ለማኙና የኢትዮጵያ ህዝብ! (ዘውድአለም ታደሠ)

አብይን ወደካርቱም ይዛው የሄደችው አውሮፕላን ላይ ቴክኒሺያን ሆኖ የሄደው ጓደኛዬ ነው። ትናንት «ከአብይ ጋር ካርቱም ደርሼ መጣሁ» ሲለኝ «ኦህ ፎቶ ተነሳሃ አብረኸው?» አልኩት። «አዪዪ» አለኝ በሃዘኔታ። «ስንመለስ እነሳለሁ ብዬ አስቤ ነበር። ሲመለስ ግን ከሰባ በላይ በእስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ይዞ ስለመጣ ግፊያና ለቅሶ ነበር። አልተመቸኝም» አለኝ።

አብይን ልታግዘው ቢበዛንኳ አልፎ አልፎ ልትተቸው የምትችለው እንጂ በቋሚነት ደምስርህ እስኪገታተር እያማጥክ ምትቃወመው መሪ አይደለም።
አብይ ተቃዋሚዎችን አጀንዳ ያሳጣ መሪ ነው። አሁን አሁንማ ሚቃወሙትን ሲያጡ ለምን ፎቶ ተነሳ? ሐገሪቱ ልትፈርስ ደርሳ ለምን ችግኝ ተከለ? ማለት ሁሉ ጀምረዋል

አዳሜ ፍሬንድሺፕ ተጎልታ ተረከዟን እያስሞረደች፣ የብርጭቆ ወረቀት የመሰለ ቆዳዋን ለማለስለስ 5 ሺ ከፍላ ፌሻል እየተሰራች፣ «ሐገሪቷ ልትፈርስ ደርሳ አብይ ለምን ችግኝ ተከለ?» ብላ ትውረገረጋለች። ልክ ሐገሪቷ ልትፈርስ ነው ብላ ሁሉን እርግፍ አርጋ ፆም ፀሎት የያዘች እኮ ነው ምትመስለው አዳሜ!

የምሬን እኮ ነው። ምድረ ፖለቲከኛ ሐገሪቱ ልትፈርስ ነው!! ይልህና በየሳምንቱ ግሮሰሪ እቁብ ሊጥል ሲመጣ ታገኘዋለህ። ብራዘር ሐገሪቱ ምትፈርስ ከሆነ እቁብ ምን ይሰራልሃል? ያለህን ይዘህ አትነካውም እንዴ? በምትፈርስ ሐገር ላይ በሶስት አመት ሚወጣ እቁብ ይገባል እንዴ?


አዳሜ ሐገሪቱ ልትፈርስ ቋፍ ላይ ነች!! እያለ ልጅ ይፈለፍላል። ቆይ የምትፈርስ ሐገር ላይ ልጅ ይወለዳል እንዴ? የታባቱ ሊያሳድጋቸው ነው? ኦገኔ … ሐገሪቱ ልትፈርስ ነው የሚለው ቁጪ በሉ ሁላ ሐገሩ ላይ የሃምሳ አመት ፕሮጀክት ቀርፆ ነው ሚንቀሳቀሰው!

ለማንኛውም አብያችን እያኮራን ነው! የአፍሪካ መሪዎችኮ ሰው ሐገር ሲሄዱ ሚጎበኙት ሺሻ ቤት ነው። ጭነው ሚመጡት ደሞ ቫያግራና ብራንድ ሽቶ ነው። አብይ ግን ከእስር ቢለቀቁ እንኳ ወደሐገራቸው ሚሳፈሩበት ከሌላቸው ከሐገሩ ምስኪኖች ጋር እየተጋፋ ነው ሚመጣው። አሁንማ ሁሉን ነገር ለመድነው! ነፃነቱንም ለመድነው። የፈለጉትን ለፍልፎ አለመታሰሩንም ለመድነው። ሰው ያሻውን አመለካከት ይዞ ካሻው ፓርቲ ካሻው ሚዲያ እንዲያቋቁም መፈቀዱንም ለመድነው! መሪ ዝቅ ብሎ ሰው ሰው የሚሸት ስራ ሲሰራ ማየቱንም ለመድነው። የትናንቱን ጭቆና፣ የትናንቱን ግፍ፣ የትናንቱን የዲሞክራሲ ረሃብ ሁሉ ረሳን!! ዛሬ አንድ ሰውዬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥበት ያለውን አዳራሽ ተከለከለ ብለን ኡኡ እንላለን። ትናንት ግን እራሱ ሰውዬው የትኛው እስር ቤት እንኳ እንዳለ አናውቅም ነበር። አረ ከሱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊቀበል የሚሰለፍ ጋዜጠኛም ባገሩ የለም ነበር!

