ለመምከርም ሁኔታዎችንም ለመጠቆም ሞክረናል፡፡ በሬ ሞኙ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ እንደተባለው ማንነታችሁ ሳይገባን ብዙ ደግፈናል፡፡ ያኔ ኦነጋውያንን ያሳበዳቸው ምን እንደሆነ ግልጽ ሆኖልናል፡፡ ለ50 ዓመት የለፉበት የጥላቻና ዘረኝነት ሴራቸው በኢትዮጵያዊነት ሊያስቀሩብን ነው በሚል ስለተጠራጠሯችሁ ነበር፡፡ በተቃራኒው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በደገፏችሁ ወቅት፡፡ አሁን ተማምናችኋል፡፡ አምኑን አዲስ አበባ ላይ ታከልን ለምን እንዳስቀመጥን ተረዱ ያላችሁበትን አሁን በተግባር እያየንው ነው፡፡ ታከለን ብቻ ሳይሆን መዋቅሩን ሁሉ፡፡ አፋኝ ፖሊስና ደህንነቱን ጭምር፡፡ ሒልተን ሆቴል ከሕዝብ ጎን መሆን በተሻለው ነበር፡፡ የውንብድና ተባባሪ በመሆኑ ዋጋ መክፈሉ አይቀርም፡፡ ከልካዩ የሆተሉ ባለስልጣንም ላያዘልቁት ራሱን በከለ፡፡ አሁን አንዱን ኦነግ ይሾምበታል ነውር አይፈሬው፡፡

የኦሮሞ አክቲቪስት ነን የምትሉ አስተውሉ፡፡ በተለይ ኒውትራል የምትመስሉ፡፡ አትሳሳቱ፡፡ በምንም መልኩ አልቻላችሁበትም፡፡ ሰሞኑን የአቤ ቶክቻው ሁኔታ አላማረኝም፡፡ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ይመስል ነበር፡፡ ግን እየወረደ ይመስላል፡፡ የአማራ ክልል የፈራነው እውነት እየተከሰተበት ነው፡፡ ከማንነቱ የወጣ ሕዝብ አደጋ ላይ ይወድቃል ስንል ነበር፡፡ አሁን የሚታየው እውነት የለየለት መምከን ነው፡፡ የሕዝብ እሴቶች፣ እምነት ባሕል በፍጥነት እየወደሙ የአለሌነት ባሕሪ እየወረረው ነው፡፡ አዴፓ የሚባለው ቡድን ያው ያደገበትን የሴራ ፖለቲካ እንጂ ሕዝብን ከልብ እየታደገ ለመሆኑ እንጃ፡፡ እንዲህ ነው ሕዝብ የሚመክነው፡፡ ሁሉም ያስተውል፡፡ በሬ ከአራጁ እየዋለ ነው፡፡ በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ…!

ታላቁ ሚኒለክ ወደ አገር ካስከቧቸው ቴክኖሎጂዎች በከፊል

ልዑል አባት ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ! አሜን!

3 COMMENTS

  1. የፈለግኸውን ቀባጥር:: በአስተዋይነት ቅንነትና ርህራሄ በኢትዮጵያ ታሪክ ከእምዬ ሚኒልክ የሚወዳደር ብልህ መሪ ቢኖር ዐቢይ አሕመድ እንደሆነ እውነትን አይተን ለማንክድ: የእውቀት አድማሳችን ትንሽ የሰፋ ሰዎች በየእለቱ የምንረዳው ሀቅ ነው:: ፅሁፍህ እንደተለመደው እርስ በርስ የሚጣረስና የተሳከረ ነው:: በቃ ዐቢይን የሚወዳደር ጭንቅላት የለም:: ለሁሉም መስክ የተዘጋጀና ከበቂ በላይ እውቀት ያለው መሪ ነው:: እናንተ ትናንሾቹ ምንም ብትገዘግዙት የሚወድቅ ዛፍ አይደለም:: በሞከራችሁ ቁጥር የእናንተን ቁጫጭነት እያጋለጠ ነው:: አንተ ስርፀ ደስታ ለኢትዮጵያ ምን ሰራሁ?? ብለህ እራስህን ለጥያቄ አቅርበህ ታውቃለህ?

  2. እጅግ በጣም ግሩም ጽሑፍ ነው።እውነትን በግልጽ የሚያስቀምጥ፣ያንዣበቡብንንና እያአቃዩን ያሉ የዘረኝነት ህመሞችን የሚያብራራ ወቅታዊ መጣጥፍ ነው።ችግሩ ሰሚ የለም።ድንቁርናውና አፍዝ አድንግዙ ዳር እሥከዳር እግር ከወርች አሥሮናል። ትብታብ የሚመስለው የገዢዎች አፈ ቅቤነትና ማስመሰል በተለይም የአቢይ ቅጥፈትና ዕብለት ብዙዎቻችንን ስላነሆለለን ተለያይተናል፤ ግራም ተጋብተናል። ከምናየው ይልቅ የምንሰማውን የምናምን ብዙ ነን። አሠለጦቹ ኦነጎች እነአቢይ ደግሞ ይህን ባሕርያችንን ሥለሚያውቁ በደንብ ይጠቀሙበታል።ስለዚህም በአዴፓ ሥም ከሠገሠጉብን አማራ መሠል አማራ ጠሎች ጋር በመተባበር የኢትዮጵያዊነት አንዱ ፈርጥ የሆነውን አማራና ሌላውንም ሕዝብ ማጥቃታቸውን ይቀጥላሉ።ሆኖም መጨረሻቸው አያምርም።

  3. “ስለዚህም በአዴፓ ሥም ከሠገሠጉብን አማራ መሠል አማራ ጠሎች ጋር በመተባበር የኢትዮጵያዊነት አንዱ ፈርጥ የሆነውን አማራና ሌላውንም ሕዝብ ማጥቃታቸውን ይቀጥላሉ።ሆኖም መጨረሻቸው አያምርም።”

    ትንሽ እንኳን የማታፍሩ ጉዶች:: አማራውን አታውቀውም::
    ያንተ ወያኔ ተመልሶ አማራውን ያድንልናል?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.