ሰኔ አንድ ቀን ፍትህን ፣ዲሞክራሲን ፣የሰብዓዊነትን ክብረት ለሚያውቅ ሁሉ የሃዘን ቀን ነው – መስከረም አበራ

ሰኔ አንድን ስናስታውስ መለስ ዜናዊ ከነብርቱ ጭካኔው ሲያስተኩስ ፣ወርቅነህ ገበየሁ ግዳይ ሲጥል ፣የደብተር ቦርሳ ያነገበ አንድ ፍሬ ልጅ “እኔ እፈራለሁ” እያለ እንደፈራው ልስልስ ሰውነቱን ጥይት ሲበሳው፣እናት ልጇን ፍለጋ ስትባዝን የመለስ ወ ወርቅነህ ባሩድ አስፍልት ላይ ሲዘርራት ፣የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች በደም ሲነከሩ በአጠቃላይ ዲሞክራሲ ላይ ሲተኮስ፣ሰብዓዊነት ላይ ሲጨከን የሚያሳይ ትዕይንት በልቦናችን ያልፋል።
ሰኔ አንድን አስቦ መለስን አለመርገም የወርቅነህ ገበየሁን በፍርድ አደባባይ መቆም አለመናፈቅ አይቻልም። ፍርድ የሚገባውን ወርቅነህን ከጎኑ ሻጥ አድርጎ አለምን ይዞር የነበረውን ጠሚ አብይም አለመታዘብ አይቻልም።

በአንፃሩ ይህን ወንጀል ለፍርድ ለማቅረብ የሚለፉትን እነ ዳኛ ፍሬ ህይወት፣አቶ ምትኩ ተሾመ፣ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻን አለማክበር አይቻልም።እነሱ ነፍሳቸውን ሸጠው ይዘውት የተሰደዱት እውነት ሃሰትን ቸክቶ ቦታውን እንዳይዝ የሚደረገው ጥረት አሁንም ሌላ ሰኔ አንድ ላለመምጣቱ እርግጠኛ እንዳንሆን የሚፈታተን ነገር አለው።የፖለቲካችን አዙሪት መሰበሪያው የት ይሆን ያስብላል!

የሆነ ሆኖ የሰኔ አንድ ሰመዓታት የሁልጊዜ ሃዘኖቻችን ናችሁ፣ነፍሳችሁን ፈጣሪ ያሳርፍ ፣አንረሳችሁም!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.