ሳስበው ሳስበው እያደነቅን መቆየት የኛ ተፈጥሮ አይደለም። ኑሯችን ከማማረርና ከጦርነት ጋር የተቆራኘ ስለነበር ካልተቃወምን የተሳሳተ ቦታ ላይ የቆምን ይመስለናል። የተቃወመና ያለቃቀሰ ብቻ ትክክልና እውነተኛ ይመስለናል! ምን ላይ እንደነበርን በአንድ አመት ረስተናል! ትናንት በራሱ አንደበት «ጨለማ ክፍል ለአራት አመት ታስሪያለሁ። መፅሃፍ ቅዱስ እንኳ እንዲገባልኝ ብለምን ተከልክዬ ነበር» ያለው እስክንድር ነጋ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ሆኖ መግለጫ እንዲሰጥ ሲለመን እምቢ እያለ አዳራሽ ያማርጣል! ትናንት በፌስቡክ ፅሁፍ ወህኒ ወርዶ እግሩ እስኪላላጥ የተደበደበው እንደስዩም ተሾመ አይነት አክቲቪስት ዛሬ ከንቲባውን ከፍ ዝቅ አርጎ ተናግሮ በማግስቱ ከንቲባው ቢሮ በክብር ለውይይት ተጋብዞ አይተናል! ትናንት ሞት ተፈርዶበት ከየመን ከየት ሃይጃክ ሲደረግ የነበረ ፖለቲከኛ ዛሬ ቤተመንግስት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ቁጭ ብሎ ይማከራል!

ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ማንም ሰው ይሄን ስለተናገርክ ወንጀለኛ ነህ ተብዬ እታሰራለሁ ብሎ አይሳቀቅም። ዛሬ የሚሳቀቀው ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳይሆን ባለስልጣን ሆኗል! በስንት ምህላና ለቅሶ የመጣው ይሄ የነፃነት ጭላንጭል ግን እጃችን ሲገባ ረከሰብን! ሳስበው ሳስበው አብይ ራኒ ጁስ በቧንቧ ቢልክልን ሁሉ የለቅሶ ስታየል እንቀይራለን እንጂ ማልቀሳችንን አናቆምም! ሁሉ ነገራችን ከዚያ ለማኝ ጋር ይቀራረባል

ለማኙ ባጋጣሚ ሎተሪ ይቆርጥና አንድ ሚሊየን ብር ደረሰው አሉ። ጋዜጠኞች ከበውት «አሁን በብሩ ምን ልታረግበት አሰብክ?» ሲሉት
«መኪና እገዛበታለሁ» አለ
«ከዛስ?» ቢሉት
«በመኪና እየዞርኩ እለምናለኋ!» ብሎ እርፍ!

 

4 COMMENTS

 1. ተምቦላ ደርሶት መኪና በመግዛት እየተዘዋወረ ለመለመን ያቀደው ሰው ቧልት ተመችቶኛል። በፊትስ ቢሆን ዝም ብሎ ከሚቀመጥ በእግርም በአህያና በበቅሎ በመታገዝ እኮ መለመን ይቻል ነበር። ችግሩ ስጪ አለ ወይ ነው? ቀልድን ትተን ወደ ዶ/ር አቢይ የካርቱም ጉዞ ስናመራ የሚታየኝ ብዙ ነገር አለ። ከብዙ ባጭሩ እይታየ እንሆ። ከዚያ በፊት ግን እውቁ ኢትዮጵያዊ ከበደ ሚካኤል “ምን ጊዜም ቢሆን ህዝብ ማለት እውር፤ የማያመዛዝን፤ ወረተኛ፤ ጊዜ የሰጠውን ብቻ ደስ ለማሰኘት የተዘጋጀ ነው” ያሉትን ታሳቢ ላድርግ። የካርቱም መሪዎች የጦር መሳሪያን ተገን አርገው ከስልጣን ሲወጡ ህዝቡ እየወጣ ጀግና በማለት እንደተቀበላቸው ያለፈው ታሪካቸው ያመላክታል። ቆይቶ ደግሞ ጀምበራቸው ስትጠልቅ ያዘው ጥለፈው ማለታቸው በገሃድ የታየ እውነታ ነው። ይህ ባህሪ ከሃበሻው ባህሪ በምንም መልኩ አይለይም። የአባት ስማቸውን ረስተው ሐይለስላሴ ይሙት ይሉ የነበሩ መኮንኖች ናቸው ንጉሱንና በዙሪያቸው የነበሩ ሃገር ወዳድ ወገኖችን ገድለው መቀመጫቸውን ያደላደሉት። እናማ ፓለቲካ እነርሱም በየምክንያቱ ሲበላሉ ሃገርን ለአፍራሽ አፍራሽ አስረክበው ከሞት የተረፉት የቆም ሞትን ሙተው ታሪክን በማሳደፍ አንድ ጥይትና አንድ ሰው እስኪቀር እያሉ እንዳላፋከሩ ቆራጡ መሪያችን ጥለው በመፈርጠጥ በሃራሬ ራሳቸውን ካስጠለሉ ዘመናት አለፈ።
  የዶ/ር አብይ ወደ ካርቱም ማቅናት የቀናው በየእስር ቤቱ ታጉረው ለነበሩት ሃበሾች ብቻ ነው። በዚህ በኩል ጠ/ሚሩ የሚያደርጉትን መልካም ሥራ አደንቃለሁ። ከሳቸው በፊትማ ማን አስቦት? ከዚህ በዘለለ የሱዳን ፓለቲካ በቱርክ፤ በግብጽ፤ በሳውዲና በአረብ ኤሜሪትስ አጠብቂኝ ውስጥ የገባ ስለሆነ የሱዳን መለዮ ለባሾች እንዳሻቸው ማድረግ ጭራሽ አይችሉም። ለህዝብ ሥልጣን የማስረከብ ልምዱም የላቸውም። አሁን በካርቱም በጥይት የተቆሉት ዜጎች ከግብጽ የጸደይ እንቅስቃሴና ፍጻሜው መማር ነበረባቸው። በዚያው አደባባብይ በጊዜው የተከማቹትን ዜጎች በጥይት ናዳ ነበር ስፍራውን እንዲለቁ ያደረጓቸው። ግብጽ ልክ እንደ ሱዳን ከላይ እስከታች በወታደራዊ መዋቅር የተያዘች በመሆኗ የሲቪል አስተዳደር ጭራሽ አይታሰብም። ሰው በከንቱ ደሙን ያፈሳል። ጠ/ሚሩ ከሱዳን ወታደሮች ጋር በካርቱም ሲመክሩ የኤርትራው መሪ ግብጽ ላይ ለምክክር ተቀምጠው ነበር። ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ድርጊት እንጂ በገጠመኝ የሆነ አይደለም። ከናስር አገዛዝ ጀምሮ ግብጽ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የማትሞክረው ነገር የለም። ለዚህም ስኬት ሃገር በቀል የሆኑ ልዮ ልዮ ዘርና ሃይማኖት ተኮር የፓለቲካ ድርጅቶችን ያስታጥቃሉ፤ ያሰለጥናሉ ያለ የሌለ ንዋያቸውን ያፈሳሉ። የሱዳን መተራመስ ደግሞ ለግብጽ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ትልቅ እድል ነው። ወያኔና ሻቢያ ያለ ሱዳን ድጋፍ ከደረሱበት የፓለቲካ ማማ መድረስ እንደማይችሉ በጊዜው የተጻፉ መጽሃፍቶች ይጠቁማሉ። አሁንም ዞሮ ተመልሶ ያው ነው። ውሃ ወቀጣ። የከፋው ሱዳን ይጠለልና ከላይ በተጠቀሱት ሃይሎች እየተረዳ ሃገር ማተራመስ ነው። ሌላ ለውጥ ይመጣል ብሎ በማሰብ ራስን የእሳት ራት ማድረግ የሱዳንን የፓለቲካ ውስብስብ በደምብ አለመረዳት ነው። በአንድ ወቅት ዶ/ር አል ቱራቢ እንዲህ ብለው ነበር። የአፍርቃ ችግር መሪዎች ብቻ አይደሉም፡ ህዝቡም ጭምር እንጂ። እውነት ነው። ለውጥ በአፍሪቃ የጉልበትና ጥገናዊ ብቻ ነው። ከዙፋን ከተወጣም በህዋላ ሞት፤ በጉልበተኛ መገልበጥ ካልሆነ በስተቀር በቃኝ ብሎ ሥልጣን ህዝብ ለመረጠው ማስረከብ የማይታሰብ ነው። የወደፊቱም የሱዳንም እድል ፈንታ አፍራሽና አጥፊ እንጂ ለህዝብ ጠቀሜታ አያመጣም። የጠ/ሚሩም ጉብኝት ዝናብ እንደሌለው ደመና ተስፋ ሰጪ ብቻ ነው።

 2. “ዛሬ አንድ ሰውዬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥበት ያለውን አዳራሽ ተከለከለ ብለን ኡኡ እንላለን።” You must be stupid to try to make us believe in this reductionist and senseless view.

 3. I ask one question to the person who wrote this commentary. Didn’t the ethiopian people accept tigre liberation front when it marched to addis abeba in 1991, thinking that they would not be worse than Mengistu. but what happened in the last 29 years is common knowledge.
  ethiopians accepted Abiy ahmad because he said the things people wanted to hear, a lot of progress has been made, of course. But the process of change that started so well is looking like it is being derailed. there are so many indicators to this. and people have the right to question when they see things going wrong. no leader should be given a blanket support. that is the mistake people make and regret that they should have been more critical before they see persecutions, killings , torture, injustice. etc on their door steps.
  something is definitely wrong with the government, it is heading in the wrong direction and should be bold enough to face criticisms from people and try to resolve issues as they arise. the notion that ;i know everything’ does not work. democracy is about consensus.

 4. Well, what you are saying has some grain of truth. The truth is that the opposition and all citizens whose destiny should be the realization of systemic change not Abey’s reform of the criminal EPRDF are not doing their homeworks. You are right that it is wrong to deny the existence of better political situation than yesterday . But it is absolutely a stupid political way of thinking to give all these credits to Abey and his comrades who had been parts and parcels of a deadly political system for a quarter of a century . Yes, they deserve due appreciation for showing a relatively better change of mind and behaviour . But they are not interested and couragous to go for the fundamental process of creating a new political arena that must aim at the birth of a truly democratic system which is the only lasting solution for the very ill- guided and bloody system of EPRDf in which Abey and his comrades are operating . Agree or disagree, the political mentality of worshiping Abey is more dangerous than the problem you are talking about. Do you have any clue about how politicians of populism and narcissism behave ? They behave as a very down earth ordinary persons whereas they do something else in the very back of the open world . I am not saying we should dismiss what Abey is doing good. What am saying is we have to ask the question of making a fundamental change of a political system is not a matter of saying Abey is a a nice guy or not. It is a matter of questioning and rejecting the very purpose of enabling the bloody and criminal system of EPRDf of which Abey is it leader. Clear and simple ! Is there a very serious problem with regard to making opposition reliable and effective alternatives? No doubt ! But the mentality of using this weakness as a justification of making Abey indispensable is a terrrible political stupidity!
  It is not difficult how your way of political thinking is so neive or infantile or distorted when you trued to make people to beleive that the case of Eskindir Nega does not matter. This is quite enough to understand how your very naive or infantile political way of thinking . I hope we can a much more matured and critical way of exchange ideas!
  Have a good time buddy!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.